Get Mystery Box with random crypto!

መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ mesiwueyesus — መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mesiwueyesus — መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ
የሰርጥ አድራሻ: @mesiwueyesus
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196
የሰርጥ መግለጫ

“እርሱ አስቀድሞ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና፦ መሢሕን አግኝተናል አለው፤ ትርጓሜውም ክርስቶስ ማለት ነው።”
— ዮሐንስ 1፥42
ክርስትና ማለት ክርስቶስ ነው ክርስትያን ነኝ ካሉ መኖር ነው ክርስቶስ ለኛ ሲል ከሞተ እኛ ለሱ ስንል መኖር ነው::

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-18 13:04:53 ከዓለቱ ጋር መስማማት
።።።።።።።።።።።።።።።።
ከፍል(2)

#እርሱ_የሚከተል_ዓለት ነው:: #የሚመራው #ብሩህ #ደመና ፣ የሚከተለው ዓለት ነው:: #የሚከተል #ከኋላ ያለ ነው:: #እግዚአብሔር_ከፊት #የሚመራ ፣ #ከጀርባችን_የሚጠብቀን ፣ #ከቀኝ_ከግራ_ወዳጅ_ሁኖ #የሚከበን ነው ።

#ሕልም አይተነን ስናስፈታ ፈቺዎቹ “በጀርባዬ መጣብኝ ያልከው በጀርባ የሚመጣ ጠላት ነው #እግዚአብሔር ያውጣህ” ይሉናል ። #ጠላት_ከጀርባ #ይመጣል ። #የጀርባ_ጠላታችንን_ብቻ #ሳይሆን የጀርባ #አካላችንን #እንኳ አይተነው #አናውቅምና_ዓለቱ_ክርስቶስ #ሊከተለን ይገባል ።

እስራኤልን የሚከተል ዓለት ነበረ ። #የዓለት_ግድግዳን_የትኛውም_ጦር #አይበሳውም:: #ጦርን #ያጥፋል_እንጂ በጦር አይበሳም ። የእኛ ከለላ እንዲህ ነው ፤ ደስ ያለው አሁን በልቡ ቆሞ ፣ በሕሊናው ተንበርክኮ ፣ በነፍስ ጩኸት እልል ይበል ። ያ የሚከተለው ዓለት ሕያው ዓለት ነው ። ያ ዓለት የሚያረካ ዓለት ነው ። ያ ዓለት #በበትር_ሲመቱት #ያለ ሕጉ ምንጭ የሚያፈልቅ ነው ። #ዓለቱ_በትሩን መስበር ሲገባው በትሩ ዓለቱን እንዲሰብረው ፈቃድና ጊዜ አገኘ።


“#ጊዜ_የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ ። #ዓለት_ክርስቶስም_መስቀሉን #መስበር_ሲችል_መስቀሉ_እርሱን_ሰቅሎ #ለዓለም_አሳየው:: #ያልተሰቀለ_ነገር #አይታይምና_ሁሉ_አይቶት_እንዲድን #ተሰቀለ:: #አርማና_ሰንደቅ_ነውና ፣ #መኩሪያ_አገራችን ፣ #መመኪያ #ንጉሣችን_ሊሆን_ተሰቀለ:: #ይህን #ዓለት_ሊያምኑት ፣ ሊጠጉት ፣ ሊደበቁበት ይገባል ። ያ ሰው ግን ዓለቱ ላይ ወድቆበት ሞተ ።

በክርስቶስ #የማያመኑ_የሚሞቱት #ዓለቱ_ላይ_ስለሚፈጠፈጡ ነው:: #እርሱ_የሕይወት_ምንጭ ነው:: #ዓለት #ብርታቱ_በመስቀል_ተመትቶ_የሕይወት #ውኃ_ፈለቀልን::#ብዙ_ዘመን የተከተለን ነው ። ስንሸሸው የተከተለን እርሱ ነው ። የሚከተለው ዓለት በበረሃው ዓለም ድፍረት ነው ። እኛን የሚነካን ከዚህ ዓለት ጋር የሚጋጭ ነው ። ሥልጣን ብርታት ኃይል እስከ ዛሬ ያልረታው የዘላለም ጽናት ነው:: #የሚከተለው #ዓለት_የኋላ_አጥር #የኋላ_እሸት ነው #እርሱን #የጠበቁ እነ #አብርሃም የማታ በረከት ፣ የሠርክ መብራት አግኝተዋል ። ዓለቱን ሊድኑበት ሲገባ ወድቀውበት የሚሞቱ ብዙዎች ናቸው ። ሊለቀስላቸው ይገባል እንጂ ሊለቀስባቸው አይገባም ። በዓለት ላይ ወድቆ የሞተው ያ ሰው የሞተው ለአንድ ጉዳይ ሳይሆን ለብዙ ጉዳዮች ሞቷል ። የሚወዱትን አጥቷል ። የሚጠሉትም ሞቷልና አይጎዳንም ብለው ይቅር ብለውታል ። ሊያሙት የሚፈልጉም “ሙት አይወቀስ ፣ ድንጋይ አይነከስ” ብለው አልፈውታል::


ይቀጥላል
83 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-17 18:28:35 ከዓለቱ ጋር መስማማት
::::::::::::::::::::::::::::::::
ክፍል 1

#ወንድሟ በአደጋ የሞተባት ሴት እንዲህ ብላ የልቅሶ ሙሾ አቀረበች ይባላል፡-

“እስቲ ልነሣና ሙሾ ላውጣለት ፣ ለዚህ ለወንድሜ ለቀረው ከዓለት። የቅኔው ሰሙ ከዓለት ላይ ወድቆ መሞቱን ሲገልጥ ወርቁ ደግሞ ካለ እኅት ፣ ካለ ዘመድ ብቻውን ለቀረው ወንድም የኀዘን መግለጫ ነው ። ካለት ከዓለት ማለት ሲሆን ደግሞም ካለ እኅት ማለት ነው ። ዓለት ብንወድቅበትም ይሰብረናል ፣

#ቢወድቅብንም ይሰብረናል ። ይህ ለጌታችን ምሳሌ ሁኗል ። ማቴ. 21፡44 ። #ጌታችን_ባለማመን_ብንቃወመውም ፣ #አላውቃችሁም ቢለንም ሁለቱም ጉዳት ነው።#ዛሬ ይህን ዓለት በማያምን ልብ ብንቃወመው የወደቅነው በዓለቱ ላይ ነውና ይሰብረናል ። #ንስሐ_ካልገባን #ደግሞ_በመጨረሻ_ቀን_ዓለቱ_በፍርድ ይወድቅብናል ። #የጌታችን_የክርስቶስ ኢየሱስን ፍርድ ለየት የሚያደርገው #ምስክር_የማይጠራበት ፣ #የእምነት #የክህደት_ቃል_የማይጠየቅበት ፣ #የውሳኔ_ቀጠሮ_የማይሰጥበት ፣ #መረጃና_ማስረጃ_የማይሰበሰብበት ፣ #ይግባኝ_የማይባልበት #ዘላለማዊ #ቅጣት_ያለበት_ነው።ይህ ዓለት ለሚያምኑት የሚከተላቸውና #የሚያረካቸው_የበረሃው_ዓለት ነው ። 1ቆ. 10 ፡ 1-5 ።


#መከተሉ_አለመለየቱን_ያመለክታል #እርሱ አይለየንም ። እስከ መጨረሻው ድረስ በእኛ ተስፋ አይቆርጥም ። እርሱ ለደግነቱ ማለቂያ ፣ #ለፍለጋው_ማረፊያ #የለውም።#በመጥራቱ_የማይጸጸት ነው #በፍለጋውም_የማይደክም_ነው።እገሌ ልቡ ጠንካራ ነው እንዴት ያገኘዋል ብለን ብናስብ ለመንገዱ ፍለጋ የሌለው ነው ። የሁሉ ፈጣሪ ፣ ልብ አውቃ ነውና ማንን በምን ቋንቋ እንደሚያነጋግር ያውቅበታል ። የት ቦታ ሲመቱ አቤት እንደሚሉ ያውቃል።

(የቀጥላል)
82 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 23:03:30 ልብ በሉ እናነት የእግዚአብሔር ጽድቅ ናቸው ይህን ድንቅ መልክት ይስሙ እኛ የሆነው በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።
77 viewsedited  20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-03 13:17:48 ማንም አልተወለደም
**
ከኢየሱስ በቀር.........

ማንም ከድንግል አልተወለደም!!

ማንም ፈቅዶ አልተወለደም!!

ማንም ራሱ ተንብዮ አልተወለደም!!

ማንም ቀድሞ ኑሮ አልተወለደም!!

ማንም ንጉስ ሆኖ አልተወለደም!!

ማንም አምላክ ሆኖ አልተወለደም!!

ማንም ከሰማይ መጥቶ አልተወለደም!!

ማንም ነፍሱን ሊሰጥ አልተወለደም!!

ማንም ነፍስ ሊያድን አልተወለደም!!

ማንም የሀጥያት መስዋዕት ሊሆን አልተወለደም!!

ማንም ተፈፀመ ሊል አልተወለደም!!

ማንም ሀጥያተኛ ወዶ አልተወለደም!!

አወላለዱ ልዩ የሆነው ኢየሱስ አዳዳኑ ልዩ ነው.......የወንጌል ርዕስ ኢየሱስ ተወልዷል ሳይሆን ኢየሱስ ያድናል ነው!!

የምስራቹ ያለው መወለዱ ላይ ሳይሆን የመወለዱ ምክንያት ላይ ነው......ተወለደ ብሎ የሚቆም ወንጌል የለም.........ተወለደ ብቻውን ወንጌል አይደለም........ለምን ተወለደ?

መጽሐፍ እንደሚል

ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

ደግሞም መጽሐፍ እንደሚል.......

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

ለኢየሱስ ትልቁ ጉዳይ ሚልዮኖች የሚያከብሩለት የእርሱ ልደት ሳይሆን የአንድ ሰው ዳግም ውልደት ነው!!

የተወለደው ልደት ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ሰው ፍለጋ ነው!!

ወንጌል ስለ ልደቱ ሳይሆን ስለ ልጁ ነው!!



#ሄኖክ_አሸብር
104 views10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 13:59:06 ጸጋ…ጸጋ…ጸጋ

ጸጋ ምን አይደለም፡-

ኃጢአትን ለማድረግ ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም፡፡
በስንፍና ለመኖር ፈቃድ እሚሰጥ አይደለም፡፡
አስከፊ የሆኑ ነገሮችን ለመቀበል ፈቃድ እሚሰጥ አይደለም፡፡
ጸጋ ውለታን መርሳት አይደለም፡፡
ጸጋ እርካሽ አይደለም፡፡

ጸጋ ምንድነው፡-

ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ነገር ግን ያልተገባን፣ ያልደከምንበት፣ በራሳችን ስራ የማንሸለመው፣ የእግዚአብሔር ሞገስ/ጽድቅ/፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው፡፡
ጸጋ ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ና የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ ጸጋ ያልተሰራበት፣ያልተደከመበት ሳይሆን የተሰራበት የተደከመበት ነው፤ ነገር ግን ሰው የሰራበት፣ የደከመበት ሳይሆን እግዚአብሔር ብቻውን የሰራበት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ጸጋ የሰውን ኃጢአትና አለመቻል በእግዚአብሔር አቅርቦት መፍትሔ መስጠት ነው፡፡
ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የመቤዠት ስራ የእግዚአብሔር አቅርቦት ነው፡፡
ጸጋ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ሆኖ በምትኩ በሰጪው ምላሽ የሌለውና የማንጠየቅበት ነው፡፡

ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
158 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 22:24:32 አልዘፍንለትም መልኬን ውበቴን አይቶ ላፈቀረኝ
እኔ ምዘፍንለት መልክና ውበቱን ሳይኖረኝ ለሞተልኝ ነው

አልዘፍንለትም አደባባይ ቢወጣ ሰው ሁሉ አይኑን ለሚጥልበት መልከመልካም
እኔ ምዘፍንለት ሰው ፊቱን እስኪሰውር ድረስ ለተናቀልኝ ነው

አልዘፍንለትም ለክብሩ ለሚቆረቆርና ከኔ ይልቅ ለክብሩ ለሚሳሳ
እኔ ምዘፍንለት አምላክ ሆኖ ሳለ ክብሩን ለጣተወልኝ ነው

አልዘፍንለትም ለራሱ ለሚኖር
እኔ ምዘፍንለት ስለኔ ብሎ የሞትን ፅዋ ለጠጣልኝ ነው

አልዘፍንለትም ድንገት ባሳዝነው ፊቱን ለሚጠቁርብኝ
እኔ ምዘፍነው ሁሌ ፈገግ ብሎ ለሚያየኝና ለሚወደኝ ነው

አልዘፍንለትም የሰማንያ እና የዘጠና አመት ውለታ ለዋለልኝ
እኔ ምዘፍነው የዘላለም ውለታ ለዋለልኝ ነው።
132 views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 12:25:53 የኢየሱስ መስቀል እና ትንሳኤ
====================== ====

ዮሐንስ 11 (John)
25፤ ኢየሱስም፡— ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
26፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።

ኢየሱስ ለማርታ ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ ብሏል ዮሐ 11:25
ስለዚህ ትንሣኤ አመት ጠብቀን የምናከብረው ቀን ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ በ 1ቆሮንቶስ መልዕክት 15፡45 እና 47
ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ስሞችን ይጠቀማል .
1, #ኃለኛው_አዳም= #the_last_Adam
2, #ሁለተኛው(#አዲሱ)#ሰው= #the_second or #New_Man

ሁለቱን መጠሪያዎች በመጠቀም ትልቅ ቁም ነገር መማር እንችላለን።

ኢየሱስ ኃለኛው አዳም( the last Adam) የሚለው መጠሪያው የምድር ቆይታውን መታዘዙን፣በመስቀሉ እና በሞቱ የመጀመሪያው አዳም መጨረሻ እና በአዳም የገባው ሃጢአት እና የሀጢአት ውጤቶች ፋፃሜ ያገኙበት ማለት ሲሆን
ሁለተኛው (አዲሱ) ሰው (the New Man) የሚለው መጠሪያው በትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መገኛ ምንጭ በመሆን አዲሱ ፍጥረት ወደ ህልውና እንዲመጣ አድርጓል።

እንዲሁም በ 2 ቆሮንቶስ 5፡17 (2 Corinthians)
ስለዚህ ማንም #በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

በኢየሱስ መስቀል አሮጌው ነገር እና ለእግዚአብሔር የማይታዘዘው አመጸኛው የሕይወት ስርዓት ያለፈ እና ፍጻሜ ያገኘ ሲሆን፣
በክርስቶስ ትንሳኤ ፦በክርስቶስ የእግዚአብሔርን ሕይወት የተካፈለው አዲሱ ፍጥረት ከሕይወት ስርዓቱ ጋር ወደ ሕልውና የመጣበት ነው።

የኢየሱስ #መስቀል የአሮጌው ፍጥረት መጨረሻ ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መጀመሪያ ነው። 2ቆሮ 5፡17.

የኢየሱስ #መስቀል ከአሮጌው አዳም እና ከሙሴ ህግ ጋር ላንገናኝ በሞት የተለያየንበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር ህይወት አግኝተን የአካል ክፍሎቹ የሆንበት ነው።ሮሜ 6, ሮሜ 7፡1-4, አፌ 2፡4-, ኤፌ 5፡30 KJV.

የኢየሱስ #መስቀል ሃጥያት የተቀጣበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ፅድቃችን የተረጋገጠበት እና በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአት አልባ የሆንበት ነው።2ቆሮ 5፡21

የኢየሱስ #መስቀል እርግማን የተወገደበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ በመንፈስ እና በስጋ የተባረክንበት ነው። ገላ 3፡13 , ኤፌ 1፡4

የኢየሱስ #መስቀል በሽታ የተወገደበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ የክርስቶስ ጤና ለኛ የተቆጠረበት ነው።ኢሳ53 , 1ጴጥ 2፡24-25.

የኢየሱስ #መስቀል ከአዳም ግዛት ጊዜያዊ ከሆነ ከምድር ተስፋ ነፃ የወጣንበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ግን ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት ብቁ የሆንበት ነው። 1 ጴጥሮስ 1፡3-5፤

የኢየሱስ #መስቀል አለቅነት እና ስልጣናት የተሻሩበት ሲሆን። ቆላስይስ 2፡15
የክርስቶስ #ትንሳኤ በጠላት ሀይል ሁሉ ላይ ባለስልጣን ለመሆን ስልጣን የተቀበልንበት ነው። ማቴ 28፡18-20,ሉቃ 10፡19

የኢየሱስ #መስቀል አባት ከልጁ ከኢየሱስ ፊቱን ያዞረበት የተወው ሲሆን። መዝ 22፡1
የክርስቶስ #ትንሳኤ አባት እኛን የተቀበለበት እና አለቅህም ከቶም አልተውህም ያለበት ነው። ዕብ 13፡5

የኢየሱስ #መስቀል ኢየሱስ አምላኬ አምላኬ ብሎ የጮኅበት ሲሆን። መዝ 22፡1
የክርስቶስ #ትንሳኤ አባ አባት ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ የተቀበልንበት ነው። ሮሜ 8፡14-17
ገላ 4፡5-7
የኢየሱስ #መስቀል የዘር፣ የነገድ እና የቋንቋ ልዩነት የጠፋበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ አማኝ ሁሉ አዲስ ፍጥረት እና ሰማያዊ ዜጋ የሆንበት ነው። ራዕ 5፡10-, ፊሊ 3፡20

ኤፌሶን 1 (Ephesians)
20-21፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤

1 ጴጥሮስ 1 (1 Peter)
3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤
150 views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 21:12:34 የልጅነተችን ሙላት ከውድቀት በፍት አዳም የነበረው ማንነት (የእግዚአብሔር መልክ፣ ምሳሌ) አይደለም። በሥጋ የተገለጠውን የክርስቶስን ልዩ ውበት በንቃት ለማንጸባረቅና ክርስቶስን ለመምሰል በክርስቶስ ውስጥ የተፈጠረው አዲሱ ማንነት ከቀደመው በእጅጉ ይልቃል።
136 views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-05 16:11:52 የማይጣረስ መጽሐፍ ይዘን የሚጣረስ መልዕክት አንስበክ፤

እውነት እላችኋለሁ ዛሬም ቢሆን ጆሮ ያለው ይስማ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው የቅድስናውን ልክ መረዳት ወይም ማወቅ አለበት!!


መጽሐፍ ቅዱስ በ 1ኛ ዮሐንስ 1፥7-10 ስናገር፦ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም። ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብም ሆነ ስናስተምር፣ በትክክለኛዉ አዉድ ከፋፍለን እንዲሁም ክርስቶስ በመስቀል ሰርቶ በጨረሰዉ የጸጋ ሥራ መዝነን ካልወሰድን፣ የእኛ ባልሆነ መልዕክት፥

ክርስቶስ የሰጠንን የሕይወት ከፍታና ክብር ሳንኖረዉ እንቀራለን። ለዝያም ነዉ፣ ብዙ ጊዜ የማይጣረስ መጽሐፍ ይዘን የሚጣረስ መልዕክት የምንሰብከዉ!! የማይጋጭ ቃል ይዘን የሚጋጭ መዝሙር የምንዘምረዉ!! የማይታኮስ እዉነት ይዘን የሚታኮስ ትንቢት የምንተነብየዉ..!! #ብዙ_ሰዉ "ኃጢአት የለብንም ብንል እራሳችንን እናስታለን" የሚለዉን ጥቅስ በመጥቀስ፣ የክርስቶስ አካል የሆነችዉን፣ በክርስቶስ የጸደቀችዉንና የተቀደሰችዉን ቤተክርስትያን፣ ኃጢአተኛ ብሎ ለመጥራት ይደፍራል! ይህ ደግሞ የክርስቶስን የመስቀል ሥራ ማግፋፋትና እግዚአብሔርን መሳደብ ነዉ!

"ኃጢአት የለብንም ብንል እራሳችንን እናስታለን" የሚለዉ ጥቅስ ለአማኝ የተጻፈ ሳይሆን ላላመኑት ሰዎች የተጻፈ ነዉ!

ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። (1ኛ ዮሐ 1:2-3) ዮሐንስ ከአብ ዘንድ ስለነበረዉና ስለተገለጠዉ የህይወት ቃል ላላመኑት ሰዎች እየመሰከረ እንጂ ያመኑትን ሰዎች እያስተማረ አይደለም!

የዮሐንስ ኅብረት ከአባት ጋር፣ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነዉ! መልዕክቱ የተጻፈላቸዉ ሰዎች ደግሞ ከዮሐንስ ጋር ኅብረት የሌላቸዉ ናቸዉ! ምክንያቱም ዮሐንስ መልዕክቱም ሲጽፍ ከእኛ ጋር ኅብረት #እንዲኖራችሁ ብሎ ጽፏልና! #እንዲኖራችሁ_ከተባለ_ቀድሞዉኑ_የላቸዉም_ማለት_ነው። በዚህም ከአብ ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት የላቸዉም። ምክንያቱም ከዮሐንስ ጋር ኅብረት መፍጠር ማለት ከአብ ጋር ብሎም ከክርስቶስ ጋር ኅብረት መፍጠር ነዉና! በዚህም ሰዎቹ ያላመኑና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸዉ መሆኑን እናዉቃለን!

ዮሐንስ ላላመኑ ሰዎች ሲጽፍ ኃጢአት አለባችሁ ብሎ እንደጻፈዉ ሁሉ ያመኑ ሰዎች ኃጢአታቸዉ ለዘላለም እንደተሰረየላቸውም ጽፏል።!
ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ። (1ኛ ዮሐንስ 2:12)

ወዳጄ፣ አማኝ ኃጢአቱ የተሰረየለት ቅዱስና ነዉር አልባ እንጂ ካልማርከኝ ብሎ የሚያለቅስ ምስኪን ኀጢአተኛ አይደለም! እወዳችኋለሁ ተባረኩልኝ።
143 views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-03 20:06:28 አንድ ወዳጅ

ከመሞትህ በፊት ልትተዋወቀው የሚገባ አንድ ወዳጅ አለ። ይህ ወዳጅ አንተን መውደድ የጀመረው አንተ ከመወለድህ በፊት ነው። መኖር ሳትጀምር ያወቀህ፥ ሳታውቀው ያኖረህ፥ ሳትጠይቀው የኃጢአትህን ዕዳ የከፈለልህ፥ በነፃ ሕይወትን ሊሰጥህ እየጠበቀህ ያለ አንድ ወዳጅ ኢየሱስ!! ይህን አንድ ወዳጅ ስታውቀው ሰማይ ያውቅሃል። አንድ ኢየሱስን በመቀበል የእግዚአብሔር ስጦታዎችን ሁሉ ማለትም የኃጢአት ይቅርታ፣ ጽድቅ፣ የዘላለም ሕይወት፣ ልጅነት እና ክብር መቀበል ትችላለህ!! ኢየሱስ ይወድሃል!!

(ወንጌል ላልተመሰከረለት ለአንድ ሰው ይህን inbox ያድርጉ፦ ለብዙዎች share ያድርጉ)
134 views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ