Get Mystery Box with random crypto!

ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @dania_islamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.81K
የሰርጥ መግለጫ

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን 3:104
T.me/Dania_Islamic
Comment👉 @Daniya_islamic_bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-03-10 18:15:39 ወዳጆች ሁሉ ለዚህ ታላቅ የረመዷን ወር ፆም እንኳን አደረሳችሁ ። ነገ ሰኞ የመጀመሪያ የፆም ቀናችን ይሆናል ። ዛሬ ተራዊሕ ይጀመራል ። መልካሙን ሁሉ ይወፍቀን።
ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
5.7K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-23 09:50:22 #አወይ_ፍቅር...

ለመልዕክተኛውም ለሰሐቦችም ከባድ የነበረው ዘመቻ ላይ የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ለመከላከል ወደሳቸው የገሰገሰው ጠልሓ ነበር። እሳቸውን በመከላከል ከጎናቸው ጦርነትን መካፈልን የተጠማው ጠልሓ ኡሁድ ላይ ጀግንነቱን አሳየ! በሙሉ አካሉ መልዕክተኛውን ይከላከል ነበር። ሐቢበላህ ﷺ በተጣሩ ቁጥር ቶሎ የሚመልሰውና ካጠገባቸው የማይጠፋው ጠልሓ ነበር። መልዕክተኛውም ﷺ እንዲህ በማለት ስለ አፍቃሪያቸው ይናገራሉ:

"لقد رأيتُني يومَ أُحُدٍ ، و ما في الأرضِ قُرْبِي مخلوقٌ ، غيرُ جبريلَ عن يميني ، وطلحةَ عن يَسَاري"

"የኡሁድ ወቅት እራሴን ተመለከትኩት ማንም ለኔ ቅርብ አልነበረም። በቀኜ ከነበረው ሰይዲና ጂብሪልና በግራዬ ከነበረው ጠልሓ በስተቀር።" ብለው ነበር ...

ጠልሓ ወደሚወዳቸው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሚወረወሩትን እያንዳንዱን ቀስቶች በአንድ እጁ እየተከላከለ በአንድ እጁ ደግሞ በሰይፍ ይዋጋ ነበር። አስባቹታል? ህልም ይመስላል አይደል? ... አሁን ላለነው እኛ ፊልም የሚመስሉ ትዕይንቶችን መስማት እንግዳ ነው አይደል?

...የመልዕክተኛው አፍቃሪ ጠልሓ ቁስል ቁስል ላይ ተደራረበበት። እስከሚችለው አቅም ሐቢቢን ﷺ ተከላከለላቸው። የቆሰሉትን ሸፊዒ በቆሰለው ጀርባው ላይ ተሸክሞ ተጓዘ! እሳቸውን ማትረፍ ላይ ቁዋው መጣለት። ሙሉ ሰውነቱ ቁስል ብቻ የሆነው ጠልሓ የአለሙ መድህን የሆኑትን ውዱ ነብዩን ﷺ የነበሩበት ሁናቴ ዳግም ሩህ ዘራበት፤ እግሮቹ ተንቀሳቀሱለት። ተሸክሟቸውም ወደ ተራራው ወጣ! ይህንን ክስተት ከሩቅ የተመለከቱት አቡበክር አስሲዲቅ እና አቡ ኡበይዳ ኢብን አል ጀራህ መልዕክተኛው ﷺ እና ጠልሓ ወዳሉበት ገሰገሱ!

ወደ ረሱል ﷺ ሲጠጉ ግን እሳቸው በደከመው አንደበት ወደ ጠልሓ እየጠቆሙ "እኔን ትታቹ ጓድ'ኣቹ ጋር ሂዱ!" አሏቸው። አባበክርም እንዲህ ይላሉ: "ጠልሓ'ን ስናየው ሙሉ ሰውነቱ ቁስል በቁስል ነበር። ከእያንዳንዱ ሰውነቱ ደም ይፈስ ነበር! ከቀስት፣ ከድንጋይ፣ ከጦር፣ ከጎራዴ ብዙ ቁስሎች አርፈውበት ነበር። እራሱንም ስቶ ከአፉም ደም እየተፋ ነበር።" ይላሉ አባበክር። ግን በህይወት ተርፎ ነበር። መልዕክተኛውም ﷺ በአፅዕኖት: "ጀነት ጠልሓ ላይ ዛሬ ወጅቦበታል!" አሉ። ... አወይ ፍቅር! መሐባ የማያደርገው የለም! የረሱለላህ ባልደረቦች የነበራቸው መስዋትዕነትና ፍቅር ደግሞ አይገለፅም!

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይዲና ሙሐመድ!

ረሱሊ'ኮﷺ! ፍቅርዎ ሁሌም አዲስ ነው
Nadia

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
7.9K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-16 15:42:04
ከምንወደዉ ጋር ፣ የተወደደ ስፍራ ላይ

አላህ ይወፍቀን!
ጁምዐኩም ሙባረክ!

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
7.4K views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 20:52:30
ፈገግም እያላቹህ

የስረኛው ፖስት ፀሃፊ ኢዲ ኮሄን ይባላል።የፅዮናዊያኑ ሰራዊት ቃል አቀባይ ነው።እንዲህ ሲል ፃፈ:-
"አሏሁ (ሱ.ወ) በቁርአን እስረኛዎቻቹን በክብር ያዙ ሲል አዞ ነበር።ፍልስጤማዊያኑ ታጣቂዎች ግን አንገላቱብን " ይላል።

ዳርፉር ሙሐመድ ለኮሄን ምላሽ ሰጠ:-
"እንዴት ነህ ኢዲ..
ዛሬ አንድ ምት ቢያርፍብህ የቁርአን አያ ትዝ አለህ?ሌላ ምት ቢጨመርማ ከሰሒሀል-ቡኻሪና ሙስነድ ኢማም አሕመድ ሐዲስ ትነግረን ነበር "
ibra

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
14.5K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 22:58:32
"እድሜ ዘመናችንን በውርደት አቀርቅረን ከመኖር ለአንድ ቀንም ቢሆን ቀና ብለን በጀግንነት መሞትን መርጠናል"

አንድ ፍልስጤማዊ ስለጦርነቱ የተናገረው

Mahi Mahisho

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
11.2K viewsedited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 09:33:28
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅኡን

ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስ ወደ አኼራ ሄዷል

በአፍሪካ ቲቪ እና በሌሎች ኢስላማዊ ሚዲያዎች በኢስላሚክ አካዳሚካል ትምህርት ቤቶች በመምህርነት በርካታ ዲናዊ ስራዎችን ያበረከተው ኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስ ባጋጠመው ህመም ለህክምና ወደ ቱርክ ተጉዞ ህክምናውን እየተከታተለ የነበረ ሲሆን የአላህ ውሳኔ ሆኖ ወደማይወረው አኼራ ተሻግሯል:: ስርዓተ ቀብሩም በቱርክ ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶበት የሚፈፀም ይሆናል::

በገንዘብ እና በዱዓ እገዛ ላደረጋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ስራችሁን ይቀበላችሁ::

ለኡስታዝ ማህሙድ ዩኑስም አላህ ምህረቱን እንዲለግሰው፣ ማረፊያውን ጀነተል ፊርዶስ እንዲያደርግለት አላህን እንማፀነዋለን::

ለቤተሰቦቹ እና ለመላው ሙስሊም አላህ መፅናናቱን ይወፍቅ

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
15.4K viewsedited  06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 22:54:43
ማሻአላህ!

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
11.4K viewsedited  19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-30 08:38:03 እናቴ ጋ ብዙ ሚስጥር አለን። የሆነ ቀን ማታም እንዲሁ ሚስጥር ነገርኳት። የሆነች የወደድኳት ልጅ አለች። ቱርካዊ ናት። ትወደኛለች እወዳታለሁ። ለመጋባትም አስበናል። ግን እናቴ ይህን ጉዳይ ለማንም አትንገሪ አልኳት።

እሷም "ሚስጢርህ ጥልቅ ጉድጓድ ዉስጥ እንደተቀበረ አስበው አብሽር።" አለችኝ።

ጠዋት ላይ ለቁርስ እንደተቀመጥን አባቴ ወደኔ እያየ "እ ጎረምሳወ ሱልጣን ኦግሎ እንዴት አደርክ!" አለኝ።

እናንተስ እንዴት አደራችሁ!
አባት ጋ ሳይደርስ እናት ጋ የሚቀር ሚስጥር የለም ልላችሁ ፈልጌ ነው ልጆች።
ABX

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
13.8K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-26 10:36:38 إِنَّ الْحَسَنَاتِ يُذْهِبْنَ السَّيِّئَاتِ

«መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወገድዳሉና»
[ሱረቱ ሁድ: 114]

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
13.9K viewsedited  07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-11 15:16:41 አንዱ ለማኝ አንዱን ሰዉዬ "ስጠኝ" ብሎ ለመነው አሉ።
ሰዉየዉም "አላህ ይስጥልኝ" አለው።
መቸስ ከአላህ በላይ የሚሰጥ የለም፣ ከሱ ስጦታ የሚበልጥም የለም አይደል።
ለማኙ ግን "አንተ ለኔ ስጠኝ አላህ ላንተ ይስጥህ።" አለው አሉ።

አለመተማመናችን እዚህ ደረጃ ደርሷል።
ለአገራችን ሰላምን ለምኑ።

ጁምዓ ሙባረክ!!
ABX

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
17.1K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ