Get Mystery Box with random crypto!

ማንም አልተወለደም ** ከኢየሱስ በቀር......... ማንም ከድንግል አልተወለደም!! ማን | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

ማንም አልተወለደም
**
ከኢየሱስ በቀር.........

ማንም ከድንግል አልተወለደም!!

ማንም ፈቅዶ አልተወለደም!!

ማንም ራሱ ተንብዮ አልተወለደም!!

ማንም ቀድሞ ኑሮ አልተወለደም!!

ማንም ንጉስ ሆኖ አልተወለደም!!

ማንም አምላክ ሆኖ አልተወለደም!!

ማንም ከሰማይ መጥቶ አልተወለደም!!

ማንም ነፍሱን ሊሰጥ አልተወለደም!!

ማንም ነፍስ ሊያድን አልተወለደም!!

ማንም የሀጥያት መስዋዕት ሊሆን አልተወለደም!!

ማንም ተፈፀመ ሊል አልተወለደም!!

ማንም ሀጥያተኛ ወዶ አልተወለደም!!

አወላለዱ ልዩ የሆነው ኢየሱስ አዳዳኑ ልዩ ነው.......የወንጌል ርዕስ ኢየሱስ ተወልዷል ሳይሆን ኢየሱስ ያድናል ነው!!

የምስራቹ ያለው መወለዱ ላይ ሳይሆን የመወለዱ ምክንያት ላይ ነው......ተወለደ ብሎ የሚቆም ወንጌል የለም.........ተወለደ ብቻውን ወንጌል አይደለም........ለምን ተወለደ?

መጽሐፍ እንደሚል

ሉቃስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
¹¹ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።

ደግሞም መጽሐፍ እንደሚል.......

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— ሮሜ 1፥3-4

ለኢየሱስ ትልቁ ጉዳይ ሚልዮኖች የሚያከብሩለት የእርሱ ልደት ሳይሆን የአንድ ሰው ዳግም ውልደት ነው!!

የተወለደው ልደት ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ሰው ፍለጋ ነው!!

ወንጌል ስለ ልደቱ ሳይሆን ስለ ልጁ ነው!!



#ሄኖክ_አሸብር