Get Mystery Box with random crypto!

ፍትሃዊነት ! ኢብን ሐዝም አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:- አንድን ሰው በሆነ ነጥብ ዙ | አስ–ሱናህ

ፍትሃዊነት !

ኢብን ሐዝም አሏህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል:-

አንድን ሰው በሆነ ነጥብ ዙሪያ ተከራከርኩት። ንግግሩን ግልፅ ማድረግ ስለማይችልም (ምላሱን ስለሚይዘው) ክርክሩን አሸነፍኩት። የተዘጋጀው መድረክም በኔ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ወደ ቤት የተመለስኩ ግዜ ግን(በተከራከርንበት ነጥብ ዙሪያ) ነፍሴ ላይ ቅሬታ አደረብኝ እና ከፊል ኪታቦቼን ማገላበጥ ስጀምር ትክክለኛውን ምላሽ ማግኘት ቻልኩ። ኪታቦቹ ላይ ያገኘሁት ምላሽ የኔ ንግግር ስህተት መሆኑን እና የተከራካሪዬ ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ነበር። ከእኔ ጋር ክርክሩን ከተጣዱት ባልደረቦቼ አንድ ሰው ነበር፤ ኪታቦቼን ስመለከት ያገኘሁትን ነገርኩትና ወደ ተከራከረኝ ሰው ጋር ሄጄ እርሱ ትክክል መሆኑን እኔ መሣሣቴን እና ወደ እርሱ ንግግር( አቋም) መመለሴን ማሳወቅ እፈልጋለሁ አልኩት። ባልደረባዬም ይህንን ለማድረግ ፍቃደኛ ሆንክ ? አለኝ
እኔም ፦ አዎ! በግዜው ይህን ማድረግ ቢቻለኝ ኖሮ እስከ ነገ አላቆየውም ነበር አልኩት።

ኢብን ሃዝም ይህን ታሪክ ከገለፀ በኋላ እንዲህ አለ፦
" እወቅ! ይህ አይነቱን ድርጊት መፈፀምህ እርሱን ሊፎካከረው ሚችል የሌለ በሆነው "ፍትሃዊነትን መጎናፀፍ" ጋር ውብ የሆነን ማስታወስ ያሸምትሃል ...

በእውነታው አንተ የተሸነፍክ ሆነህ ሳለ ፍላጎትህ አንተ አሸናፊ እንደሆንክ ማሳየት ወይም ካንተ ጋር ለሚጣዱ ባንተ ለሚታለሉና በውሳኔህ ለሚተማመኑት አሸናፊ መሆንክን ማሳየት አይሁን። ርካሽ ፣በጣም የወደቅክ ፣ ደካማ እና ግብ የሌለው ትሆናለህና።"

[ረሳዒል ኢብን ሃዝም 4/337].


https://telegram.me/tewihd