Get Mystery Box with random crypto!

አስ–ሱናህ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewihd — አስ–ሱናህ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewihd — አስ–ሱናህ
የሰርጥ አድራሻ: @tewihd
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.33K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው።
💎እዲሁም የኡለማዎች አጫጭር ፈትዋዎች ይለቀቁበታል إن شاء الله
ስተቴ በቁርአን በሀዲስ ላረመኝ الله ይዘንለት።

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-26 20:08:03 #አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ #
# የመጨረሻው ክፍል

ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ ቀን የአላህ ፍቃድ ሆነና ተያይዘው እሷ ዘንድ ደረሱ ። እሷም ታሪካዊ ጠላቶቿን ገና ከመድረሳቸው አውቃቸው ነበር ። እናም ሁሉንም በአንድ ላይ ግቡ አለቻቸው። እሷ ከመጋረጃ ጀርባ ስለነበረች አትታይም። ሁሉም ከገቡ ቡኋላ እንዲህ አለች «ስራውን ያጋለጠ ዱአ ይደረግለታል ። ሁላችሁም እንዲህ አይነት በሽታ ሊያጋጥማችሁ ለምን እንደቻለ ተናገሩ ችግሩን ያልተናገረ መፍትሄ አይገኝለትም ዱአም አላደርግለትም» ትላለች በዚህ ጊዜ የባለቤቷ ወንድም «እኔ ጥፋቴን በወንድሜ ፊት አልናገርም አፍራለው» ሲል ወንድሙ «ምንም አይደል ተናገር ያንተን መዳን ነው የምፈልገው» አለው አልናገርም ተናገር አልናገርም ሲባባሉ በመጨረሻ ደፍሮ « እንግዲያውስ ይቅርታ አድርግልኝ ሚስትህን ያባረርኳት እኔ ነኝ ፣ ደብድቤያታለው በህይወት ትኑር ትሙት አላውቅም ። ላንተ ትነግርብኛለች በሚል ስጋት ዝሙት እንደሰራች አስመስክሬባታለው» በማለት ራሱን አጋለጠ ። ወንድምየው ምን ያክል ሊሰማው እንደሚችል መገመት ይከብዳል።ያልጠበቀውን ነገር ሲሰማ እንደ እንጨት ደርቆ ቀረ ።ከዚያም ምስክሮቹም እንደዚሁ በሀሰት መስክሩ ብሎን ከመሰከርን ቡኋላ ነው እንዲ አይነት ችግር ያጋጠመን ብለው ራሳቸውን አጋለጡ

ሌላውም በተራው አንዲት ሴት አስፈራራለው ብሎ ህፃን ልጅ እንደገደለ ይናገራል። ሌላኛው ደግሞ ከሞት ያዳነችውን ሴት በ300 ዲናር ባሪያ ናት ብሎ የሸጠ መሆኑንና የገዛትም እንደዚሁ ባሪያዬ ናት ብሎ ሲስማት መርከቡ መገልበጡን ይናገራል ። ሁሉንም በየተራ ካናዘዘች ቡሀላ ማንነቷን ሳትነግረው ከሀጅ የመጣውን ባለቤቷን እሷ ወዳለችበት መጋረጃ እንዲገባ ትነግረዋለች ። «እኔ አጅነቢይ ጋር አልገባም ይላል» «ካልገባህ ወንድምህ አይድንም» ሲባል «የራሱ ጉዳይ አይዳን ከሀጅ ነው የመጣሁት አልገባም » ይላል እሷም ሀጅ የሄደውን ባሏን እየፈተነችው ነበር ። የባሏን ጥንካሬና ታማኝነት ካየች ቡሀላ እኔ ባለቤትህ ነኝ ስትለው በድንጋጤ ፈዞ ቀረ።

«አልሞትሽም አለሽ? ሲል» «አለሁ አልሞትኩም» አለች «አንቺ ባለቤቴ ነሽ» «አዎ ነኝ ይኸው እንደሰማከው ነው» አለች «ጥፋታቸውን እንዲያጋልጡ ያደረኩት በኔ ላይ እንዳትጠራጠር ነው ። ምን ምን እንዳሉ ሁሉንም ሰምተሀል። በኔ በኩል አላህ ስድስቱንም ሰዎች በተለያየ ችግርና መከራ አስተሳስሮ በማምጣትና በአንተ ፊት ስራቸውን እንዲያጋልጡ በማድረጉ አላህን አመሰግነዋለው። ካሁን ቡሃላ አንተ ሁሉንም መበቀል ትችላለ ፍርዱን ላንተ ትቼዋለው «ምን ይሁኑ ትላለ» ስትለው «አላህ ተበቅሏቸዋል ሁሉንም አውፍ ብየቸዋለው እና ዱአ አድርጊላቸው» ሲላት እንዲህ ስትል ዱአ አደረገች

«አላህ ሆይ ችግራቸውን አንሳላቸው ከአሁን ቡሃላ ይብቃቸው » ብላ ዱአ ስታደርግ ሁሉም ተፈወሱ ወደየመጡበት መሄድ ቻሉ ።

አላህ እሱን ለምትፈራው ሴት የሰጣት ተዐምር ነበር ።
ከታሪኩ የምንረዳው ነገር ቢኖር በድሮ ዘመን ወደ ሃጅ የሄደ ሰው ከሀጅ ቡሃላ ምን ያህል ጠንካራና ጥንቁቅ እንደሆኑና ከአጅነቢይ ጋር የነበረውን ግብግብ አይተናል ።
( ሂካይቱ ሷሊሂ ገፅ 81 ። ሸርሁል ጆርዳኒይ አርበኢነ ሀዲስ አነወዊይ ገፅ 84)

. https://t.me/tewihd/
229 viewsedited  17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:20:31 አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል 2 ሁለተኛዋ ፈተናዋ በምትኖርበት ቤት ውስጥ የሆነ ዘመድ ተብዬ ሰው መጥቶ እንደ አጋጣሚ ያያታል ፤በውበቷ ተሸንፎ ያለ ምክንያት እቤት ውስጥ ለማደር ይፈልጋል ፤ ለብቻው ማደሪያ ክፍል ተሰጥቶት እያለ በሌሊት እሷ ወዳለችበት ክፍል መጥቶ ነውረኛ ጥያቄ ይጠይቃታል። ከጮኸችና እምቢ ካለች አስፈራራበታለው ብሎ ጩቤ ይዞ ነበርና ከሴትዮዋ ጋር የሚያስተዳድራት ህፃን ልጅ…
243 views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 07:14:02 ሰሊም=ሚድያ pinned « ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ ከነብዩላህ ኢብራሂም ቤተሰብ ጀምሮ የነበሩ ድንቅ የአላህ ባሮችን ማንነትና ተአምር የሚያሳይ ተከታታይ የሆነ ታሪክ በቻናላችን ይዘንላቹ እንቀርባለን !!!! ኢንሻ አላህ በተቻለን አቅም በቀን ሁለቴ ጥዋትና ማታ የምንለቅ ይሆናል ሀቂቃ ታሪኩ በጣም አስተማሪና ወደ ህይወታችን አምጥተን ልንሰራበት የሚገባ ነው እንዲሁም በማንበብ ብዙ የማናቃቸውን ነገሮች እናውቃለን…»
04:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:33:59 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ ከነብዩላህ ኢብራሂም ቤተሰብ ጀምሮ የነበሩ ድንቅ የአላህ ባሮችን ማንነትና ተአምር የሚያሳይ ተከታታይ የሆነ ታሪክ በቻናላችን ይዘንላቹ እንቀርባለን !!!!

ኢንሻ አላህ በተቻለን አቅም በቀን ሁለቴ ጥዋትና ማታ የምንለቅ ይሆናል ሀቂቃ ታሪኩ በጣም አስተማሪና ወደ ህይወታችን አምጥተን ልንሰራበት የሚገባ ነው እንዲሁም በማንበብ ብዙ የማናቃቸውን ነገሮች እናውቃለን እና ይህ ታሪክ የማንበብ ልማዳችንንም ያዳብርልናል ብዬ አስባለው
202 views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:36:52 #አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ታሪኩ በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ነው የዚህች ሴት ባሏ ወደ ሀጅ ለመሄድ አሰበና የሚወዳት ባለቤቱ ብቻዋን ስለነበረች አይዞሽ እንዲላትና ችግር እንዳይደርስባት በቅርብ የነበረውን ወንድሙን አደራ በማለት ይሄዳል ከቀናት በኋላ አጅነብይ ነበርና ሰይጣን በዚያም በዚህም ብሎ ያልሆነ ነገር እንዲጠይቃት ይወሰውሰዋል ። እሱም ስሜቱንና የሰይጣኑን ጉትጎታ…
255 viewsedited  06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:00:47 ተቅዋ ማለት!!
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ እንድህ አለ፦

"ተቅዋ ማለት ራስህን ከማንም ሰው የተሻልኩ ነኝ ብለህ አለማየት ነው!!"
تفسير البغوي ١/٦٠
175 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:51:49 #አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ

ታሪኩ በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ነው
የዚህች ሴት ባሏ ወደ ሀጅ ለመሄድ አሰበና የሚወዳት ባለቤቱ ብቻዋን ስለነበረች አይዞሽ እንዲላትና ችግር እንዳይደርስባት በቅርብ የነበረውን ወንድሙን አደራ በማለት ይሄዳል ከቀናት በኋላ አጅነብይ ነበርና ሰይጣን በዚያም በዚህም ብሎ ያልሆነ ነገር እንዲጠይቃት ይወሰውሰዋል ። እሱም ስሜቱንና የሰይጣኑን ጉትጎታ መቋቋም አቅቶት የወንድሙን አደራ በመጣስ ያልሆነ ነገር ይጠይቃታል
ሴትዬዋ በኃይማኖቷ ጠንካራ ነበረችና «የወንድምህን አደራ አትብላ ከሌባ ጠብቅ ብትባል አንተው ሌባ ትሆናለህ?» በማለት ቁርጥ አቋሟን ስትነግረው፣ እንደማትቀመስ ስታስረዳው «ዝሙት ፈፅማለች በማለት ክብርሽን በማጉደፍ አዋርድሻለው » እያለ በማስፈራራት ቢሞክርም እሷ ግን «የፈለከውን አድርግ አላህ ምንጊዜም ከእኔ ጋር ነው»አለችው ።
የፈለገው ነገር ባለመሳካቱ ለጊዜው አፍሮ ቢመለስም ሰይጣን አቅጣጫውን ቀይሮ ላይሆንልህ ነገር ጠይቀህ ቀርቶብህ ቢሆን ይሻልህ ነበር፤ ወንድምህ ሲመጣ ልትነግርብህ ነው ፤ ያንተ ነገር አለቀለት ፤ ዋልህ ባይሆን መፍትሄውን ልንገርህ ዝሙት ስትሰራ አገኘኋዋት በልና ደብድባት ፤ ሕይወቷ እንዳይተርፍ አድርገህ በመደብደብ ከቤት አውጥተህ ሌላ ቦታ ለብልግና ሄዳ ችግር እንደደረሰባት በማስመሰል ሌላ ሰፈር ወስደህ ጣላት ሲለው ምክሩን በመተግበር እንዳለው ያደርጋል።
ከዚያም በኋላ ከቤት ወጥታ እንደባለገች በማስወራት የሐሰት ምስክር ሁለት ሰዎችን ቀጥሮ እየወጣች ታድራለች፤ ከብዙ ሰዎች ጋር ስትማግጥ አይተናታል ብለው እንዲመሰክሩ በማድረግ ወንድሙ ሲመጣ ለማሳመን ይበጀኛል ያለውን መረጃ ሁሉ ይዞ ይጠብቀዋል።

እሷም ከወደቀችበት መንደር ላይ ስታጣጥር ያየሰው ሁኔታዋ አሳዝኖት ከወደቀችበት አንስቶ እቤቱ ይወስዳታል። ስትረጋጋና ነፍሷን ስታውቅ ማንነቷ ሲጠይቋት «ባለቤቴ ሀጅ ሄዷል። ወንድሙ ግን በቤቴ ውስጥ እንደ ደበደበኝ አውቅ ነበር ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምንም ነገር አላውቅም ፤ የት ነው ያገኛችሁኝ» ስትል «ያገኘሁሽ እንዲህ አይነት ሰፈር ነው ፤ ሰዓቱም ሌሊት ስለ ነበር የአውሬ እራት እንዳትሆኚ ብዬ ነው ወደቤቴ ያመጣሁሽ» ይላታል

«እንደዚያ ከሆነ ቅርብ ቤተሰብ ከሌለሽ ባለቤትሽ ከሀጅ እስኪመጣ እዚህ ተቀመጪ ሁሉም ነገር እኛ እንረዳሽለን» አሏት። እዚያ ቤት በጥገኝነት እያለች አላህን የሚፈራ ሰው እንደ ኢማኑ ጥንካሬ ፈተና ይበዛበት ነበርና ሁለተኛ ፈተና ጠበቃት !

ይቀጥላል ......
ቻናሉን ጆይን በማለት ታሪኩን ተከታተሉ

አሁኑኑ ጆይን
https://telegram.me/tewihd
276 views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:51:55 እውን ዑመር ብኑል ኸጣብ ሴት ልጃቸውን ከነ ህይወቷ ቀብረዋልን?
~
ብዙዎቻችን በተለያየ አጋጣሚ ታላቁ ሶሐባ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ በጃሂሊያ ሴት ልጃቸውን ቀብረው እንደነበር እንደሰማን ወይም እንዳወራን እገምታለሁ። የሚያስደነግጠው ግን ዑመርን ባልሰሩት ጥፋት ስማቸውን ስናነሳው መቆየታችን ነው። መቼስ በዲናችን እውነት ያልሆነን ወሬ ማራገብ ያለውን አደጋ አናጣውም። በተለይ ደግሞ በዲን ስም በአላህ ቤት በመስጂድ ውስጥ ጥፋቱ ሲሰራ አስቡት። እርግጥ ነው ዑመር ጥፋቱን ሰርተውት ቢሆን እንኳን በጃሂሊያ ዘመን በተሰራ ጥፋት በኢስላም ተጠያቂ አይሆኑም። ይህን ቅጥፈት የፈበረኩት ሺዓዎች ግን በቀጥታ ዑመርን ሲያወግዙ ከሱኒው ዓለም ሰሚ ስላጡ እንዲህ በጀርባ ያሰርጋሉ፣ በጀርባም ይወጋሉ። በሚገርም ሁኔታም ጥረታቸው ተሳክቶ መሰረታዊ ጉዳዮችን የማያውቀው ሁሉ ይህን ቂሷ ያስተጋባል። ምንም በጃሂሊያ ዘመን ቢሆንም ዑመርን ባልተጨበጠ ወሬ መወረፍ ጥራዝ ነጠቅነት ብቻ ሳይሆን ፍረደ ገምድልነትም ነው። እስኪ ማነው ይህን ለራሱ የሚወድ? ለማስታወስ ያህል የቂሷው ጭብጥ ይህን ይመስላል።
(ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከጓደኞቻቸው ጋር ተቀምጠው ሳለ ትንሽ ከሳቁ በኋላ አለቀሱ። ምክንያቱን ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “በጃሂሊያ ጊዜ ከተምር እየጨበጥን ጣኦት እንሰራ ነበር። እናመልከውም ነበር። ከዚያ ግን እንበላው ነበር። ይህ ነው የሳቅኩበት ምክኒያት። ያስለቀሰኝ ደግሞ አንዲት ሴት ልጅ ነበረችኝ። ከነህይወቷ ልቀብራት ፈለግኩኝ። ይዣት ሄድኩና ጉድጓድ መቆፈር ያዝኩኝ። አፈሩ እየተረጨ ፂሜ ላይ ሲደርስ እሷ ከፂሜ ላይ ታራግፍልኝ ነበር። እንዲህ እየሆነች ከነህይወቷ ቀበርኳት።”)
ታሪኩ ይሄው ነው። ወደ ፍተሻ እንግባ። ኢስላምን ከሌሎች እምነቶች ብቻ ሳይሆን “ዘመናዊ” ከሚባለውም የታሪክ አዘጋገብ ልዩ የሚያደርገው ድንቅ የታሪክ መመርመሪያ መኖሩ ነው። ለመመርመር ደግሞ ናሙና ያስፈልገዋል። ናሙናው ሽንት ወይም ደም ወይም አክታ አይደለም። ናሙናው “ሰነድ” ይባላል። ጉዳዩን ሲቀባበሉ የነበሩት ሰዎች ሰንሰለት። ሰንሰለቱም፣ በሰንሰለቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ታማኝነትና ብቃትም በጥብቅ ይፈተሻል፣ ይመረመራል። ሰነድ የዲናችን ክፍል ነው። ዲናችን ከሰርጎ ገቦች የሚጠበቅበት ልዩ ማበጠሪያ ወንፊት ነውና። ለዚያም ነው ኢብኑ ሙባረክ “ሰነድ ከዲን ነው። ሰነድ ባይኖር ኖሮ ማንም ተነስቶ የፈለገውን ያወራ ነበር” ማለታቸው። ታዲያ የላይኛው ታሪክ ወደ ምርመራ ክፍል ሲገባ ከናካቴው ናሙና ማግኘት አልተቻለም። ሰነድ የለውምና። ለአቅመ ምርመራ አልደረሰም ማለት ነው። ታሪኩ በሚገርም ሁኔታ ከየትኛው የቀደምት የሱናና የሐዲስ እንዲሁም የታሪክ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም። እናስ ከየት መጣ? ዑመርን በክፉ ከሚወነጅሉት ሺዓዎች ዘንድ። ዘጋቢውም ኒዕመቱላህ አልጀዛኢሪ የተባለ የለየለት ዋሾ ራፊ - ዷ ነው፣ ሺዐ።
የታሪኩን ቅጥፈት ከሚያጋልጡ ነጥቦች ውስጥ:–
1. ታሪኩ በተጨባጭ ቅጥፈት እንደሆነ ከሚያጋልጡ ቀዳሚ ነገሮች ውስጥ አንዱ በቀደምት የሱኒዎች የሱናም ሆነ የታሪክ ድርሳናት ውስጥ ጭራሽ አለመገኘቱ ነው።
2. ዑመር ከመጀመሪያ ሚስታቸው ከዘይነብ ቢንቲ መዝዑን የወለዷቸው ልጆች እነኚህ ናቸው:– ሐፍሷ፣ ዐብዱላህ እና ዐብዱረሕማን አልክበር። (አልቢዳያ ወኒሃያን ይመልከቱ።) ከነዚህ ውስጥ ታላቋ ሐፍሷ ነች። ታዲያ ታላቋን ሐፍሷን ሳይቀብሩ እንዴት ነው ትንሿን የሚቀብሩት?
3. ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ በጃሂሊያም በኢስላምም ያገቧቸውም ሴቶች የወለዷቸውም ልጆች ስም ዝርዝር ሲተላለፍ ስለቀበሯት ህፃን ግን እንዴት አንድ እንኳን ከቤተሰባቸው ሳያወራ ይቀራል? ይህን ወሬ እውነት ቢሆን ኖሮ ከዑመር ቤተሰብም #ከቀደምት ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንትም ሳንሰማው እንዴት ብሎ ከስንት መቶ አመት በኋላ ከመጣው ከዚህ የዑመር ጠላት ሺዐ እንሰማዋለን?
4. ሴት ልጅ ከነህይወት መቅበር በዐረቦች ዘንድ የነበረ አስከፊ ባህል ቢሆንም የሁሉም ዐረቦች ባህል ግን አልነበረም። ይሄ ባህል የዑመር ጎሳ በሆኑት በኑ ዐዲይ ውስጥም የተለመደ አልነበረም። ታዲያ በየት ብሎ ነው እንዲህ ዓይነቱን ታሪክ ያለ #ጠንካራ ማስረጃ ወደ ዑመር የምናስጠጋው? እዚህ ላይ የዑመር እህት ፋጢማ የአጎቷን ልጅ ሰዒድ ብኑ ዘይድን ማግባቷን እናስታውስ። ሳትቀበር በህይወት መቆየቷ ምን ያመላክተናል?
5. ሌላ የታሪኩን ቅጥፈት ከሚጠቁሙ ነገሮች ውስጥ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ {ከነ ህይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ} (ተክዊር፡ 8) ስለሚለው የቁርአን አንቀፅ መልእክት በተጠየቁ ጊዜ እንዲህ ማለታቸው ነው፡- “ቀይስ ብኑ ዓሲም ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ዘንድ መጣና ‘እኔ በጃሂሊያ ስምንት ሴት ልጆቼን ከነ ህይወታቸው ቀብሬያለሁ’ አላቸው። እሳቸውም ‘ለእያንዳንዷ አንዳንድ ባሪያ ነፃ አውጣ’ አሉት። ‘እኔ ባለ ግመል ነኝ’ አለ። ‘እንግዲያውስ ከፈለግክ ከያንዳንዳቸው አንዳንድ ግመል መፅውት’” አሉት። (አሶሒሓህ፡ 3298 ይመልከቱ) እንግዲህ ተመልከቱ ይህን ታሪክ ያስተላፉትው ዑመር ብኑል ኸጣብ ናቸው። እሳቸው የጥፋቱ ተጋሪ ቢሆኑ ኖሮ ሊያወሩ የሚችሉበት ወሳኝና ተያያዥ ቦታ ነበር። ግን የቀይስን ሲያወሩ ስለራሳቸው ምንም አላሉም። እሳቸው የራሳቸውን ደብቀው ይሄ የሳቸው ጠላት የሆነው ሺዐ ደረሰበት ማለት የሚመስል ወሬ አይደለም።
ይታወስ ሺዐዎች በውሸት የተካኑ ፍጡሮች ናቸው።
1. ኢማሙ ሻፊዒይ እንዲህ ብለዋል፡- “ከስሜት ተከታዮች ውስጥ እንደ ራፊ - ዷ በአላህ ላይ በቅጥፈት የሚመሰክር አላየሁም።” (ኡሱሉል ኢዕቲቃድ፡ 8/2811)
2. ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፡- “ራፊ - ዳዎች ከአላህ ፍጡሮች ሁሉ የመጨረሻ ውሸታሞቹ ናቸው፡፡” (አልመናሩል ሙኒፍ፡ 52)
3. ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ብለዋል፡- “የእውቀት፣ የታሪክ፣ የዘገባና የኢስናድ ሰዎች በአንድ ድምፅ የሚስማሙበት ነገር ቢኖር ራፊ - ዳዎች ከሁሉም አንጃዎች የመጨረሻ ውሸታሞቹ መሆናቸውን ነው። ውሸት እነሱ ዘንድ ጥንታዊ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የኢስላም ሊቃውንት ራፊ - ዳዎች በውሸት ብዛት ከሌሎች ልቀው መውጣታቸውን መስክረዋል።" (መጅሙዑል ፈታዋ፡ 1/59)
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 17/2006)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
213 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 23:02:16 እንግዳን ያለ መህረም ቤት ውስጥ ጥሎ መሄድ ሁኩሙ ምንድን ነው

ሼይኽ ኢብኑ ባዝ ❬ረሂመሁላህ❭እንዲህ ተብለው ተጠየቁ

#ጥያቄ

➞▹▹ቤቴ እንግዳ መጣብኝ ይሄኔ እኔ እሱን ከቤት ያለ ማህረም ሚስቴ ብቻ ካለች ሚስት ለብቻዋ ክላስ ወይም ማድቤት ውስጥ ትቸው ወደ ውጭ ላንዳድ ጉዳይ መውጣት ይቻላልን
➞በአንድ ክላስ በቤት ለብቻቸው ወይንስ ይህ ነገር እንደ ኸልዋ ይቆጠራል በዚህ ላይ ብታብራሩልን ጀዛኩምላህ ኸይር

#መልስ

➞▹▹በጭራሽ ➷አይሆንም ብቻቸውን ➷ትተሀቸው መውጣት ➷አይቻልም ይልቁንም ➷አንተ ራስህ ➷እንግዳውጋ ትቀመጣለህ ➷አብረህ እሱጋ ➷ትሆናለህ እንዲሁም ➷ከወጣህ አብረህ ➷እንግዳውጋ ትወጣለህ ➷በቤት ውስጥ ሴቶ ➷ብቻዋን ከሆነች◃◃◌

➞▹▹ነገር ግን ➷ሴቷጋ በቤት ➷ውስጥ ሌላ ➷ሰው ካለ ➷ማህረም ካሉ ምንም ➷አደለም ነገር ግን ➷ብቻዋን ከሆነች ➷ግን እንግዳው ጋር ➷ብቻዋ መሆን ➷የለባትም◃◃◌

➞▹▹እንግዳ ➷አያስተማምንም እና ➷እንግዳውም መጥፎ ➷ሊሆን ይችላል ➷ወደ አንተ የመጣውም ➷ለዚህ ጉዳይ ➷ይሆናል ስለዚህ ➷ልትጠነቀቅ ይገባል ➷ችልተኛ መሆን ➷የለብህም◃◃◌

➞▹▹የአላህ ➷መልክተኛ ኸልዋ ብቻ ➷ለብቻቸው መተው ➷ከልክለዋል አንድ ➷ወንድ እና ➷አንዲት ሴትን ብቻ ➷ለብቻቸው ➷መተው ከልክለዋል ➷ወንድልጅ ሴትጋ ➷ብቻው አይተውም ➷ሰወስተኛው ➷ሸይጣን ነው◃◃◌

➞▹▹እንግዳውጋ ➷ብቻዋን ልትተዋት ➷አይቻልልህም ወይ ➷አብራቹሁ አንተ እና ➷እንግዳው ትወጣላቹሁ ወይ ➷አብራቹ እቤት ➷ትቀመጣላቹሁ አላህ ➷ብሎ እንግዳው ➷ወደ መጣበት ➷እስኪመለስ እስኪለቅ ➷ድረስ

➞▹▹
#ጠያቂው ➷እሱ ከሌላ ➷ክላስ ሚስትም ከሌላ ➷ክላስ◃◃◌

➞▹▹
#መልስ ➷የተለያየ ክፍልም ➷ቢሆን ይህ ➷ስህተት ነው ➷አይቻልም ሰው ➷መለለቱን እያወቀ ➷እንግዳውጋ ➷ብቻዋን ጥሎ ➷መሄድ ስህተት ➷ነው◃◃◌

ሌሎች ፈትዋዎችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
216 views20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 09:16:08 . የጂል ቀልድ አትቀልድ!
~
በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣… ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]

በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።"
አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው በምርም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 30/2010)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
322 views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ