Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጲያ የአካባቢ ደህንነት መብት ከሚጠብቁት አገሮች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ ይህንን መብት ለመጠበቅ | የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

ኢትዮጲያ የአካባቢ ደህንነት መብት ከሚጠብቁት አገሮች ውስጥ አንዷ ነች፡፡
ይህንን መብት ለመጠበቅ የአላማዎች ምንጭ የት እንደሆነ ያውቃሉ?
በ1987 ዓ.ም የወጣው ሕገ-መንግሥት
አንቀጽ 92
1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጲያዊ ንጹህና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት፡፡
2. ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የማያናጋ መሆን አለበት፡፡
3. የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖሊሲና ፕሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሀሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት፡፡
4. መንግሥትና ዜጎች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡
አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ግንቦት 17/2014 ዓ.ም