Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ ''ከኳሰ እና ከትምህርት አንዱን ምረጥ'' ዳዋ ሆቴሳ 'ከኳስ እና ከትምህርት አንዱን | @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW

የቀጠለ

''ከኳሰ እና ከትምህርት አንዱን ምረጥ'' ዳዋ ሆቴሳ

'ከኳስ እና ከትምህርት አንዱን ምረጥ' ተብሎ ያደገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሆቴሳ

በልጅነቱ እረኛ ነበር። የወላጆቹን ከብቶች ያግዳል። ተማሪም ነበር። ይሁን እንጂ ፍቅሩ ከኳስ ጋር ነበር። በሰፈራቸው በሚገኘው ሜዳ፣ አልያም በወላጆቹ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከኳስ ጋር ስሯሯጥ ነው ያደጉት ይላል፤ የዛሬው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ዳዋ ሆጤሳ።

ወላጆቹ እግር ኳስ አብዝቶ መጫወቱን አልወደዱትም ነበር። የወላጆቹ ፍላጎት ልጃቸው ትኩረቱ ትምህርት ላይ እንዲሆን ነበር። የኳስ ፍቅሩ ከልክ ያለፈባቸው ወላጆች ልጃቸው በብዙ መንገድ ቀጥተዋል። ቅጣቶቹ ግን ዳዋን ኳስ ይዞ ከመሯሯጥ አላገዱትም።

በመጨረሻም 'ከትምህርት እና ከኳስ አንዱን ምረጥ!' ተባለ። ዳዋ ሳያቅማማ ምርጫውን አስታወቀ። ኳስን መረጠ።

እግር ኳስ እየተጫወት የፍቅር አጋሩን አገኘ። በኳስም ሕይወቱ ሰምሯል። ለአገር ተሰልፏል። በአፍሪካ ዋንጫ መድረክ አገሩን ወክሎ ግብ አስቆጠረ።

ዳዋ ስለልጅነት ጊዜው፣ እድገቱ እና ስለ የእግር ኳስ ሕይወቱ ለቢቢሲ ተናግሯል።

@ABBuna2005
@ABBuna2005
@Deposta
@Deposta