Get Mystery Box with random crypto!

#አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ታሪኩ በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ነው የ | አስ–ሱናህ

#አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ

ታሪኩ በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ነው
የዚህች ሴት ባሏ ወደ ሀጅ ለመሄድ አሰበና የሚወዳት ባለቤቱ ብቻዋን ስለነበረች አይዞሽ እንዲላትና ችግር እንዳይደርስባት በቅርብ የነበረውን ወንድሙን አደራ በማለት ይሄዳል ከቀናት በኋላ አጅነብይ ነበርና ሰይጣን በዚያም በዚህም ብሎ ያልሆነ ነገር እንዲጠይቃት ይወሰውሰዋል ። እሱም ስሜቱንና የሰይጣኑን ጉትጎታ መቋቋም አቅቶት የወንድሙን አደራ በመጣስ ያልሆነ ነገር ይጠይቃታል
ሴትዬዋ በኃይማኖቷ ጠንካራ ነበረችና «የወንድምህን አደራ አትብላ ከሌባ ጠብቅ ብትባል አንተው ሌባ ትሆናለህ?» በማለት ቁርጥ አቋሟን ስትነግረው፣ እንደማትቀመስ ስታስረዳው «ዝሙት ፈፅማለች በማለት ክብርሽን በማጉደፍ አዋርድሻለው » እያለ በማስፈራራት ቢሞክርም እሷ ግን «የፈለከውን አድርግ አላህ ምንጊዜም ከእኔ ጋር ነው»አለችው ።
የፈለገው ነገር ባለመሳካቱ ለጊዜው አፍሮ ቢመለስም ሰይጣን አቅጣጫውን ቀይሮ ላይሆንልህ ነገር ጠይቀህ ቀርቶብህ ቢሆን ይሻልህ ነበር፤ ወንድምህ ሲመጣ ልትነግርብህ ነው ፤ ያንተ ነገር አለቀለት ፤ ዋልህ ባይሆን መፍትሄውን ልንገርህ ዝሙት ስትሰራ አገኘኋዋት በልና ደብድባት ፤ ሕይወቷ እንዳይተርፍ አድርገህ በመደብደብ ከቤት አውጥተህ ሌላ ቦታ ለብልግና ሄዳ ችግር እንደደረሰባት በማስመሰል ሌላ ሰፈር ወስደህ ጣላት ሲለው ምክሩን በመተግበር እንዳለው ያደርጋል።
ከዚያም በኋላ ከቤት ወጥታ እንደባለገች በማስወራት የሐሰት ምስክር ሁለት ሰዎችን ቀጥሮ እየወጣች ታድራለች፤ ከብዙ ሰዎች ጋር ስትማግጥ አይተናታል ብለው እንዲመሰክሩ በማድረግ ወንድሙ ሲመጣ ለማሳመን ይበጀኛል ያለውን መረጃ ሁሉ ይዞ ይጠብቀዋል።

እሷም ከወደቀችበት መንደር ላይ ስታጣጥር ያየሰው ሁኔታዋ አሳዝኖት ከወደቀችበት አንስቶ እቤቱ ይወስዳታል። ስትረጋጋና ነፍሷን ስታውቅ ማንነቷ ሲጠይቋት «ባለቤቴ ሀጅ ሄዷል። ወንድሙ ግን በቤቴ ውስጥ እንደ ደበደበኝ አውቅ ነበር ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምንም ነገር አላውቅም ፤ የት ነው ያገኛችሁኝ» ስትል «ያገኘሁሽ እንዲህ አይነት ሰፈር ነው ፤ ሰዓቱም ሌሊት ስለ ነበር የአውሬ እራት እንዳትሆኚ ብዬ ነው ወደቤቴ ያመጣሁሽ» ይላታል

«እንደዚያ ከሆነ ቅርብ ቤተሰብ ከሌለሽ ባለቤትሽ ከሀጅ እስኪመጣ እዚህ ተቀመጪ ሁሉም ነገር እኛ እንረዳሽለን» አሏት። እዚያ ቤት በጥገኝነት እያለች አላህን የሚፈራ ሰው እንደ ኢማኑ ጥንካሬ ፈተና ይበዛበት ነበርና ሁለተኛ ፈተና ጠበቃት !

ይቀጥላል ......
ቻናሉን ጆይን በማለት ታሪኩን ተከታተሉ

አሁኑኑ ጆይን
https://telegram.me/tewihd