Get Mystery Box with random crypto!

አልዘፍንለትም መልኬን ውበቴን አይቶ ላፈቀረኝ እኔ ምዘፍንለት መልክና ውበቱን ሳይኖረኝ ለሞተልኝ | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

አልዘፍንለትም መልኬን ውበቴን አይቶ ላፈቀረኝ
እኔ ምዘፍንለት መልክና ውበቱን ሳይኖረኝ ለሞተልኝ ነው

አልዘፍንለትም አደባባይ ቢወጣ ሰው ሁሉ አይኑን ለሚጥልበት መልከመልካም
እኔ ምዘፍንለት ሰው ፊቱን እስኪሰውር ድረስ ለተናቀልኝ ነው

አልዘፍንለትም ለክብሩ ለሚቆረቆርና ከኔ ይልቅ ለክብሩ ለሚሳሳ
እኔ ምዘፍንለት አምላክ ሆኖ ሳለ ክብሩን ለጣተወልኝ ነው

አልዘፍንለትም ለራሱ ለሚኖር
እኔ ምዘፍንለት ስለኔ ብሎ የሞትን ፅዋ ለጠጣልኝ ነው

አልዘፍንለትም ድንገት ባሳዝነው ፊቱን ለሚጠቁርብኝ
እኔ ምዘፍነው ሁሌ ፈገግ ብሎ ለሚያየኝና ለሚወደኝ ነው

አልዘፍንለትም የሰማንያ እና የዘጠና አመት ውለታ ለዋለልኝ
እኔ ምዘፍነው የዘላለም ውለታ ለዋለልኝ ነው።