Get Mystery Box with random crypto!

#አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ # # የመጨረሻው ክፍል ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ ቀ | አስ–ሱናህ

#አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ #
# የመጨረሻው ክፍል

ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ ቀን የአላህ ፍቃድ ሆነና ተያይዘው እሷ ዘንድ ደረሱ ። እሷም ታሪካዊ ጠላቶቿን ገና ከመድረሳቸው አውቃቸው ነበር ። እናም ሁሉንም በአንድ ላይ ግቡ አለቻቸው። እሷ ከመጋረጃ ጀርባ ስለነበረች አትታይም። ሁሉም ከገቡ ቡኋላ እንዲህ አለች «ስራውን ያጋለጠ ዱአ ይደረግለታል ። ሁላችሁም እንዲህ አይነት በሽታ ሊያጋጥማችሁ ለምን እንደቻለ ተናገሩ ችግሩን ያልተናገረ መፍትሄ አይገኝለትም ዱአም አላደርግለትም» ትላለች በዚህ ጊዜ የባለቤቷ ወንድም «እኔ ጥፋቴን በወንድሜ ፊት አልናገርም አፍራለው» ሲል ወንድሙ «ምንም አይደል ተናገር ያንተን መዳን ነው የምፈልገው» አለው አልናገርም ተናገር አልናገርም ሲባባሉ በመጨረሻ ደፍሮ « እንግዲያውስ ይቅርታ አድርግልኝ ሚስትህን ያባረርኳት እኔ ነኝ ፣ ደብድቤያታለው በህይወት ትኑር ትሙት አላውቅም ። ላንተ ትነግርብኛለች በሚል ስጋት ዝሙት እንደሰራች አስመስክሬባታለው» በማለት ራሱን አጋለጠ ። ወንድምየው ምን ያክል ሊሰማው እንደሚችል መገመት ይከብዳል።ያልጠበቀውን ነገር ሲሰማ እንደ እንጨት ደርቆ ቀረ ።ከዚያም ምስክሮቹም እንደዚሁ በሀሰት መስክሩ ብሎን ከመሰከርን ቡኋላ ነው እንዲ አይነት ችግር ያጋጠመን ብለው ራሳቸውን አጋለጡ

ሌላውም በተራው አንዲት ሴት አስፈራራለው ብሎ ህፃን ልጅ እንደገደለ ይናገራል። ሌላኛው ደግሞ ከሞት ያዳነችውን ሴት በ300 ዲናር ባሪያ ናት ብሎ የሸጠ መሆኑንና የገዛትም እንደዚሁ ባሪያዬ ናት ብሎ ሲስማት መርከቡ መገልበጡን ይናገራል ። ሁሉንም በየተራ ካናዘዘች ቡሀላ ማንነቷን ሳትነግረው ከሀጅ የመጣውን ባለቤቷን እሷ ወዳለችበት መጋረጃ እንዲገባ ትነግረዋለች ። «እኔ አጅነቢይ ጋር አልገባም ይላል» «ካልገባህ ወንድምህ አይድንም» ሲባል «የራሱ ጉዳይ አይዳን ከሀጅ ነው የመጣሁት አልገባም » ይላል እሷም ሀጅ የሄደውን ባሏን እየፈተነችው ነበር ። የባሏን ጥንካሬና ታማኝነት ካየች ቡሀላ እኔ ባለቤትህ ነኝ ስትለው በድንጋጤ ፈዞ ቀረ።

«አልሞትሽም አለሽ? ሲል» «አለሁ አልሞትኩም» አለች «አንቺ ባለቤቴ ነሽ» «አዎ ነኝ ይኸው እንደሰማከው ነው» አለች «ጥፋታቸውን እንዲያጋልጡ ያደረኩት በኔ ላይ እንዳትጠራጠር ነው ። ምን ምን እንዳሉ ሁሉንም ሰምተሀል። በኔ በኩል አላህ ስድስቱንም ሰዎች በተለያየ ችግርና መከራ አስተሳስሮ በማምጣትና በአንተ ፊት ስራቸውን እንዲያጋልጡ በማድረጉ አላህን አመሰግነዋለው። ካሁን ቡሃላ አንተ ሁሉንም መበቀል ትችላለ ፍርዱን ላንተ ትቼዋለው «ምን ይሁኑ ትላለ» ስትለው «አላህ ተበቅሏቸዋል ሁሉንም አውፍ ብየቸዋለው እና ዱአ አድርጊላቸው» ሲላት እንዲህ ስትል ዱአ አደረገች

«አላህ ሆይ ችግራቸውን አንሳላቸው ከአሁን ቡሃላ ይብቃቸው » ብላ ዱአ ስታደርግ ሁሉም ተፈወሱ ወደየመጡበት መሄድ ቻሉ ።

አላህ እሱን ለምትፈራው ሴት የሰጣት ተዐምር ነበር ።
ከታሪኩ የምንረዳው ነገር ቢኖር በድሮ ዘመን ወደ ሃጅ የሄደ ሰው ከሀጅ ቡሃላ ምን ያህል ጠንካራና ጥንቁቅ እንደሆኑና ከአጅነቢይ ጋር የነበረውን ግብግብ አይተናል ።
( ሂካይቱ ሷሊሂ ገፅ 81 ። ሸርሁል ጆርዳኒይ አርበኢነ ሀዲስ አነወዊይ ገፅ 84)

. https://t.me/tewihd/