Get Mystery Box with random crypto!

ከዓለቱ ጋር መስማማት :::::::::::::::::::::::::::::::: | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

ከዓለቱ ጋር መስማማት
::::::::::::::::::::::::::::::::
ክፍል 1

#ወንድሟ በአደጋ የሞተባት ሴት እንዲህ ብላ የልቅሶ ሙሾ አቀረበች ይባላል፡-

“እስቲ ልነሣና ሙሾ ላውጣለት ፣ ለዚህ ለወንድሜ ለቀረው ከዓለት። የቅኔው ሰሙ ከዓለት ላይ ወድቆ መሞቱን ሲገልጥ ወርቁ ደግሞ ካለ እኅት ፣ ካለ ዘመድ ብቻውን ለቀረው ወንድም የኀዘን መግለጫ ነው ። ካለት ከዓለት ማለት ሲሆን ደግሞም ካለ እኅት ማለት ነው ። ዓለት ብንወድቅበትም ይሰብረናል ፣

#ቢወድቅብንም ይሰብረናል ። ይህ ለጌታችን ምሳሌ ሁኗል ። ማቴ. 21፡44 ። #ጌታችን_ባለማመን_ብንቃወመውም ፣ #አላውቃችሁም ቢለንም ሁለቱም ጉዳት ነው።#ዛሬ ይህን ዓለት በማያምን ልብ ብንቃወመው የወደቅነው በዓለቱ ላይ ነውና ይሰብረናል ። #ንስሐ_ካልገባን #ደግሞ_በመጨረሻ_ቀን_ዓለቱ_በፍርድ ይወድቅብናል ። #የጌታችን_የክርስቶስ ኢየሱስን ፍርድ ለየት የሚያደርገው #ምስክር_የማይጠራበት ፣ #የእምነት #የክህደት_ቃል_የማይጠየቅበት ፣ #የውሳኔ_ቀጠሮ_የማይሰጥበት ፣ #መረጃና_ማስረጃ_የማይሰበሰብበት ፣ #ይግባኝ_የማይባልበት #ዘላለማዊ #ቅጣት_ያለበት_ነው።ይህ ዓለት ለሚያምኑት የሚከተላቸውና #የሚያረካቸው_የበረሃው_ዓለት ነው ። 1ቆ. 10 ፡ 1-5 ።


#መከተሉ_አለመለየቱን_ያመለክታል #እርሱ አይለየንም ። እስከ መጨረሻው ድረስ በእኛ ተስፋ አይቆርጥም ። እርሱ ለደግነቱ ማለቂያ ፣ #ለፍለጋው_ማረፊያ #የለውም።#በመጥራቱ_የማይጸጸት ነው #በፍለጋውም_የማይደክም_ነው።እገሌ ልቡ ጠንካራ ነው እንዴት ያገኘዋል ብለን ብናስብ ለመንገዱ ፍለጋ የሌለው ነው ። የሁሉ ፈጣሪ ፣ ልብ አውቃ ነውና ማንን በምን ቋንቋ እንደሚያነጋግር ያውቅበታል ። የት ቦታ ሲመቱ አቤት እንደሚሉ ያውቃል።

(የቀጥላል)