Get Mystery Box with random crypto!

የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

የቴሌግራም ቻናል አርማ bosub — የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
የቴሌግራም ቻናል አርማ bosub — የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
የሰርጥ አድራሻ: @bosub
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 287
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ በቦ/ክ/ከ/ዐ/ሕ/ጽ/ቤት የሕ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት ቻናል ስለ ተለያዩ ሀገሮች ሕጎች(በተለይም ስለ ኢትዮጵያ ሕጎች)ማብራሪያ የሚሰጥበት፣አዳዲስ ሕጎች share የሚደረጉበት፣ወቅቱን ያገናዘቡ ዜናዎችም ሆነ መረጃዎች የሚተላለፉበት፣በዳይሬክቶሬቱ ስር የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫዎች፣የሕግ መልዕክቶች፣በራሪ ጽሑፎች እና የመሳሰሉት ወደ እናንተ ተደራሽ የሚደረጉበት ነው።
መልካም ቆይታ!

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-22 10:31:36 ሰላም ለእርስዎ ይሁን!
እርስዎ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በመጠቆም የዜግነት ግዴታዎትን ከመወጣት ባለፈ ጠቀም ያለ ማበረታቻ ሊያገኙ እንደሚችሉ ያውቃሉ? ይከተሉኝማ!
በሀገራችን የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ በህገ-መንግስቱ በአንቀጽ 40 ንዑስ አንቀጽ 3 እንደሰፈረው የህዝብና የመንግስት ሀብት ሲሆን መሸጥ ወይም መለወጥ እንደማይቻል ተደንግጎ ሳለ በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ ግን ሕገ-ወጥ የመሬት ይዞታና ግንባታ፣ እና የመሬት ወረራን ጨምሮ መሬት ነክ የሌብነትና የማጭበርበር ወንጀል ተስፋፍቶ ይገኛል።
በመሆኑም በከተማዋ እየተስፋፋ የመጣውን ህገ-ወጥነት ለማስቆምና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በህዝብ ተሳትፎ ወንጀሉን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር መከናወን እንዳለበት በመታመኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሕገ-ወጥነትን ለሚጠቁሙ መረጃ አቅራቢዎች ስለሚሰጥ ማበረታቻ የሚደነግግ ደንብ ቁጥር 121/2013 አውጥቷል።
በቀደመው ልጥፋችን የጥቆማ አቀራረብ ስነ-ስርአቱን በአጭሩ አጋርተንዎት እንደነበር ይታወቃል። ለዛሬም ከዚህ ደንብ ላይ 3 ጥቆማ የሚቀርብባቸውን ሕገ-ወጥ ድርጊቶችና የሚያስገኙትን ማበረታቻ እናጋራዎታለን፤ ሌሎቹን በቀጣይ ልጥፎቻችንን የምንመለስባቸው ይሆናል።
ማንኛውም ሰው፥-
1. ወደ መሬት ባንክ ቢገባም ባይገባም አግባብ ያለው አካል ሳይፈቅድ ማንኛውም የከተማ መሬት መያዙን ወይም መወረሩን ከጠቆመ በተጠቆመው ይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
2. አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ በህጋዊነት ከተያዘ ይዞታ ጎን፣ (ከፊት ለፊቱ ወይም ከበስተ-ሗላው) ያለ የከተማ ቦታ ተስፋፍቶ መከለሉን፣ ጥቅም ላይ መዋሉን፣ መታጠሩን ወይም ከአዋሳኝ ይዞታ ጋር መቀላቀሉን ከጠቆመ ከተስፋፋው ይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
3. በአካባቢ ልማት ፕላን መሰረት ለመንገድ አውታር፣ ለማህበራዊ ተቋማት፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ስፍራዎች፣ ለፓርክ፣ ለመንግስት ይዞታዎች እና ለተለያዩ አገልግሎቶች ተለይተው የተቀመጡ ባዶ ቦታዎች በህገ-ወጥ መንገድ መያዛቸውን ከጠቆመ ከተያዘው የይዞታ ልኬት ስፋት ልክ በወቅቱ የሊዝ መነሻ ዋጋ 10 (አስር) በመቶ ማበረታቻ ያገኛል፤
ሰኔ 15 2014 ኣ.ም
114 viewsfasika aggena, 07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 11:36:54 ሰላም!
በከተማችን አዲስ አበባ ተንሰራፍቶ የሚገኘው ሕገ-ወጥነት ያሳስብዎታል? እንደነዋሪ አንድ ነገር ማድረግ ብችል ብለው ይመኛሉ?
እነሆ የከተማ አስተዳደሩ ሕገ-ወጥነትን ለሚጠቁሙ መረጃ አቅራቢዎች የሚደረግን ማበረታቻ አስመልክቶ ደንብ ቁጥር 121/2013ን ማውጣቱን ስንገልጽልዎት በታላቅ ደስታ ነው! ይበሉ! ሕገ-ወጥነትን በመጠቆም የዜግነት ግዴታዎትን ከመወጣትዎ ባለፈ ጠቀም ያለ ማበረታቻ ያግኙ።
የጥቆማ አቀራረብ ስነ-ስርአቱም እንደሚከተለው ነው፥-
• አግባብ ባለው ተቋም የማይታወቅ ወይም ሊታወቅ ወይም ሊደረስበት የማይችል የተደበቀ ወይም የተሸፈነ ሕገ-ወጥ ድርጊትን የሚመለከት ጥቆማ ያለው ማንኛውም መረጃ አቅራቢ ጥቆማውን ለከንቲባ ጽ/ቤት በአካል፣ በቃል፣ በጽሑፍ፣ በስልክ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም አመቺ በሆነ በማናቸውም ሌሎች መንገዶች ሊያቀርብ ይችላል።
ጥቆማውም ከመረጃ አቅራቢው ሙሉ ስም እና አድራሻ በተጨማሪ የሚከተሉትን ዝርዝሮች መያዝ አለበት፥-
ሀ) ህገ-ወጥ ድርጊቱ የተፈፀመበትን ተቋም እና ድርጊቱን የፈጸመውን ሰራተኛ፣ ኃላፊ ወይም ግለሰብ ስም፤
ለ) ድርጊቱ የተፈፀመበት ቀንና ቦታ (ልዩ ቦታ)፤
ሐ) ጥቆማው የሚቀርብበት ዋናው ጉዳይ እና ደጋፊ መረጃዎች (ካለ)፤
መ) መረጃ አቅራቢው ወይም ጠቋሚው ህገ-ወጥ ድርጊት ከፈፀመው ሰው ጋር ያለው ግንኙነት፤
ሠ) በህገ-ወጥ ተግባሩ ተሳታፊ ወይም ተካፋይ ናቸው ብሎ የሚጠረጥራቸው ሰዎችን ዝርዝር መረጃ (ካለ)፤
• የከንቲባ ጽ/ቤት በዚህ አግባብ ጥቆማ ሲቀርብለት ጥቆማውን ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የባህር መዝገብ ላይ ይመዘግባል፤ እንደኣስፈላጊነቱም ጥቆማ የቀረበበትን ጉዳይ፣ ቀንና ጊዜ ጠቅሶ ለጠቋሚው የማረጋገጫ ደረሰኝ ይሰጣል፤ ጥቆማውንም በ48 ሰአታት ውስጥ ጉዳዩን የመመርመር ሀላፊነት ላለው ሀላፊ ማቅረብ አለበት።
• ለተመዘገበው መረጃ ማበረታቻው የሚከፈለው መረጃው አግባብ ባለው ተቋም ተመርምሮ ተጨባጭ መረጃ መሆኑ ሲረጋገጥ እና ህገ-ወጥ ተግባሩ ሲከሽፍ ወይም ንብረቱ ሲመለስ ወይም ህገ-ወጥ ተግባሩ የመጨረሻ ውሳኔ ሲያገኝ ነው።
• ሆኖም የቀረበው መረጃ ተጨባጭ መሆኑ ተረጋግጦ ሳለ በመንግስት የማስፈፀም ድክመት ምክንያት የመጨረሻ ውጤት ባይገኝም ጥቆማ አቅራቢው ማበረታቻውን የማግኘት መብት አለው።

ሰኔ 13 2014 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)
114 viewsfasika aggena, edited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 14:58:22 እንዲያው ቸር ከርመዋል?
ዛሬም ስለጡረታ ልናወጋዎ ተመልሰናል!
ኢትዮጵያ አዳዲስ የጡረታ አዋጆች ማውጣቷን በቀደመው መልእክታችን ላይ ሳያነቡ አልቀሩም! እንደው በገጠመኝ ካመለጥዎት እንኳን እንዲህ እናስታውስዎ!
• የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 907/2007 በመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267/2014፤
• የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 908/2007 ደግሞ በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014
ተሽረዋል፤ ተተክተዋል።
እናም ስለጡረታ ህጎች ለወደፊት ሰፋ ያለ ትንተና ይዘን እንደምንመለስ የገባነውን ቃል እዚህ ጋር እያጸናን ለዛሬ በመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267/2014 ስለጡረታ መውጫ እድሜና የአገልግሎት ጡረታ አበል የተደነገገውን በጥቂቱ እናጋራዎ!

ስለጡረታ መውጫ ዕድሜ
1/ የጡረታ መውጫ ዕድሜ፣ የመንግሥት ሠራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበውን የልደት ዘመን መሠረት ያደረገ፣ ሲሆን ከመከላከያ ሠራዊትና ከፖሊስ አባላት በስተቀር ለሌሎች የመንግሥት ሠራተኞች 60 (ስልሳ) ዓመት ነው፤
2/ የሚኒስትሮች ምክር-ቤት በጥናት ላይ ተመስርቶ በልዩ ሁኔታ ለሚታዩ የሙያ መስኮች ወይም በከባድ ወይም ለጤንነትና ለሕይወት አስጊ በሆኑ የሥራ መስኮች ላይ ለተሰማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ከ60 (ስልሳ) አመት የበለጠ ወይም ያነሰ የጡረታ መውጫ ዕድሜ ሊወስን ይችላል፤

ስለአገልግሎት ጡረታ አበል
1/ ቢያንስ 10 (አስር) ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው በመድረሱ ከስራ ሲሰናበት የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ-ልክ ይከፈለዋል፤
2/ ቢያንስ 10 (አስር) ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሠራተኛ ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በራሱ ፈቃድ አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሲደርስ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ-ልክ ይከፈለዋል፤
3/ ቢያንስ 25 (ሐያ-አምስት) ዓመት ያገለገለ የመንግስት ሠራተኛ ከዲስፕሊን ጉድለት በስተቀር በራሱ ፈቃድ አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሊደርስ አምስት ዓመት ከሚቀረው ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕድሜ-ልክ የአገልግሎት ጡረታ አበል ይከፈለዋል፤
4/ ቢያንስ አንድ ሙሉ የምርጫ ዘመን ያገለገለ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊ ወይም የምክር-ቤት አባል ከኃላፊነት ሲነሳ ዕድሜው 50 (ሀምሳ) ዓመት የሞላው ከሆነ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ-ልክ ይከፈለዋል፤
5/ በተራ ቁጥር (2) ወይም (3) መሠረት አገልግሎት ያቋረጠ የመንግስት ሠራተኛ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሳይደርስ በጤና ጉድለት ምክንያት ለሥራ ብቁ አለመሆኑ ከተረጋገጠበት ጊዜ ቀጥሎ ካለው ወር ጀምሮ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ-ልክ ይከፈለዋል፤ የሞተ ዕንደሆነም ከሞተበት ጊዜ ቀጥሎ ካለው ወር ጀምሮ ለተተኪዎች አበል ይከፈላል፤።
6/ የመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ህልውና በማክተሙ፣ የሰው ኃይል ብዛት ከሚፈለገው በላይ በመሆኑ ወይም ከፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘ ከሥራ እንዲሰናበት የተደረገና አገልግሎቱ ከ25 ዓመት ያላነሰና ዕድሜው ከ50 ዓመት ያላነሰ የመንግስት ሰራተኛ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ሲወሰን የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ ዕድሜ-ልክ ይከፈለዋል፤

ሰኔ 02 ቀን 2014 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ)
166 viewsfasika aggena, 11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 17:51:20 ሰላም!
ዛሬ ትንሽ ስለጡረታ!
ኢትዮጵያ አዳዲስ የጡረታ አዋጆች ማውጣቷን ሰምተዋል? ይኸውልዎ!
• የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 907/2007 በመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267/2014፤
• የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 እና ማሻሻያው አዋጅ ቁጥር 908/2007 ደግሞ በግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1268/2014
ተሽረዋል፤ ተተክተዋል።
እነዚህ ህጎች ለወደፊት በሰፊው የምንመለስባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለዛሬ በመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 1267/2014 ስለአገልግሎት ዘመን የተደነገገውን በጨረፍታ እናጋራዎ!
የአገልግሎት ዘመን አቆጣጠር
1/ የመንግሥት ሠራተኛ የአገልግሎት ዘመን መቆጠር የሚጀምረው በመንግሥት ሰራተኝነት ከተቀጠረበት ወይም ከተመደበበት ቀን አንስቶ ሲሆን በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ጡረታ አቅድ ሽፋን ባለው ድርጅት የፈፀመው የአገልግሎት ዘመን በሙሉ ተዳምሮ ይታሰብለታል፤
2/ የሚከተሉት አገልግሎቶች ታሳቢ ይደረጉለታል፥-
ሀ) ከጡረታ መውጫ ዕድሜ በኋላ አገልግሎቱ በሕግ መሠረት ተራዝሞለት በሥራ ላይ እንዲቆይ የተደረገበት ጊዜ፤
ለ) የጡረታ መውጫ ዕድሜው በመድረሱ የጡረታ አበል ከተወሰነለት በኋላ በመንግሥት ውሳኔ ወደ ሥራ ተመልሶ አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ፤
ሐ) የደመወዝ ክፍያ ሳይቋረጥ በማናቸውም ምክንያት አገልግሎቱ ተቋርጦ የቆየበት ጊዜ፤
መ) በየወሩ ደመወዝ እየተከፈለው ሙሉ ጊዜውን በማናቸውም የመንግሥት አካል ወይም በሠራተኛ ማህበር በተመራጭነት አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ፤
ሠ) በመንግሥት መሥሪያ ቤት በጊዜያዊነት አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ፤
ረ) በመንግሥት ትዕዛዝ መንግሥት ከ50 በመቶ በታች የካፒታል ድርሻ በያዘበት ድርጅት በማገልገል ያሳለፈው ጊዜ፤
ሰ) በመንግሥት ውሳኔ በዓለም አቀፍ ድርጅት በማገልገል ያሳለፈው ጊዜ፤
ሸ) ከጡረታ መውጫ ዕድሜ በኋላ በምክር፟ቤት አባልነት አገልግሎት የሰጠበት ጊዜ፤
ቀ)የአገልግሎት ወይም የጤና ጉድለት ዳረጎት ተከፍሎት ከተሰናበተ በሗላ የወሰደውን ዳረጎት መልሶ እንደገና በመንግሥት ሠራተኛነት የተቀጠረ ወይም የተመደበ ሰራተኛ የቀድሞ አገልግሎት ይታሰብለታል፤
በ) ከሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም በፊት የጡረታ መዋጮ ተመላሽ ተደርጎለት የወሰደውን የጡረታ መዋጮ ከባንክ የማስቀመጫ ወለድ ጋር መልሶ እንደገና በመንግሥት ሠራተኛነት የተቀጠረ ወይም የተመደበ ሰራተኛ የቀድሞ አገልግሎቱ ይታሰብለታል፤
3/ ከፊደል ተራ (ሐ) እስከ (ሸ) የተመለከተው ጊዜ በአገልግሎት ዘመንነት ሊታሰብ የሚችለው ሠራተኛው ወይም ተመራጩ መክፈል ያለበትን የጡረታ መዋጮ የአሠሪውን ድርሻ ጨምሮ ራሱ የከፈለ ወይም እንዲከፈልለት ያደረገ እንደሆነ ነው፤
4/ የሚከተሉት አገልግሎቶች ታሳቢ አይደረጉለትም፡-
ሀ) አገልግሎቱ በሕጉ መሠረት ካልተራዘመ በስተቀር የጡረታ መውጫ ዕድሜው ከደረሰበት ከሚቀጥለው ወር አንስቶ የሚሰጠው አገልግሎት፤
ለ) ኢትዮጵያ ተዋዋይ ወገን የሆነችበት ማናቸውም የዓለም አቀፍ ስምምነት እንደተጠበቀ ሆኖ በሕጋዊ ፈቃድ የኢትዮጵያ ዜጋ የሆነ የመንግስት ሠራተኛ የኢትዮጵያን ዜግነት ከማግኘቱ በፊት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም በጡረታ አቅድ በተሸፈነ የግል ድርጅት የሰጠው አገልግሎት፤

ሰኔ 02 ቀን 2014 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ)
235 viewsfasika aggena, 14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 14:13:41 ሰላም!
እነሆ ዛሬ ደግሞ ስለግብር ከፋይ ደረጃዎች ጥቂት ልንልዎት ተከስተናል!
የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር979/2008 ግብር ከፋዮችን የደረጃ "ሀ"፣ የደረጃ "ለ" እና የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በሚል በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍላቸዋል። የትኞቹ ግብር ከፋዮች በየትኞቹ ምድቦች እንደሚካተቱ ቀጥሎ እንመለከታለን፥-
ሀ) የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅት፣ ወይም ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢው ብር አንድ ሚሊዮን ወይም ከዚህ በላይ የሆነ ማንኛውም ሌላ ሰው፤
ለ) የደረጃ "ለ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅትን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አንድ ሚሊዮን የሚያንስ ነገር ግን ከብር አምስት መቶ ሺህ እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
ሐ) የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅትን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አምስት መቶ ሺህ የሚያንስ ሰው ነው።
ልብ ይበሉ!
* መንግስት ታክስ ከፋዩ የሚያሳውቀውን ግብር ወይም የሚያገኘውን ሌላ መረጃ መሠረት በማድረግ ለግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ደረጃ የተለወጠ መሆን አለመሆኑን ሊወስን ይችላል።
* መንግስት ግብር ከፋዮችን የደረጃ "ሀ"፣ የደረጃ "ለ" ወይም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ብሎ ለመመደብ የሚያስችለውን ዓመታዊ ጠቅላላ የገቢ መጠን በኢኮኖሚ ጥናት ላይ በመመስረት ቢያንስ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሻሻል አለበት።

ግንቦት 22 2014 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ)
165 viewsfasika aggena, edited  11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 10:04:01 የንግድ፣ ኮንስትራክሽን፣ ባንክና ኢንሹራንስ ችሎቶች በአዲስ አደረጃጀት በአዲስ ምድብ ችሎት ተደራጀ
*
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋን ጨምር በ11 ምድብ ችሎቶች የወንጀል፣ ፍትሕ ብሔር እና ሥራ ክርክር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ፍርድ ቤቱ የንግድና ኢንቨስተመንት ጉዳዮች ካላቸው ልዩ ባህሪ፣ ለኢንቨትመነት የሚመች የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል አዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ለማቋቋም ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሶስት ምድብ ችሎቶች ማለትም ልደታ፣አራዳ እና ቂርቆስ ምድብ ቸሎቶች በንግድ፣ ባንክና ኢንሹራንስ እና ኮንስትራክሽን ጉዳዮችን ሲያስተናግድ የነበረውን ከሰኔ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ፒያሳ በተለምዶ ብሪቲሽ ካውንስል በሚባለው ሕንጻ ላይ በቂ የዳኞች ቢሮ፣ የችሎት አዳራሽ፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት፣ የአስማሚ ማዕከል ፣ የአስተዳደር ክፍሎች በመያዝ 12ኛው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት በሚል ስያሜ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር በመሆኑ ተገልጋዮች ይህንኑ በማወቅ እንድትስተናገዱ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ምንጭ:- የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር
Received at 7:21 PM
Viewed 53 times
155 viewsfasika aggena, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 14:21:09 ኢትዮጲያ የአካባቢ ደህንነት መብት ከሚጠብቁት አገሮች ውስጥ አንዷ ነች፡፡
ይህንን መብት ለመጠበቅ የአላማዎች ምንጭ የት እንደሆነ ያውቃሉ?
በ1987 ዓ.ም የወጣው ሕገ-መንግሥት
አንቀጽ 92
1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጲያዊ ንጹህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት፡፡
2. ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የማያናጋ መሆን አለበት፡፡
3. የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖሊሲና ፕሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሀሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት፡፡
4. መንግሥትና ዜጎች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ግንቦት 17/2014 ዓ.ም
195 viewsየሕግ ስርፀት እና ምክር መስጠት, 11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 12:02:40
181 viewsfasika aggena, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 12:02:40 በቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የሕግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት በኢትዮጵያ የውርስ ሕግ መሰረታዊ ሐሳቦች ዙሪያ ግንቦት 12 ቀን 2014 ኣ.ም ከክ/ከተማው ለተወጣጡ ነዋሪዎች ከተሰጠ ስልጠና ላይ የተወሰዱ ምስሎች
156 viewsfasika aggena, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 17:10:05 ጤና ይስጥልኝ!
በ1987ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት
የመከላከያ መርሆች ምንን መሠረት ያደረገ ነው?
አንቀፅ 87
የመከላከያ መርሆዎች
1. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች የብሔረሰቦት እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋዕዖ ያካተተ ይሆናል፡፡
2. የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚመራው ሲቪል ይሆናል፡፡
3. የመከላለያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
4. የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
5. የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል፡፡

አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ግንቦት 12/2014 ዓ.ም
188 viewsebise, edited  14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ