Get Mystery Box with random crypto!

ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @dania_islamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.81K
የሰርጥ መግለጫ

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን 3:104
T.me/Dania_Islamic
Comment👉 @Daniya_islamic_bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-08-25 18:22:24
ለይለቱል ጁሙዓህ

የአላህን ቸርነትና እዝነት ተመልከቱማ
ያለድካም ጀነት የምንገባባቸዉ ብዙ ሰበቦችን ነዉ ያዘጋጀልን ከነዛም መካከል ሰለዋት አንዱ ነዉ ።

በረሱላችንﷺ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ብናደርግ ከአላህ አስር ይመለስልናል የአንዱን ዋጋም አላህ እንጂ ማንም አያዉቀዉም።

ገንዘብም ሆነ ልጆች በማይጠቅሙበት በዛ በጭንቅ ቀን የረሱላችንን ሸፍዓ የምናገኝ ያድርገን
አሚን

ሰላቱላህ ሰላሙላህ ዓለይከ ያረሱለሏህ
#ሶሉ ዓለል ሀቢብ #ኸሚስ!
Abas

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
5.8K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:57:15
አምላካችን አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ

ورحمتي وسعت كل شيء " ..

" እዝነቴ ሁሉን ነገር ሰፋች ...." ይለናል።

እዝነቱ ሲበዛ ሰፊ ነው።
የቱን ያህል ብታጠፉም አትፍሩ፣ አትሸበሩ፣
በእዝነቱ ዉስጥ አልካተትም፣ ችሮታውም አይደርሠኝም፣ ምህረቱም አይጎበኘኝም፣ ይቅርታውም አይተርፈኝም ብላችሁ አትስጉ።

ላ ወላሂ!
በፍጹም ስጋት አይግባችሁ። ..
እዝነቱ ይደርሰናል፣ ችሮታው ያካብበናል፣ ይቅርታውም ይተርፈናል፣
ኢንሻአላህ!!

ሰባሐል ኸይር!
ABX

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
5.1K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:00:36 የተሰጠህን ካወቅከው ያጣሀውን ትረሳለህ

የታመመው……ጤናዬን ባገኝ

የደሀየው ………ገንዘብ ቢኖረኝ

ባለሀብቱ……… ስልጣን ብይዝ

ደካማው………አቅም ቢኖረኝ ሲል ስንት መልካም ስራን አሳለፈ !!

ያልተሰጠንን ነገር ስንቆጥር በተሰጠን ትልቅ ነገር አላህን አመስግነን ምርጥ ባርያዎቹ ውስጥ የመግባትን ዕድል አሳጣን፡፡

አላህ ሆይ !
ውለታህኔ አስታውሰው ከሚያመሰግኑህ ባሮችህ መድበን ። #ሰበሀል_ኸይር!
umer yasin

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
5.9K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 08:12:27
የምታዩት ደስ የሚል ቀደምት የቱርክ ሃገር ልማድ ነው:‐
መስጂድ ውስጥ፣ በመንገድ ላይ፣ በቤት ውስጥ ወይም በማንኛውም ቦታ የተፈቃሪው [ﷺ] ስም ሲጠራ እጃቸውን ልባቸው ላይ ይለጥፋሉ።
ይህንን የሚያደርጉበት የሚደንቅ ምክንያት አላቸው።…
የነቢዩ [ﷺ] ሥም ሲጠራ የሙእሚን ቀልብ ከቦታው ተነስቶ በናፍቆት ክንፍ ሊበር ይደርሳል። ስለዚህ ሰውየው እጁን በልቡ ላይ አድርጎ ያረጋጋዋል። በተናፋቂው ሐውዳቸው ላይ እስከሚያገኛቸው ድረስ እንዲታገስ ያባብለዋል!
ዐጂብ ነው!…
:
በኑሩ ምድር፣ ከጀነቱ ጨፌ፣ በሸፊዓችን [ﷺ] አቅራቢያ ያላችሁ ሰዎች ታድላችኋልና በዚያራችሁ ላይ አስታውሱን። ምርጣችንን ሰልሙልን!
አላሁመ ሰሊ ወሰልም ወባሪክ ዐላ ሰይዲና ሙሀመድ!
Tofik Bahiru

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
9.3K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:23:34
#ጁምዐ_ሙባረክ!
ሱረቱል ኻህፍ + ሰለዋት + ዚክር አትርሱ!

Join our page! #ሼር

JOIN @EthioIslamic_tweets
12.6K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 07:55:20
#ከጁምዓ ስነ ስርአት ውስጥ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِذا قُلْتَ لِصاحِبِكَ يَومَ الجُمُعَةِ: أنْصِتْ، والإِمامُ يَخْطُبُ، فقَدْ لَغَوْتَ﴾

“በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጎደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርክ።”
#𝐉𝐮𝐦𝐦𝐚_𝐌𝐮𝐛𝐚𝐫𝐚𝐤
ቡኻሪ ዘግበውታል: 934

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
9.9K viewsedited  04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 17:44:16
ዛሬ ጠዋት በድንገት ነበር የፅዮናዊቷ እስራኤል ወታደሮች መኖርያ ቤቱን የከበቡት። እርሱ ግን በቀላሉ እጅ አልሰጠም። በያዘው መሳርያ ብቻውን ይፋለማቸው ጀመር። የቻለውን ያህል እየተኮሰ የአላህን ጠላቶችን በአቅሙ ረፈረፈ።

አሁን ግን አልቻለም ሰውነቱ በጥይት ተመቶ በርከት ያለ ደም ይፈሰው ይዟል። ሰውነቱ ተበሳስቶ መሬት ላይ ወድቋል። እንደምንም የእጅ ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ እንዲህ ሲል ተናገረ:-

"እናንተ የፍልስጤም ወጣቶች ሆይ! መሳርያችሁን አጥብቃችሁ ታጠቁ። ስለ ቁድስ ጥላችሁ ውደቁ። እኔ እናቴንና የተከበረው መስጂድ ያረፈበትን ውድ ሀገሬን እወዳለሁ። አሁን ግን ጌታዬን እየተገናኘሁ ነው አዎ በእርግጥም ሸሂድ ሆኛለሁ.... " ንግግሩ ተቋረጠ። ነፍሱ ወደ ጌታው በረረች። አዎ በእርግጥም እሱ ኢብራሂም ናቡልሲ ይሰኛል። ጀግና የፍልስጤም ወጣት ነው የአላህን ጠላቶች ያብረከረከ። ሙጃሂድ ነው ስለ ቁድስ ነፍሱን የሰጠ። አዎ እርሱ በእርግጥም ፍልስጤማዊ ወንድ ነው። አላህ ይቀበለው።

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
10.2K viewsedited  14:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 10:44:49
ያ ረቢ ፍልስጤምን!

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
9.4K views07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 07:18:04 በዒድ ቀን የሚደርጉ ሱናዎች

በዒድ ሌሊት ዱዓ አድርጉ

ወደ ሶላት ከመሄዳችሁ በፊት ሰውነታችሁን ታጠቡ

በደንብ ያማረ ንጹህ ልብስ ልበሱ እና እራስዎን አስውቡ

ከኢድ አል አድሃ ሶላት በፊት ምንም ነገር አለመብላት ይመከራል

ተክቢራ ይበሉ

የኢድ ሶላትን ክፍት ቦታ ላይ አድርጉ

ዱአ በማድረግ ሰላምታ ተሰጣጡ (ተቀባበል አሏሁመኒ ወሚንኩ) አሏህ ከእኛም ከናንተም (በጎ ስራዎቻችንን) ይቀበለን።

ወደ ሶላት በአንድ መንገድ ይሂዱ በሌላ መንገድ ይመለሱ

አቅም ካላችሁ (ኡድሂያ) መደረግ አለበት

መልካም እና የደስታ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። የዒድን ቀን በማህበረሰባችን ውስጥ ያሉ ደካሞች እና ችግረኞች በመንከባከብ ኡድሂያችንን በማውጣት እና የአሏህን ትዕዛዝ እና የውዱ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በመጠበቅ እናክብር።

#ኢደል_አድሀ_ሙባረክ

@Dania_Islamic || ዳኒያ ሰኢስላማዊ ቻናል
5.1K viewsedited  04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:58:51
እንኳን ለ1443 የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም ዐደረሰን

#መልካም_ዒድ

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
4.4K viewsedited  03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ