Get Mystery Box with random crypto!

ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ dania_islamic — ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @dania_islamic
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 17.81K
የሰርጥ መግለጫ

« ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ ፣ ...»
ቁርኣን 3:104
T.me/Dania_Islamic
Comment👉 @Daniya_islamic_bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-30 15:47:02 እናቴ መርፌ ውስጥ ክር እንዳስገባላት ጠራችኝ።
በዚሁ ቅፅበት የአንድ ሰው ምክር ትዝ አለኝ ፦

«እናትህ መርፌ ውስጥ ክር እንድታስገባላት ከጠየቀችህ ተቀብለህ ወዲያውኑ አታስገባው። ይልቁንም ያረጀችና እድሜዋ የገፋ እንዳይመስላትና ቀልቧ እንዳይሰበር አውቀህ ታግለህ ታግለህ አስገባው» ብሎ መክሮኝ ነበር ።

እኔም ማስገባቱ ቀላል እንዳልሆነ እየነገርኳት ጥቂት ደቂቃዎችን ታገልኩ ። በድንገት አንድ ጥፊ ፊቴ ላይ አረፈ

«ድሮውንም እውር ያደረገህ ይሄ ሞባይልና ፌስቡክ ነው»


@muslims_couple || ፍቅር ሰባኪ TemUd
3.2K views( የአዚዛ ልጅ ), 12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 19:37:45
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
353 viewsNeba promotion, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 23:43:35
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
243 viewsNeba promotion, 20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 23:16:48
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
436 viewsNeba promotion, 20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 00:17:22
ባለ ትዳር ነሽ ወይስ ገና አላገባህም
ወይስ መንገድ ላይ

ስለ ፍቅር እና ትዳር በጣፋጭ ትረካዎች እያዋዛ የሚያቀርብ ፍቅር የሆነ ቻናል ይዘን ብቅ አልን!

JOIN በማለት ብቻ ቤተብ ይሁኑ!
613 viewsNeba promotion, 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 12:36:26 አዕራቢዎቹ ተጣሉና:
አንደኛው: ‐ «በአንድ ጥፊ መዲና እንዳላደርስህ!» ብሎ ዛተ።
ሌላኛው ምናለ?: ‐ «አንድ ጥፊ ጨምርልኛ። ባንተ እጅ አላህ ሐጅ ፅፎልኝ ይሆናል!»
:
ፀባቸው ራሱ ደስ ሲል!
Tofik Bahru

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
1.5K views( የአዚዛ ልጅ ), 09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-26 09:01:55 አስቂኝ ክስተት ፈገግ በሉበት
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
የመን ውስጥ ዘማር የተባለ ቦታ ላይ አንድ መስጂድ ውስጥ የተከሰተ በጣም አስቂኝ ክስተት ነው አንብበው ሳይጨርሱ በሳቅ ሟቋረጥ ግን አይቻልም¡
||
ይህ ክስተት እዚያው መስጂዱ ውስጥ ሶ'ፈል አወል (የመጀመሪያው ሰፍ) ላይ ቆሞ ሲሰግድ የነበረ አንድ ሰጋጅ ነው የሚያስተላልፍልን...
*
እናም ይህ ሰው እንዲህ ይለናል:-
«አንድ ሰው ይሞትና ተሰግዶበት ተቀበረ ከዚያም ከኢሻ ሶላት በኋላ ነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ሊመልሱት ይዘውት ወደ መስጂድ ሲመጡ ሰአት ሄዶ ስለነበር መስጂዱ ተዘግቷል።

ስለዚህ ኻዲሞች ለፈጅር ሶላት ሲመጡ እንዲያነሱት በሚል ጀናዛ መሸከሚያው ከመስጂዱ በር ከደረጃ ላይ ያስቀምጡታል።
:
ነገር ግን ሌሊት 9:30 ሰአት አካባቢ አንድ ሰውዬ ወደ መስጂድ ሲመጣ መስጂዱ ዝግ ሆኖ እና በረንዳው ተከፍቶ አገኘው የተወሰነ ቢጠብቅም መስጂዱን የሚከፍተው አጣ ብርዱ በጣም ሲበረታበት ዞር ብሎ ሲያይ ጀናዛ መሸከሚያው ከአጠገቡ አገኘ በውስጡም ብርድልብስ ነገር አለ።
:
እና ይህ ሰው አገኘሁ ብሎ ጀናዛ መሸከሚያው ውስጥ ብርድ-ልብሱን ለብሶ ለጥ ብሎ እንቅልፉን ተኛ አባቴ! በብርድ ደንዝዞ የነበረው ሰውነቱ ትንሽ ምቾት ሲያገኝ ነፍሱንም አያውቅ ለጥ ብሎ ተኝቶልሀል...
ሃሃሃ!

ትንሽ እንደቆየ የመስጂዱ ኻዲም መጥቶ መሲጂዱ ሊከፍት ሲል በረንዳ ላይ ከነእሹ (ጀናዛ መሸከሚያው) ላይ የተኛ ሰውዬ ይመለከታል ከፈጅር በኋላ ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ መሰለው...
:
ከኋላውም ሌሎች ሰዎች መጥቶ ግማሹ ሽንት ቤት ሌላው ውዱእ ሊያደርግ ይሄዳሉ ይህ በረንዳ ላይ ተኝቶ የሚያዩት ሰውዬ (ጀናዛ) ደግሞ ሁሉም ቀድመውኝ የመጡ ሰዎች ሊሰገድበት ያመጡት ጀናዛ ነው ብሎ ያስባል በውስጡ...
(ያዝ እንግዲህ¡)

በዚያ ላይ ፈጅር ነው ሰው ከእንቅልፉ ተነስቶ እየመጣ ነው ያለው ገና በደንብ ያልነቃ ህዝብ ነው።

ሊሰገድበት የመጣ ጀናዛ ይሆናል በማለት ተጋግዘው ወደ መስጂድ ኢማሙ ጋር ወደ ሚህራብ አስገቡት።
ሃሃ!
:
ብ ር ድ የቀጠቀጠው ሰውዬ ሲሸከሙት አያውቅ ተኝቷል¡ ህእ! ሰዎቹም የማን ይሁን ብለው አይጠይቁ ገና ከእንቅልፋቸው በደንብ አልነቁም እና ተሸክመው መስጂድ ውስጥ አስገቡት።

ፈጅር አዛን ብሎ ለመስገድ ወደ 50 የሚሆኑ ሰዎች ተሰበሰቡ።

ይህንን ታሪክ የሚያስተላልፍልን ሰው እኔም ከሰጋጆቹ አንዱ ነኝ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ነበርኩ ይላል።

ከፈርድ በኋላ ልንሰግድበት ጀናዛው ከፊት ተደርጎ የፈጅር ሶላት እየሰገድን ነው።
እህእ!
:
ልክ ለሁለተኛው ረከአ ስንነሳ ጂናዛው ሲንቀሳቀስ አየሁ እንዴዴዴ አይኔ ነው ወይስ ምንድ ነው¿ ብዬ አይኔን አበስኩ ጨፍኜም ገለጥኩ መንቀሳቀሱን ግን አልተወም በቃ እንቅልፍ አለቀቀኝም ይሆናል ብዬ አሰብኩ።

ነገር ግን ነእሹ በደንብ መንቀሳቀስ ጀመረ ያኔ መረባበሽና መፍራት ጀመርኩ።

ይህ የተኛው ሰውዬ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ድንገት አንገቱ አውጥቶ ሰገዳችሁ? ብሎ ጠየቀ።
:
ያኔ! ሁሉም ሰጋጆች ደንግጦ መተረማመስና መሮጥ ጀመሩ እኔም አጠገቤ ከነበረው በር ወጥቼ በባዶ እግሬ ሮጥኩኝ ወደ 1 ኪ.ሜ ያክል የሚርቀውን ቤቴን በትንሽ ደቂቃዎች ደረስኩ ደግሞ ባዶ እግሬ መሆኔም የማውቀው ነገር የለም።
ኢማሙ (አሰጋጁም) ሲያየው ደንግጦ መሬት ላይ ይወድቋል ሌሎች ሰዎች ግማሹ ከግድግዳ ጋር ይጋጫል ሌላው ደግሞ ልክ እንደኔው በባዶ እግሩ ይሮጣል መስጂድ ውስጥ አንድ ሰው አልቀረም።
:
አሁንም ሌላኛው በጣጣጣም የሚያስቀው ክስተት ተከሰተ

ያ ከሬሳ መሸከሚያ(ከነእሹ) ላይ ተኝቶ የነበረው ሰውዬ ሲነሳ ሰዎች ሲሸሹ ሲሮጡ ሲያይ ከኋላቸው ተከትሎ መሮጥ ጀመረ።
እናንተ ምን ሆናችሁ ነው ? ቂያማ ቆሞ ነው እንዴ? እያለ ከኋላ ኋላቸው መሮጥ ጀመረ።
ሃሃሃ!
:
ሰዎቹ ደግሞ ወደ ኋላቸው ሲዞሩ ይህ ሰውዬ እየተከተላቸው መሆኑ ያያሉ ያኔ ይብስባቸዋል ባለ በሌለ ሀይላቸው ይሮጣሉ።
በዚህ መልኩ ሁሉም ሰላታቸውን አቋርጠው ሮጡ...»
ይለናል ቦታው ላይ የነበረ አንዱ ሰጋጅ።

@Dania_Islamic || ዳኒያ ኢስላማዊ ቻናል
672 views( የአዚዛ ልጅ ), 06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-25 17:52:50 ባልዬው ሽንኩርት የምትልጥ ሚስቱን ለማሽኮርመም ማድ ቤት ውስጥ ገብቶ
«የኔ ፍቅር አደራ እጅሽን እንዳትቆርጪ» አላት። ምን ብትለው ጥሩ ነው
«ነብዩ ዩሱፍ የገቡ አስመሰልከው እኮ»
Mohammed Ahmed

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
614 views( የአዚዛ ልጅ ), 14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-22 10:18:46 ዘመድ አዝማድ ጓደኛና ሚዜ የጫጉላ ምሽታቸውን ያጣጥሙ ዘንድ ቤት አስገብተዋቸው ተበታትነዋል። በመልካም ስነምግባሩ በፈሪሀ አላህነቱ የሚታወቀው ባል ሚስቱን ከጎኑ አቁሞ ሁለት ረከዓ አሰገደና ጭንቅላቷን ይዞ ዱዐ አደረገ። ሚስት ቬሎዋን አወለቀችና የመኝታ ልብሷን ቀይራ ከአልጋው ጫፍ ተቀመጠች። ጭንቅላቷን ወደ መሬት አቀርቅራለች። ፊቷን ሐዘን አጥሎታል። የደቀቀ ሰውነቷ ሐሳብ ያከሳት መሆኑ ያስታውቃል።

አጠገቧ አንገቷን አቅፎ ተቀመጠ። ምን እንደሚጠይቃት ግራ ገብቶኝ ፈጠጠ። በዝምታዋ መሃል እንባዋ ቁልቁል ፈሰሰ። "አይቤን ሰትርልኝ ከሌላ ወንድ አርግዣለሁ" ትላለች በቁጭትና በሀዘን እያለቀሰች። ድንግጥ አለ። በተቀመጠበት ደረቀ። የእሱም እንባ የሚወርድበትን ሰበብ እየጠበቀ ይመስል ኩልል ብሎ ተንደረደረ። አዘነ።

ከቤት ወጥቶ ግቢ ውስጥ ወዳለች አንዲት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ተኮርምቶ የቀኝና ግራ እጁን በመዳፉ ላይ አላትሞ፣ በአውራ ጣቶቹ ድጋፍ አገጩን አሳርፎ ሽቅብ ወደ ላይ አንጋጦ ተቀመጠ፡፡ ዓይኖቹ በጨለማው መሀል የሰማዩን ሰማያት ሰነጣጥቀው ከአላህ ፊት ዱለውታል። አዕምሮው ህመሙንና የልብ ስብራቱን በውስጥ ምላሱ ለአላህ ያንበለብላል፡፡ ጌታዬ ሆይ ሰትራት ይላል በአንደበቱ።

ሁሉንም ለአላህ ሰጥቶ አይቧን ሊሸፍንላት ወሰነ። በፍቅር እየተንከባከባት ከሰው እይታ እንድትገለል አደረጋት። እርግዝናው ዘጠኝ ወሩን ደፍኖ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ ተወለደ። የመግሪብ አዛን እየተሰማ ነበር። የተወለደውን ልጅ በበቂ ሁኔታ እንድታጠባው ካደረገ በኋላ በካርቶን አድርጎ ወደ መስጂድ ይዞት አመራ። ሰጋጆች ወደ መስጂድ መግባታቸውን ከተመለከተ በኋላ ሰው እንዳላየው ሲያረጋግጥ ልጁን መስጂድ በር ላይ ጥሎ ወደ ውስጥ ዘለቀ። ሰዎች ሰላታቸውን ጨርሰው ሲወጡ መስጂድ በር ላይ በተጣለው ህፃን ግራ ተጋብተው የማን ነው? እያሉ ይጮሃሉ።

ያመለጠውን ሁለት ረከአ ሰግዶ ሲወጣ ሰዎች በህፃኑ ዙርያ መሰብሰባቸውን ተመለከተ። ልጅ እንደሚፈልግ ሰው እየተንሰፈሰፈ አቀፈው
"ፍቀዱልኝና እንደ ልጄ ተንከባክቤ ላሳድገው" አለ ልጁን ከነካርቶኑ አቅፎ ወደ ቤት ጉዞ እየጀመረ። ለእናቱ ሰጣትና "ልጅሽን ያለስጋት አሳድጊ አይብሽ ተሸፍኗል አብሽሪ" አላት። ባሏን ከእቅፏ አስገብታ እየሳመችው እንባዋ ከአይኖቿ ኩልል ብለው ፈሰሱ።

ምንጭ
عجائب وغرائب حول العالم
Mahi Mahisho

@Muslimss_couplee || ፍቅር ሰባኪ TemUd
1.3K views( የአዚዛ ልጅ ), 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-19 22:36:10
የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

ረሱል ( ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም )
በስንት አመታቸው ነበር ወደ አኼራ የሄዱት ?
ሀ , 51
ለ , 60
ሐ, 63
መ, 40
ረ ,መልስ የለም
365 viewsNeba promotion, 19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ