Get Mystery Box with random crypto!

ከዓለቱ ጋር መስማማት ።።።።።።።።።።።።።።።። ከፍል(2) #እርሱ_ | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

ከዓለቱ ጋር መስማማት
።።።።።።።።።።።።።።።።
ከፍል(2)

#እርሱ_የሚከተል_ዓለት ነው:: #የሚመራው #ብሩህ #ደመና ፣ የሚከተለው ዓለት ነው:: #የሚከተል #ከኋላ ያለ ነው:: #እግዚአብሔር_ከፊት #የሚመራ ፣ #ከጀርባችን_የሚጠብቀን ፣ #ከቀኝ_ከግራ_ወዳጅ_ሁኖ #የሚከበን ነው ።

#ሕልም አይተነን ስናስፈታ ፈቺዎቹ “በጀርባዬ መጣብኝ ያልከው በጀርባ የሚመጣ ጠላት ነው #እግዚአብሔር ያውጣህ” ይሉናል ። #ጠላት_ከጀርባ #ይመጣል ። #የጀርባ_ጠላታችንን_ብቻ #ሳይሆን የጀርባ #አካላችንን #እንኳ አይተነው #አናውቅምና_ዓለቱ_ክርስቶስ #ሊከተለን ይገባል ።

እስራኤልን የሚከተል ዓለት ነበረ ። #የዓለት_ግድግዳን_የትኛውም_ጦር #አይበሳውም:: #ጦርን #ያጥፋል_እንጂ በጦር አይበሳም ። የእኛ ከለላ እንዲህ ነው ፤ ደስ ያለው አሁን በልቡ ቆሞ ፣ በሕሊናው ተንበርክኮ ፣ በነፍስ ጩኸት እልል ይበል ። ያ የሚከተለው ዓለት ሕያው ዓለት ነው ። ያ ዓለት የሚያረካ ዓለት ነው ። ያ ዓለት #በበትር_ሲመቱት #ያለ ሕጉ ምንጭ የሚያፈልቅ ነው ። #ዓለቱ_በትሩን መስበር ሲገባው በትሩ ዓለቱን እንዲሰብረው ፈቃድና ጊዜ አገኘ።


“#ጊዜ_የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” እንዲሉ ። #ዓለት_ክርስቶስም_መስቀሉን #መስበር_ሲችል_መስቀሉ_እርሱን_ሰቅሎ #ለዓለም_አሳየው:: #ያልተሰቀለ_ነገር #አይታይምና_ሁሉ_አይቶት_እንዲድን #ተሰቀለ:: #አርማና_ሰንደቅ_ነውና ፣ #መኩሪያ_አገራችን ፣ #መመኪያ #ንጉሣችን_ሊሆን_ተሰቀለ:: #ይህን #ዓለት_ሊያምኑት ፣ ሊጠጉት ፣ ሊደበቁበት ይገባል ። ያ ሰው ግን ዓለቱ ላይ ወድቆበት ሞተ ።

በክርስቶስ #የማያመኑ_የሚሞቱት #ዓለቱ_ላይ_ስለሚፈጠፈጡ ነው:: #እርሱ_የሕይወት_ምንጭ ነው:: #ዓለት #ብርታቱ_በመስቀል_ተመትቶ_የሕይወት #ውኃ_ፈለቀልን::#ብዙ_ዘመን የተከተለን ነው ። ስንሸሸው የተከተለን እርሱ ነው ። የሚከተለው ዓለት በበረሃው ዓለም ድፍረት ነው ። እኛን የሚነካን ከዚህ ዓለት ጋር የሚጋጭ ነው ። ሥልጣን ብርታት ኃይል እስከ ዛሬ ያልረታው የዘላለም ጽናት ነው:: #የሚከተለው #ዓለት_የኋላ_አጥር #የኋላ_እሸት ነው #እርሱን #የጠበቁ እነ #አብርሃም የማታ በረከት ፣ የሠርክ መብራት አግኝተዋል ። ዓለቱን ሊድኑበት ሲገባ ወድቀውበት የሚሞቱ ብዙዎች ናቸው ። ሊለቀስላቸው ይገባል እንጂ ሊለቀስባቸው አይገባም ። በዓለት ላይ ወድቆ የሞተው ያ ሰው የሞተው ለአንድ ጉዳይ ሳይሆን ለብዙ ጉዳዮች ሞቷል ። የሚወዱትን አጥቷል ። የሚጠሉትም ሞቷልና አይጎዳንም ብለው ይቅር ብለውታል ። ሊያሙት የሚፈልጉም “ሙት አይወቀስ ፣ ድንጋይ አይነከስ” ብለው አልፈውታል::


ይቀጥላል