Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም! እነሆ ዛሬ ደግሞ ስለግብር ከፋይ ደረጃዎች ጥቂት ልንልዎት ተከስተናል! የፌደራል የገቢ ግብ | የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

ሰላም!
እነሆ ዛሬ ደግሞ ስለግብር ከፋይ ደረጃዎች ጥቂት ልንልዎት ተከስተናል!
የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር979/2008 ግብር ከፋዮችን የደረጃ "ሀ"፣ የደረጃ "ለ" እና የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በሚል በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፍላቸዋል። የትኞቹ ግብር ከፋዮች በየትኞቹ ምድቦች እንደሚካተቱ ቀጥሎ እንመለከታለን፥-
ሀ) የደረጃ "ሀ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅት፣ ወይም ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢው ብር አንድ ሚሊዮን ወይም ከዚህ በላይ የሆነ ማንኛውም ሌላ ሰው፤
ለ) የደረጃ "ለ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅትን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አንድ ሚሊዮን የሚያንስ ነገር ግን ከብር አምስት መቶ ሺህ እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
ሐ) የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ፥- ድርጅትን ሳይጨምር ዓመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አምስት መቶ ሺህ የሚያንስ ሰው ነው።
ልብ ይበሉ!
* መንግስት ታክስ ከፋዩ የሚያሳውቀውን ግብር ወይም የሚያገኘውን ሌላ መረጃ መሠረት በማድረግ ለግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ደረጃ የተለወጠ መሆን አለመሆኑን ሊወስን ይችላል።
* መንግስት ግብር ከፋዮችን የደረጃ "ሀ"፣ የደረጃ "ለ" ወይም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ብሎ ለመመደብ የሚያስችለውን ዓመታዊ ጠቅላላ የገቢ መጠን በኢኮኖሚ ጥናት ላይ በመመስረት ቢያንስ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሻሻል አለበት።

ግንቦት 22 2014 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህግ ስርጸትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ)