Get Mystery Box with random crypto!

በቤተሰቡ ከትምህርት ወይም ከእግርኳስ ምረጥ የተባለው ዳዋ ሁቴሳ የእግርኳስ ህይወቱን ለቢቢሲ በዚህ | @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW

በቤተሰቡ ከትምህርት ወይም ከእግርኳስ ምረጥ የተባለው ዳዋ ሁቴሳ የእግርኳስ ህይወቱን ለቢቢሲ በዚህ መልኩ አካፍሏል!

በልጅነቱ እረኛ ነበር የወላጆቹን ከብቶች ያግዳል ተማሪም ነበር ይሁን እንጂ ፍቅሩ ከኳስ ጋር ነበር በሰፈራቸው በሚገኘው ሜዳ፣ አልያም በወላጆቹ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከኳስ ጋር ስሯሯጥ ነው ያደጉት ይላል፤ የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሁቴሳ።

ወላጆቹ እግር ኳስ አብዝቶ መጫወቱን አልወደዱትም ነበር የወላጆቹ ፍላጎት ልጃቸው ትኩረቱ ትምህርት ላይ እንዲሆን ነበር የኳስ ፍቅሩ ከልክ ያለፈባቸው ወላጆች ልጃቸው በብዙ መንገድ ቀጥተዋል ቅጣቶቹ ግን ዳዋን ኳስ ይዞ ከመሯሯጥ አላገዱትም።

በመጨረሻም 'ከትምህርት እና ከኳስ አንዱን ምረጥ!' ተባለ ዳዋ ሳያቅማማ ምርጫውን አስታወቀ ኳስን መረጠ።

እግር ኳስ እየተጫወት የፍቅር አጋሩን አገኘ በኳስም ሕይወቱ ሰምሯል ለአገር ተሰልፏል በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ አገሩን ወክሎ ግብ አስቆጠረ።

ተወልጄ ካደግኩባት ከተማ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ የወጣ ያለ አይመስለኝም አላውቅም።

ከዲኤስቲቪ (እግር ኳስ ለመከታተል ከሳተላይት ቴሌቪዥን) አልርቅም ነበር ኳስ ለማሳየት ገንዘብ ይጠይቁ ነበር በልጅነት ጊዜ ደግሞ ገንዘብ ማግኘት ቀላል አልነበረም።

እኔ እግር ኳስ ብወድም ቤተሰቦቼ ግን ኳስ እንድጫወት አይፈቅዱልኝም ነበር በኳስ ምክንያት ብዙ ቅጣት ደርሶብኛል ከብቶቹን ትቼ ወደ ኳስ ሜዳ ሄጄ ኳስ እጫወት ነበር በዚህም ምክንያት በተለይ አባቴ በተኛሁበት ይመታኝ ነበር።

ወላጆቼ ኳስ አትጫወትም ብለው ሲከለክሉኝ ምግብ አልበላም እያልኩ አስቸግር ነበር 9ኛ ክፍል እስክደርስ በዚህ ሁኔታ ቆይቻለሁ።

ቀስ በቀስ ለትምህርት ቤት መጫወት ጀመርኩ 'ልምድ ያግኝ' እያሉኝ ወደ ነገሌ ቦረና ይዘውኝ ይሄዱ ነበር።

በወቅቱ ነገሌ ክለቡ በኦሮሚያ ሊግ ውስጥ ይጫወት ነበር ለነገሌ ስጨዋት የመጀመሪያው ክፍያዬ 300 ብር ነበር።

የልጆች አባት

የሕይወት አጋሬ ኳስ እና አትሌቲክስ ትወዳለች ግን እሷ በትምህርት ገፍታበታለች በልጅነት ነው የተጋባነው ብዙ ዓመት በፍቅር ቆይተናል ከስድስት ዓመት በፊት ነው የተጋባነው አሁን ሁለት ልጆች አሉን።

ኑሮዬ በአዳማ ከተማ ነው አዳማ ላይ ቤት ገዝቻለሁ።

ዳዋ ማለት ሰው መንካት የማይችለው ትልቅ ደን ማለት ነው ሁጤሳ ማለት ደግሞ እኩለ ለሊት ላይ የተወለደ ሰው ማለት ነው።

ወደ ትውልድ ከተማዬ ስሄድ በተለያዩ ፕሮጀክቶች መካከል ውድድር በማካሄድ ታዳጊዎች እንዲበረታቱ ጥረት አደርጋለሁ በቅርቡ ግን በአካባቢው የጸጥታ ችግር ስላለ ሄጄ አላውቅም።

ፕሪሚዬር ሊጉን ከተቀላቅልኩ 7ኛ ዓመቴ ነው በእነዚህ ዓመታት፤

ናሽናል ሲሚንት (ድሬ ዳዋ)
ቅዱስ ጊዮርጊስ - ለሁለት ዓመት
አዳማ- ለአራት ዓመት
ሃዲያ ሆሳዕና - አንድ ዓመት

አዳማ - አሁን ዳግም ተመልሼ እየተጫወትኩ ነው በጣም ተደስቻለሁ

የአፍሪካ ዋንጫ ማለት ትልቅ ውድድር ነው በትልቅ ውድድር ላይ ተሰልፌ ጎል ማስቆጠሬ በጣም ነው ያስደሰተኝ።

በሁለት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፌ ተጫውቻለሁ በዚህ ውድድር ላይ የሴኔጋሉን ሳዲዮ ማኔን እና ለአርሰናል የሚጫወተውን ጋናዊውን ቶማስ ፓርቴን አግኝቻለሁ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የሚጎለው ነገር የለም ግን እንደ ተጫዋች ብዙ መስራት ያለብን ነገር አለ ለምሳሌ በቴክኒክ እንጂ በሰውነት ብቃት ከእነሱ ጋር አንወዳደርም።

እንደ አትሌቶቻችን ብዙ የስኬት ደረጃ ላይ መድረስ አለመቻላችን ያበሳጨኛል እንደ አንድ ግለሰብ ያሳዝነኛል ለዚህ አገር ብዙ ማድረግ እፈልጋለሁ።

@Deposta
@ABBuna2005