Get Mystery Box with random crypto!

. የጂል ቀልድ አትቀልድ! ~ በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣… | አስ–ሱናህ

. የጂል ቀልድ አትቀልድ!
~
በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣… ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]

በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።"
አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው በምርም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 30/2010)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor