Get Mystery Box with random crypto!

@አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW

የቴሌግራም ቻናል አርማ deposta — @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW
የቴሌግራም ቻናል አርማ deposta — @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW
የሰርጥ አድራሻ: @deposta
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 228
የሰርጥ መግለጫ

🔵ጅማ አባ ቡና ነው ⚪️
👆ABA BUNA NEW 👆
👆ስለ ቡና እናወራለን 👆
👆ስለ ቡና እንዘምራለን 👆
ወቅታዊ እና አዳዲስ መረጃዎችን በቀጥታ ከ ስታድየም ከማህበራዊ ድረገፆች ፣ ቡናን የተመለከቱ ማናቸውንም መረጃ እናቀርባለን፡፡
★ቡናን ለመደገፍ ብዙ ምክኛት አለን★★✍✍✍
Admin 👉👉 @dagmaw_minlik

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-23 17:57:54
በ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሚወርዱ ሦስት ክለቦች መካከል ሁለቱ ቀሪ ሁለት የጨዋታ ሳምንታት እየቀሩ ተለይተዋል። አዲስ አበባ ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር በ2015 ወደ ሁለተኛው የሀገሪቱ የሊግ እርከን መውረዳቸው ተረጋግጧል።

@Deposta
@Deposta
@ABBuna2005
56 viewsedited  14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:16:43 ከሁለተኛው ግብ መቆጠር በኋላ በነበሩት ደቂቃዎች አዳማ ከተማዎች የማጥቃት ኃይላቸውን ለማሻሻል አዎንታዊ ለውጦችን በማድረግ ጥረት ያደረጉ ሲሆን በአንፃሩ ፋሲሎችን እንዲሁ በተመሳሳይ ተጨማሪ ግብ ለማግኘት ጥረቶችን ቢያደርጉም ትኩረት የሚስቡ ሙከራዎችን ሳንመለከት ጨዋታውን ፍፃሜውን አግኝቷል።
ፋሲል ከነማዎች ድል ማድረጋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን ወደ 55 በማሳደግ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበራቸውን የሦስት ነጥብ ልዩነት ሲያስቀጥሉ በአንፃሩ ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገዱት አዳማ ከተማዎች ደግሞ በ30 ነጥብ አሁንም 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
84 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:16:32 ከግቧ መቆጠር በኋላ አሁን ሳይጣደፉ ጥቃቶችን መሰንዘራቸውን የቀጠሉት ፋሲሎች በተለይ በረከት ደስታ ከተሰለፈበት የግራ መስመር መነሻቸውን ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈፀማቸውን የቀጠሉ ቢሆንም አጋጣሚዎቹን ወደ ግብነት መቀየር ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። ግብ ካስተናገዱ ወዲህ በተወሰነ መልኩ ወደ ፊት ገፍተው ይጫወታሉ ተብለው የጠበቁት አዳማ ከተማዎች በ71ኛው ደቂቃ ከቆመ ኳስ መነሻውን ባደረገ ማጥቃት አዲስ ተስፋዬ ከቀኝ መስመር የሳጥን ጠርዝ ወደ ውስጥ ያሻማውን ኳስ ደስታ ዮሐንስ በግንባሩ ገጭቶ ሳማኬ ካዳነበት አጋጣሚ ውጪ ተጠቃሽ ሙከራዎችን ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል። በፋሲል በኩል ግን ወደ ኢትዮጵያ ዳግም ከተመለሰ የመጀመሪያ ግቡን በጨዋታው ያገኘው ሙጂብ ቃሲም በ78ኛው ደቂቃ አምሳሉ ጥላሁን ወደ ቀኝ ካደላ አቋቋም ከቆመ ኳስ ያሻማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት የቡድኑን መሪነት ማሳደግ ችሏል።
74 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:16:22 ምንም እንኳን ፋሲሎች በአጋማሹ ዕድሎችን ለመፍጠር ሙከራዎችን ሲያደርጉ የተመለከትን ቢሆንም አዳማዎች ግን በቁጥር በርከት ብለው ለመከላከል ሲያደርጉት የነበረው ጥረት እና ትጋት የሚደነቅ ነበር። በአጋማሹ በፋሲሎች በኩል የተሻለ የሚባሉት ሁለት ተከታታይ ሙከራዎች የተደረጉት በ42ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። በቅድሚያ አምሳሉ ጥላሁን ወደ ቀኝ ካደላ አቋቋም ካሻማው የቆመ ኳስ ያሬድ ባየህ ያደረገው ሙከራ በሳኩቡ ካማራ ሲድንበት ከተመለሰው ኳስ በረከት ደስታ ያሻማውን ኳስ አስቻለው ታመነ በግንባሩ ገጭቶ ያደረገው ሙከራ ለጥቂት ከግቡ አናት በላይ ወጥታበታለች።
ከዕረፍት መልስም በተመሳሳይ ይዘት በቀጠለው ጨዋታ 56ኛው ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛቸው ከመሀል ሜዳ አካባቢ ያሳለፈተለትን ድንቅ ኳስ ከተከላካዮች አፈትልኮ የወጣው ሙጂብ ቃሲም በመጀመሪያ ንክኪ ተንሸራቶ በማስቆጠር ውጥረት ውስጥ የነበሩትን የክለቡ ደጋፊዎች ወደ ተለየ የደስታ ስሜት ውስጥ መክተት የቻለችን ግብ አስቆጥሯል።
66 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:16:14 ሪፖርት | ሙጂብ ቃሲም ዐፄዎቹን በዋንጫ ፉክክር አቆይቷል
June 20, 2022 by soccerethiopia21
ሪፖርት | ሙጂብ ቃሲም ዐፄዎቹን በዋንጫ ፉክክር አቆይቷል
በዕለቱ የመጀመሪያ በነበረው ጨዋታ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ ወዲህ ከግብ ርቆ የሰነበተው ሙጂብ ቃሲም ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ፋሲል ከነማ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለውን ልዩነት አስጠብቆ እንዲቀጥል አስችሏል።
አዳማ ከተማዎች ባለፈው የጨዋታ ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና ከተረታው ስብስብ ባደረጓቸው ለውጦች ፀጋአብ ዮሴፍ እና ቅጣት ያለበት ቶማስ ስምረቱን በዮሴፍ ዮሐንስ እና እዮብ ማቲዎስን ተክተው ያስገቡ ሲሆን በአንፃሩ ሰበታ ከተማን አሸንፈው የመጡት ፋሲል ከነማዎች ደግሞ ከድር ኩሊባሊ ፣ በዛብህ መለዮ እና ጉዳት ያገኘው ኦኪኪ አፎላቢን አስወጥተው በምትካቸው አስቻለው ታመነ ፣ ሱራፌል ዳኛቸው እና በረከት ደስታን ተክተው በማስገባት የዛሬውን ጨዋታ አድርገዋል።
እጅግ ቀዝቃዛ አጀማመር ባስመለከተን የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአመዛኙ አዳማ ከተማዎች ከኳስ ጀርባ በጥንቃቄ ለመከላከል ጥረት ያደረጉበት እንዲሁም ፋሲል ከተማዎች ደግሞ ይህን የአዳማን የመከላከል ውቅር ለመስበር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የተመለከትንበት ነበር። ፋሲሎች በርከት ያሉ የኳስ ቅብብሎችን በማድረግ ወደ ተጋጣሚ ሳጥን ለመድረስ ተደጋጋሚ ጥረቶችን ያደረጉ ሲሆን በዚህም በተለይ በቀኝ መስመር በኩል የነበራቸው አፈፃፀም በንፅፅር የተሻለ ሆኖ ተመልክተናል።
በ9ኛው እና 14ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር ከተሻማ ኳስ በረከት ደስታ ሁለት አጋጣሚዎችን ቢያገኝም ኳሶቹን መጠቀም ሳይችል የቀረ ሲሆን ከዚህ ውጪ በአንድ አጋጣሚ ሱራፌል ዳኛቸው ከሳጥን ውጪ ካደረገው ሙከራ ሌላ በአዳማ የሜዳ አጋማሽ እንዳሳለፉት ደቂቃ ፋሲሎች በቂ ዕድሎችን መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።
54 views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 12:14:15
ፋሲል ከነማ ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ በ2022/23 የካፍ የክለቦች ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ሊጉ ሲጠናቀቅ ቻምፒዮን የሚሆነው ክለብ የቻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ይዞ የሚያጠናቅቀው ደግሞ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናል።

@Deposta
@Deposta
@ABBuna2005
45 viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 21:14:31 የቀጠለ

''ከኳሰ እና ከትምህርት አንዱን ምረጥ'' ዳዋ ሆቴሳ

'ከኳስ እና ከትምህርት አንዱን ምረጥ' ተብሎ ያደገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሆቴሳ

በልጅነቱ እረኛ ነበር። የወላጆቹን ከብቶች ያግዳል። ተማሪም ነበር። ይሁን እንጂ ፍቅሩ ከኳስ ጋር ነበር። በሰፈራቸው በሚገኘው ሜዳ፣ አልያም በወላጆቹ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከኳስ ጋር ስሯሯጥ ነው ያደጉት ይላል፤ የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሆጤሳ።

ወላጆቹ እግር ኳስ አብዝቶ መጫወቱን አልወደዱትም ነበር። የወላጆቹ ፍላጎት ልጃቸው ትኩረቱ ትምህርት ላይ እንዲሆን ነበር። የኳስ ፍቅሩ ከልክ ያለፈባቸው ወላጆች ልጃቸው በብዙ መንገድ ቀጥተዋል። ቅጣቶቹ ግን ዳዋን ኳስ ይዞ ከመሯሯጥ አላገዱትም።

በመጨረሻም 'ከትምህርት እና ከኳስ አንዱን ምረጥ!' ተባለ። ዳዋ ሳያቅማማ ምርጫውን አስታወቀ። ኳስን መረጠ።

እግር ኳስ እየተጫወት የፍቅር አጋሩን አገኘ። በኳስም ሕይወቱ ሰምሯል። ለአገር ተሰልፏል። በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ አገሩን ወክሎ ግብ አስቆጠረ።

ዳዋ ስለልጅነት ጊዜው፣ እድገቱ እና ስለ የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ ተናግሯል።

@ABBuna2005
@ABBuna2005
@Deposta
@Deposta
84 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:03:45 በቤተሰቡ ከትምህርት ወይም ከእግርኳስ ምረጥ የተባለው ዳዋ ሁቴሳ የእግርኳስ ህይወቱን ለቢቢሲ በዚህ መልኩ አካፍሏል!

በልጅነቱ እረኛ ነበር የወላጆቹን ከብቶች ያግዳል ተማሪም ነበር ይሁን እንጂ ፍቅሩ ከኳስ ጋር ነበር በሰፈራቸው በሚገኘው ሜዳ፣ አልያም በወላጆቹ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከኳስ ጋር ስሯሯጥ ነው ያደጉት ይላል፤ የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሁቴሳ።

ወላጆቹ እግር ኳስ አብዝቶ መጫወቱን አልወደዱትም ነበር የወላጆቹ ፍላጎት ልጃቸው ትኩረቱ ትምህርት ላይ እንዲሆን ነበር የኳስ ፍቅሩ ከልክ ያለፈባቸው ወላጆች ልጃቸው በብዙ መንገድ ቀጥተዋል ቅጣቶቹ ግን ዳዋን ኳስ ይዞ ከመሯሯጥ አላገዱትም።

በመጨረሻም 'ከትምህርት እና ከኳስ አንዱን ምረጥ!' ተባለ ዳዋ ሳያቅማማ ምርጫውን አስታወቀ ኳስን መረጠ።

እግር ኳስ እየተጫወት የፍቅር አጋሩን አገኘ በኳስም ሕይወቱ ሰምሯል ለአገር ተሰልፏል በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ አገሩን ወክሎ ግብ አስቆጠረ።

ተወልጄ ካደግኩባት ከተማ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ የወጣ ያለ አይመስለኝም አላውቅም።

ከዲኤስቲቪ (እግር ኳስ ለመከታተል ከሳተላይት ቴሌቪዥን) አልርቅም ነበር ኳስ ለማሳየት ገንዘብ ይጠይቁ ነበር በልጅነት ጊዜ ደግሞ ገንዘብ ማግኘት ቀላል አልነበረም።

እኔ እግር ኳስ ብወድም ቤተሰቦቼ ግን ኳስ እንድጫወት አይፈቅዱልኝም ነበር በኳስ ምክንያት ብዙ ቅጣት ደርሶብኛል ከብቶቹን ትቼ ወደ ኳስ ሜዳ ሄጄ ኳስ እጫወት ነበር በዚህም ምክንያት በተለይ አባቴ በተኛሁበት ይመታኝ ነበር።

ወላጆቼ ኳስ አትጫወትም ብለው ሲከለክሉኝ ምግብ አልበላም እያልኩ አስቸግር ነበር 9ኛ ክፍል እስክደርስ በዚህ ሁኔታ ቆይቻለሁ።

ቀስ በቀስ ለትምህርት ቤት መጫወት ጀመርኩ 'ልምድ ያግኝ' እያሉኝ ወደ ነገሌ ቦረና ይዘውኝ ይሄዱ ነበር።

በወቅቱ ነገሌ ክለቡ በኦሮሚያ ሊግ ውስጥ ይጫወት ነበር ለነገሌ ስጨዋት የመጀመሪያው ክፍያዬ 300 ብር ነበር።

የልጆች አባት

የሕይወት አጋሬ ኳስ እና አትሌቲክስ ትወዳለች ግን እሷ በትምህርት ገፍታበታለች በልጅነት ነው የተጋባነው ብዙ ዓመት በፍቅር ቆይተናል ከስድስት ዓመት በፊት ነው የተጋባነው አሁን ሁለት ልጆች አሉን።

ኑሮዬ በአዳማ ከተማ ነው አዳማ ላይ ቤት ገዝቻለሁ።

ዳዋ ማለት ሰው መንካት የማይችለው ትልቅ ደን ማለት ነው ሁጤሳ ማለት ደግሞ እኩለ ለሊት ላይ የተወለደ ሰው ማለት ነው።

ወደ ትውልድ ከተማዬ ስሄድ በተለያዩ ፕሮጀክቶች መካከል ውድድር በማካሄድ ታዳጊዎች እንዲበረታቱ ጥረት አደርጋለሁ በቅርቡ ግን በአካባቢው የጸጥታ ችግር ስላለ ሄጄ አላውቅም።

ፕሪሚዬር ሊጉን ከተቀላቅልኩ 7ኛ ዓመቴ ነው በእነዚህ ዓመታት፤

ናሽናል ሲሚንት (ድሬ ዳዋ)
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ለሁለት ዓመት
አዳማ- ለአራት ዓመት
ሃዲያ ሆሳዕና - አንድ ዓመት

አዳማ - አሁን ዳግም ተመልሼ እየተጫወትኩ ነው በጣም ተደስቻለሁ

የአፍሪካ ዋንጫ ማለት ትልቅ ውድድር ነው በትልቅ ውድድር ላይ ተሰልፌ ጎል ማስቆጠሬ በጣም ነው ያስደሰተኝ።

በሁለት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፌ ተጫውቻለሁ በዚህ ውድድር ላይ የሴኔጋሉን ሳዲዮ ማኔን እና ለአርሰናል የሚጫወተውን ጋናዊውን ቶማስ ፓርቴን አግኝቻለሁ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሚጎለው ነገር የለም ግን እንደ ተጫዋች ብዙ መስራት ያለብን ነገር አለ ለምሳሌ በቴክኒክ እንጂ በሰውነት ብቃት ከእነሱ ጋር አንወዳደርም።

እንደ አትሌቶቻችን ብዙ የስኬት ደረጃ ላይ መድረስ አለመቻላችን ያበሳጨኛል እንደ አንድ ግለሰብ ያሳዝነኛል ለዚህ አገር ብዙ ማድረግ እፈልጋለሁ።

@Deposta
@ABBuna2005
83 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:36:39
"በሐገር ውስጥም ሆነ በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤ ብሔራዊ ቡድናችን ባስመዘገበው ውጤት የጂማ አባ ቡና ስፖርት ክለብ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳንም ደስ አለን!" Jimma aba buna Sport Club - Team Page

@Deposta
@Deposta
@ABBuna2005
85 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 08:07:17
ኢድ ሙባረክ | Eid Mubarak

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ በድጋሚ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!!

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የመረዳዳት እንዲሁም የመተዛዘን እንዲሆንላችሁ በቴሌግራም ቻናላችን በጅማ አባ ቡና ስፓርት ክለብ ስም ተመኘን።

#EID_MUBARAK

አባ ቡና ነዉ

@Deposta
@ABBuna2005
140 viewsedited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ