Get Mystery Box with random crypto!

ጸጋ…ጸጋ…ጸጋ ጸጋ ምን አይደለም፡- ኃጢአትን ለማድረግ ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም፡፡ በስን | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

ጸጋ…ጸጋ…ጸጋ

ጸጋ ምን አይደለም፡-

ኃጢአትን ለማድረግ ፈቃድ የሚሰጥ አይደለም፡፡
በስንፍና ለመኖር ፈቃድ እሚሰጥ አይደለም፡፡
አስከፊ የሆኑ ነገሮችን ለመቀበል ፈቃድ እሚሰጥ አይደለም፡፡
ጸጋ ውለታን መርሳት አይደለም፡፡
ጸጋ እርካሽ አይደለም፡፡

ጸጋ ምንድነው፡-

ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የሆነ ነገር ግን ያልተገባን፣ ያልደከምንበት፣ በራሳችን ስራ የማንሸለመው፣ የእግዚአብሔር ሞገስ/ጽድቅ/፣ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው፡፡
ጸጋ ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ና የእግዚአብሔር ስራ ነው፡፡ ጸጋ ያልተሰራበት፣ያልተደከመበት ሳይሆን የተሰራበት የተደከመበት ነው፤ ነገር ግን ሰው የሰራበት፣ የደከመበት ሳይሆን እግዚአብሔር ብቻውን የሰራበት ነው፡፡
የእግዚአብሔር ጸጋ የሰውን ኃጢአትና አለመቻል በእግዚአብሔር አቅርቦት መፍትሔ መስጠት ነው፡፡
ጸጋ በኢየሱስ ክርስቶስ የመቤዠት ስራ የእግዚአብሔር አቅርቦት ነው፡፡
ጸጋ በነጻ የተሰጠ ስጦታ ሆኖ በምትኩ በሰጪው ምላሽ የሌለውና የማንጠየቅበት ነው፡፡

ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤