Get Mystery Box with random crypto!

የንግድ፣ ኮንስትራክሽን፣ ባንክና ኢንሹራንስ ችሎቶች በአዲስ አደረጃጀት በአዲስ ምድብ ችሎት ተደራጀ | የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

የንግድ፣ ኮንስትራክሽን፣ ባንክና ኢንሹራንስ ችሎቶች በአዲስ አደረጃጀት በአዲስ ምድብ ችሎት ተደራጀ
*
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድሬደዋን ጨምር በ11 ምድብ ችሎቶች የወንጀል፣ ፍትሕ ብሔር እና ሥራ ክርክር ጉዳዮች ላይ የዳኝነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ፍርድ ቤቱ የንግድና ኢንቨስተመንት ጉዳዮች ካላቸው ልዩ ባህሪ፣ ለኢንቨትመነት የሚመች የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል አዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት ለማቋቋም ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሶስት ምድብ ችሎቶች ማለትም ልደታ፣አራዳ እና ቂርቆስ ምድብ ቸሎቶች በንግድ፣ ባንክና ኢንሹራንስ እና ኮንስትራክሽን ጉዳዮችን ሲያስተናግድ የነበረውን ከሰኔ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ ፒያሳ በተለምዶ ብሪቲሽ ካውንስል በሚባለው ሕንጻ ላይ በቂ የዳኞች ቢሮ፣ የችሎት አዳራሽ፣ የአንድ መስኮት አገልግሎት፣ የአስማሚ ማዕከል ፣ የአስተዳደር ክፍሎች በመያዝ 12ኛው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ምድብ ችሎት በሚል ስያሜ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር በመሆኑ ተገልጋዮች ይህንኑ በማወቅ እንድትስተናገዱ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ምንጭ:- የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር
Received at 7:21 PM
Viewed 53 times