Get Mystery Box with random crypto!

ከግቧ መቆጠር በኋላ አሁን ሳይጣደፉ ጥቃቶችን መሰንዘራቸውን የቀጠሉት ፋሲሎች በተለይ በረከት ደስታ | @አባ ቡና ነው 🎤🎤 @ABA BUNA NEW

ከግቧ መቆጠር በኋላ አሁን ሳይጣደፉ ጥቃቶችን መሰንዘራቸውን የቀጠሉት ፋሲሎች በተለይ በረከት ደስታ ከተሰለፈበት የግራ መስመር መነሻቸውን ያደረጉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈፀማቸውን የቀጠሉ ቢሆንም አጋጣሚዎቹን ወደ ግብነት መቀየር ግን ሳይችሉ ቀርተዋል። ግብ ካስተናገዱ ወዲህ በተወሰነ መልኩ ወደ ፊት ገፍተው ይጫወታሉ ተብለው የጠበቁት አዳማ ከተማዎች በ71ኛው ደቂቃ ከቆመ ኳስ መነሻውን ባደረገ ማጥቃት አዲስ ተስፋዬ ከቀኝ መስመር የሳጥን ጠርዝ ወደ ውስጥ ያሻማውን ኳስ ደስታ ዮሐንስ በግንባሩ ገጭቶ ሳማኬ ካዳነበት አጋጣሚ ውጪ ተጠቃሽ ሙከራዎችን ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል። በፋሲል በኩል ግን ወደ ኢትዮጵያ ዳግም ከተመለሰ የመጀመሪያ ግቡን በጨዋታው ያገኘው ሙጂብ ቃሲም በ78ኛው ደቂቃ አምሳሉ ጥላሁን ወደ ቀኝ ካደላ አቋቋም ከቆመ ኳስ ያሻማውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት የቡድኑን መሪነት ማሳደግ ችሏል።