Get Mystery Box with random crypto!

የማይጣረስ መጽሐፍ ይዘን የሚጣረስ መልዕክት አንስበክ፤ እውነት እላችኋለሁ ዛሬም ቢሆን ጆሮ ያለ | መሢሑ ኢየሱስ ክርስቶስ

የማይጣረስ መጽሐፍ ይዘን የሚጣረስ መልዕክት አንስበክ፤

እውነት እላችኋለሁ ዛሬም ቢሆን ጆሮ ያለው ይስማ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ሰው የቅድስናውን ልክ መረዳት ወይም ማወቅ አለበት!!


መጽሐፍ ቅዱስ በ 1ኛ ዮሐንስ 1፥7-10 ስናገር፦ ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም። ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብም ሆነ ስናስተምር፣ በትክክለኛዉ አዉድ ከፋፍለን እንዲሁም ክርስቶስ በመስቀል ሰርቶ በጨረሰዉ የጸጋ ሥራ መዝነን ካልወሰድን፣ የእኛ ባልሆነ መልዕክት፥

ክርስቶስ የሰጠንን የሕይወት ከፍታና ክብር ሳንኖረዉ እንቀራለን። ለዝያም ነዉ፣ ብዙ ጊዜ የማይጣረስ መጽሐፍ ይዘን የሚጣረስ መልዕክት የምንሰብከዉ!! የማይጋጭ ቃል ይዘን የሚጋጭ መዝሙር የምንዘምረዉ!! የማይታኮስ እዉነት ይዘን የሚታኮስ ትንቢት የምንተነብየዉ..!! #ብዙ_ሰዉ "ኃጢአት የለብንም ብንል እራሳችንን እናስታለን" የሚለዉን ጥቅስ በመጥቀስ፣ የክርስቶስ አካል የሆነችዉን፣ በክርስቶስ የጸደቀችዉንና የተቀደሰችዉን ቤተክርስትያን፣ ኃጢአተኛ ብሎ ለመጥራት ይደፍራል! ይህ ደግሞ የክርስቶስን የመስቀል ሥራ ማግፋፋትና እግዚአብሔርን መሳደብ ነዉ!

"ኃጢአት የለብንም ብንል እራሳችንን እናስታለን" የሚለዉ ጥቅስ ለአማኝ የተጻፈ ሳይሆን ላላመኑት ሰዎች የተጻፈ ነዉ!

ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። (1ኛ ዮሐ 1:2-3) ዮሐንስ ከአብ ዘንድ ስለነበረዉና ስለተገለጠዉ የህይወት ቃል ላላመኑት ሰዎች እየመሰከረ እንጂ ያመኑትን ሰዎች እያስተማረ አይደለም!

የዮሐንስ ኅብረት ከአባት ጋር፣ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነዉ! መልዕክቱ የተጻፈላቸዉ ሰዎች ደግሞ ከዮሐንስ ጋር ኅብረት የሌላቸዉ ናቸዉ! ምክንያቱም ዮሐንስ መልዕክቱም ሲጽፍ ከእኛ ጋር ኅብረት #እንዲኖራችሁ ብሎ ጽፏልና! #እንዲኖራችሁ_ከተባለ_ቀድሞዉኑ_የላቸዉም_ማለት_ነው። በዚህም ከአብ ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት የላቸዉም። ምክንያቱም ከዮሐንስ ጋር ኅብረት መፍጠር ማለት ከአብ ጋር ብሎም ከክርስቶስ ጋር ኅብረት መፍጠር ነዉና! በዚህም ሰዎቹ ያላመኑና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸዉ መሆኑን እናዉቃለን!

ዮሐንስ ላላመኑ ሰዎች ሲጽፍ ኃጢአት አለባችሁ ብሎ እንደጻፈዉ ሁሉ ያመኑ ሰዎች ኃጢአታቸዉ ለዘላለም እንደተሰረየላቸውም ጽፏል።!
ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ። (1ኛ ዮሐንስ 2:12)

ወዳጄ፣ አማኝ ኃጢአቱ የተሰረየለት ቅዱስና ነዉር አልባ እንጂ ካልማርከኝ ብሎ የሚያለቅስ ምስኪን ኀጢአተኛ አይደለም! እወዳችኋለሁ ተባረኩልኝ።