Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ! በ1987ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት የ | የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት

ጤና ይስጥልኝ!
በ1987ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት
የመከላከያ መርሆች ምንን መሠረት ያደረገ ነው?
አንቀፅ 87
የመከላከያ መርሆዎች
1. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች የብሔረሰቦት እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋዕዖ ያካተተ ይሆናል፡፡
2. የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚመራው ሲቪል ይሆናል፡፡
3. የመከላለያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
4. የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
5. የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል፡፡

አሊ ሣፊ (አቃቤ ሕግ)
ግንቦት 12/2014 ዓ.ም