Get Mystery Box with random crypto!

የኢየሱስ መስቀል እና ትንሳኤ ====================== ==== ዮሐንስ 11 (Joh | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

የኢየሱስ መስቀል እና ትንሳኤ
====================== ====

ዮሐንስ 11 (John)
25፤ ኢየሱስም፡— ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
26፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም፤ ይህን ታምኚያለሽን? አላት።

ኢየሱስ ለማርታ ትንሣኤ እና ሕይወት እኔ ነኝ ብሏል ዮሐ 11:25
ስለዚህ ትንሣኤ አመት ጠብቀን የምናከብረው ቀን ሳይሆን ማንነት ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ በ 1ቆሮንቶስ መልዕክት 15፡45 እና 47
ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ስሞችን ይጠቀማል .
1, #ኃለኛው_አዳም= #the_last_Adam
2, #ሁለተኛው(#አዲሱ)#ሰው= #the_second or #New_Man

ሁለቱን መጠሪያዎች በመጠቀም ትልቅ ቁም ነገር መማር እንችላለን።

ኢየሱስ ኃለኛው አዳም( the last Adam) የሚለው መጠሪያው የምድር ቆይታውን መታዘዙን፣በመስቀሉ እና በሞቱ የመጀመሪያው አዳም መጨረሻ እና በአዳም የገባው ሃጢአት እና የሀጢአት ውጤቶች ፋፃሜ ያገኙበት ማለት ሲሆን
ሁለተኛው (አዲሱ) ሰው (the New Man) የሚለው መጠሪያው በትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መገኛ ምንጭ በመሆን አዲሱ ፍጥረት ወደ ህልውና እንዲመጣ አድርጓል።

እንዲሁም በ 2 ቆሮንቶስ 5፡17 (2 Corinthians)
ስለዚህ ማንም #በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

በኢየሱስ መስቀል አሮጌው ነገር እና ለእግዚአብሔር የማይታዘዘው አመጸኛው የሕይወት ስርዓት ያለፈ እና ፍጻሜ ያገኘ ሲሆን፣
በክርስቶስ ትንሳኤ ፦በክርስቶስ የእግዚአብሔርን ሕይወት የተካፈለው አዲሱ ፍጥረት ከሕይወት ስርዓቱ ጋር ወደ ሕልውና የመጣበት ነው።

የኢየሱስ #መስቀል የአሮጌው ፍጥረት መጨረሻ ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መጀመሪያ ነው። 2ቆሮ 5፡17.

የኢየሱስ #መስቀል ከአሮጌው አዳም እና ከሙሴ ህግ ጋር ላንገናኝ በሞት የተለያየንበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር ህይወት አግኝተን የአካል ክፍሎቹ የሆንበት ነው።ሮሜ 6, ሮሜ 7፡1-4, አፌ 2፡4-, ኤፌ 5፡30 KJV.

የኢየሱስ #መስቀል ሃጥያት የተቀጣበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ፅድቃችን የተረጋገጠበት እና በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአት አልባ የሆንበት ነው።2ቆሮ 5፡21

የኢየሱስ #መስቀል እርግማን የተወገደበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ በመንፈስ እና በስጋ የተባረክንበት ነው። ገላ 3፡13 , ኤፌ 1፡4

የኢየሱስ #መስቀል በሽታ የተወገደበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ የክርስቶስ ጤና ለኛ የተቆጠረበት ነው።ኢሳ53 , 1ጴጥ 2፡24-25.

የኢየሱስ #መስቀል ከአዳም ግዛት ጊዜያዊ ከሆነ ከምድር ተስፋ ነፃ የወጣንበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ ግን ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት ብቁ የሆንበት ነው። 1 ጴጥሮስ 1፡3-5፤

የኢየሱስ #መስቀል አለቅነት እና ስልጣናት የተሻሩበት ሲሆን። ቆላስይስ 2፡15
የክርስቶስ #ትንሳኤ በጠላት ሀይል ሁሉ ላይ ባለስልጣን ለመሆን ስልጣን የተቀበልንበት ነው። ማቴ 28፡18-20,ሉቃ 10፡19

የኢየሱስ #መስቀል አባት ከልጁ ከኢየሱስ ፊቱን ያዞረበት የተወው ሲሆን። መዝ 22፡1
የክርስቶስ #ትንሳኤ አባት እኛን የተቀበለበት እና አለቅህም ከቶም አልተውህም ያለበት ነው። ዕብ 13፡5

የኢየሱስ #መስቀል ኢየሱስ አምላኬ አምላኬ ብሎ የጮኅበት ሲሆን። መዝ 22፡1
የክርስቶስ #ትንሳኤ አባ አባት ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ የተቀበልንበት ነው። ሮሜ 8፡14-17
ገላ 4፡5-7
የኢየሱስ #መስቀል የዘር፣ የነገድ እና የቋንቋ ልዩነት የጠፋበት ሲሆን
የክርስቶስ #ትንሳኤ አማኝ ሁሉ አዲስ ፍጥረት እና ሰማያዊ ዜጋ የሆንበት ነው። ራዕ 5፡10-, ፊሊ 3፡20

ኤፌሶን 1 (Ephesians)
20-21፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤

1 ጴጥሮስ 1 (1 Peter)
3-5፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤