Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.78K
የሰርጥ መግለጫ

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2022-07-24 12:50:05 መላውን ዓለም ከመጨበጥ ይልቅ ራስን መጨበጥ የተሻለ ነው

ምንጭ ፦ ህያውነት ፫ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ ሀብታሙ ተስፋዬ
ተስፋሁን ምትኩ

ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው - እንደ አንድ እምቅ አቅም፡፡ ሲወለድ ልከኛ ሆኖ አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ልዩ ነው - ምክንያቱም በመላው ህልውና ውስጥ ሰው ብቻ ነው አንድ አቅም ሆኖ የሚወለደው፤ ሌሎች እንስሳት ልከኛ ሆነው ነው የሚወለዱት፡፡

አንድ ውሻ ሲወለድ ውሻ ሆኖ ነውና መላ ህይወቱንም እንዲያ ሆኖ ይኖራል። አንድ አንበሳ ሲወለድ አንበሳ ሆኖ ነው፡፡ ሰው ሲወለድ ግን ሰው ሆኖ አይደለም፡፡ ሰው ሲወለድ እንደ ዘር ሆኖ ነው። ሰው ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ሰው የወደፊት ተስፋ አለው! ሌሎች እንስሳት ግን ተስፋ የላቸውም፡፡ ሁሉም እንስሳት ሲወለዱ በደመነፍስ ፍፁም ሆነው ነው፡፡ ሰው ብቸኛው ፍፁም ያልሆነ እንስሳ ነው። ስለዚህም በሰው ላይ እድገት፣ ዝግመተ - ለውጥ ይቻላል።

ትምህርት በእቅምና በልከኝነት መካከል ያለ ድልድይ ነው። ትምህርት በዘር መልክ ራሳችሁን እንድትሆኑ ያግዛችኋል፡፡ በተራ ትምህርት ቤቶች፣ በኮሌጆችና በዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት አይደለም። በእነዚህ ተቋማት የምታገኙት ትምህርት ጥሩ ስራ፣ ጥሩ ገንዘብ እንድታገኙ የሚያደርጋችሁ ብቻ ነው:: እውነተኛ ትምህርት አይደለም፤ ህይወትን አይሰጣችሁም። በቃ የኑሮዋችሁን ደረጃ ከፍ ቢያደርገው ነው፤ ነገር ግን የተሻለ ኑሮ የተሻለ ህይወት አይደለም፤ ሁለቱ አንድ አይደሉም።

በዓለም የሚሰጠው ትምህርት ተብዬ ነገር ዳቦ እንድታገኙ ብቻ የሚያዘጋጃችሁ ነው። ኢየሱስ እንዳለው «ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም::>> ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ ደግሞ ይህን ነው እያደረጉ ያሉት - በተሻለ፣ በቀለለ፣ በተመቸ፣ ጥረት፣ ድካም በሌለበት መንገድ ዳቦ እንድታገኙ ያግዛችኋል። ስራቸው በሙሉ እናንተን ዳቦና ቅቤ እንድታገኙ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትምህርት በጣም፣ በጣም ኋላቀር ነው:: ለህይወት አያዘጋጃችሁም፡፡

ስለዚህም ብዙ ሮቦቶች ሲረማመዱ ታያላችሁ:: እንደ ተላላኪዎች፣ የጣቢያ ተቆጣጣሪዎች፣ ዋና ሰብሳቢዎች ብቃት አላቸው:: ፍፁማን ናቸው፣ ጥበበኞች ናቸው:: በጥልቀት ብትመለከቷቸው ግን ለማኞች እንጂ ሌላ ምንም እንዳልሆኑ ትረዳላችሁ፡፡ የህይወትን እንዲት ቅንጣት እንኳን አልቀመሱም፡፡ ህይወት ምን እንደሆነ፣ ፍቅር ምን እንደሆነ፣ ብርሃን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ ስለ እግዚአብሄር ምንም አያውቁም፣ ህልውናን አልቀመሱም፣ እንዴት መዝፈን፣ መደነስ፣ መደሰት እንዳለባቸው አያውቁም:: የህይወትን ሰዋሰው የማያውቁ መሀይማን ናቸው። አዎ፣ ከሌሎች የበለጠ ያገኛሉ፤ ከሌሎች የበለጠ ብልጣ ብልጦች ናቸው፤ በስኬት መሰላል ከፍ ብለው ይወጣሉ - በውስጣቸው ግን ባዶ፣ ምስኪኖች ናቸው፡፡

ትምህርት ውስጣዊ ብልፅግናን ያጐናፅፋል፡፡ የበለጠ መረዳ መስጠት በጣም ኋላቀር የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ነው። ኋላ ቀር ነው ያልኩት በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው፤ ካልተማርኩ በህይወት መቆየት አልችልም፣ በሚለው አስተሳሰብ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ሗላቀር ነው ያልኩት በውስጡ ነውጥን ስላዘለ ነው፤ ውድድርን ያስተምራችሗል፣ ምኞታም ያደርጋችኋል። ሌላ ምንም ሳይሆን ሰዎች እርስ በርስ የሚጠላሉበት የውድድር ዓለም ለመፍጠር የሚደረግ ዝግጅት ነው።

ስለዚህም ዓለም የእብዶች መኖሪያ ሆናለች። በዚህ ሁኔታ ፍቅር ሊወጣ አልቻለም። አንዱ የሌላኛውን ጉሮሮ በሚበጥስበት በዚህ ነውጠኛ፣ ምኞታም የውድድር ዓለም ውስጥ እንዴት ፍቅር ሊታይ ይችላል? ሗላ ቀር ነው ያልኩት «በደንብ ካልተማርኩ፣ በቂ ከለላ ካላገኘው፣ ደህና መረጃ ካልያዝኩ በህይወት ፈተና ውስጥ አሸናፊ አልሆን ይሆናል>> በሚል ፍራቻ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ህይወትን እንደ ትግል ብቻ ነው የሚመለከታት፡፡

እኔ ትምህርትን የማየው ህይወትን እንደ ትግል ሳይሆን እንደ ደስታ ሲቀርፅ ነው፡፡ ህይወት ውድድር ብቻ መሆን የለባትም፣ ደስታ ጭምር እንጂ፡፡ ትምህርት በዓለም ላይ ከሚገኙ ዘፈን፣ ዳንስ፣ ቅኔ፣ ሙዚቃ፣ ስዕል፤ ዛፎች፣ አዕዋፋት፣ ሰማይ፤ ፀሃይ፣ ጨረቃ እና ሌሎች ነገሮች በሙሉ ሊያዋህዳችሁ ይገባል፡፡

ትምህርት ራሳችሁን እንድትሆኑ ሊያዘጋጃችሁ ይገባል። አሁን ግን አስመሳዮች እንድትሆኑ እያዘጋጃችሁ ነው፤ ሌሎችን እንዴት መምሰል እንዳለባችሁ እያስተማራችሁ ነው፡፡ ይህ ትምህርት ማሳት ነው፡፡ ትክክለኛ ትምህርት ራሳችሁን በእውነተኛ መንገድ እንዴት እንደምትሆኑ ያስተምራችኋል። እናንተ የተለያችሁ ናችሁ። እናተን የሚመስል ማንም የለም ፡ ወደፊትም አይኖርም። ይህ እግዚአብሄር ያጐናፀፋችሁ ታላቅ በረከት ነው። ይህ የእናንተ ክብር ነው! ልዩ መሆን ነው፡፡ አስመሳይ አትሁኑ፤ የካርቦን ቅጂዎች አትሁኑ።

እናንተ ትምህርት የምትሉት ነገር ግን ይህን እያደረገ ነው፡፡ የካርቦን ቅጂዎችን ይፈጥራል፤ እውነተኛ መልካችሁን ያጠፋል። <<ትምህርት>> የሚለው ቃል ሁለት ትርጉሞች አሉት፤ ሁለቱም ደግሞ ውብ ናቸው። አንደኛው ትርጉሙ ተግባር ላይ ባይውልም በደንብ ይታወቃል- አንድ ነገር ከውስጣችሁ ማውጣት። <<ትምህርት» ማለት በውስጥ ያለን ማውጣት፣ ውሀን ከጉድጓድ እንደ ማውጣት አቅምን በተግባር ማውጣት ነው።

ይህ ግን አልተተገበረም፡፡ ከዚህ ይልቅ ነገሮች ወደ ውስጥ እንዲገቡ እንጂ እንዲወጡ አልተደረገም። ህብረተሰብ እና ታሪክ፣ ሳይንስ እና ሂሳብ ወደ ውስጣችሁ ያንቆረቁርላችኋል። እናም ፓሮቶች ትሆናላችሁ። ልክ እንደ ኮምፒዩተር ይጉሰጉሱባችኋል:: የእናንተ የትምህርት ተቋማት ነገሮች በጭንቅላቶቻችሁ ውስጥ የሚታጨቁባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

እውነተኛ ትምህርት በውስጣችሁ የተደበቀውን (እግዚአብሔር በውስጣችሁ እንደ ሃብት ያስቀመጠውን) አውጥቶ፣ ገልጦ አንፀባራቂ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል፡፡

ትምህርት ሌላም ትርጉም አለው:: ትምህርት (Education) የሚለው ቃል የመጣው Educare ከሚለው ቃል ነው:: ትርጉሙም ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት እንደማለት ነው፡፡ ከጨለማ ወደ ብርሃን ማምጣት በጣም አስፈላጊ ትርጉም አለው፡፡ ዮፓኒሻዶች እንዲህ ይላሉ «ጌታችን ሆይ፣ ከሃሰት ወደ እውነት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ፣ ከሞት ወደ ህይወት ምራን፡፡ ጌታችን ሆይ ከጨለማ ወደ ብርሃን ምራን፡፡» ይህ ነው «የትምህርት» ትክክለኛ ትርጉም፡- ከጨለማ ወደ ብርሃን።

ሰው ግን በጨለማ፣ ባለመንቃት ውስጥ እየኖረ ነው:: ሆኖም በብርሃን ምሉዕ መሆን ይቻላል፡፡ ነበልባሉ እዚያ አለ፡፡ ይሁንና መንበልበል፣ ወደ ውጭ መውጣት አለበት፡፡ ንቃት እዚያ አለ፤ ይሁን እንጂ መቀስቀስ አለበት:: ሁሉም ነገር ተሰጥቷችኋል! ስትወለዱ ይዛችሁት መጥታችኋል፡፡ ሰብአዊ አካል ስላለን ብቻ ሰው ነን ማለቱ ስህተት ነው፡፡ ለዘመናት ለብዙ መሳሳቶች መንስኤ የሆነው ይህ አስተሳሰብ ነው፡፡

ሰው ሲወለድ እንደ አንድ እድል፣ ሁኔታ ሆኖ ነው። ይህን የተጠቀሙበት ደግሞ እጅግ ጥቂቶች ብቻ ናቸው - ኢየሱስ፣ ቡድሀ፣ መሐመድ፣ ባሃውዲን። እውን ሰው የሆኑት እጅግ ጥቂቶች ናቸው- በብርሀን ሲመሉ የቀረ ጨለማ አይኖርም፣ በነፍስ ውስጥ የሚተርፍ አለመንቃት አይኖርም- ሁሉም ነገር ብርሃን ሲሆን፣ እናንተ ንቃትን ስትሆኑ...

ንቃት፣ ንቃት ብቻ፣ ንፁህ ንቃት... ይህ ያለው ብቻ ምሉዕ ይሆናል። ይሄን ጊዜ ህይወት ቡራኬ ትሆናለች።

ትምህርት ከጨለማ ወደ ብርሃን ይወስዳችኋል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
27.8K viewsedited  09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 09:04:53 10 minutes to start your day right
Motivational speach

@Zephilosophy
@Zephilosophy
6.8K viewsedited  06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 21:37:59 Rophnan ft Julian marley
Merkeb
(አርምሞ)


የልቦናን መቅረፅ አብርቶ
የሚጓዝ መች ይሰምጣል ከቶ
ወደ ውስጥ ላየ ለገባው
መርከቡ ሰፊ ነው ከውሀው


ሰው ራሱን ካዳመጠ ከራስ ከታረቀ
የመኖርን ሚስጢር እውነት አወቀ
ልብ ላይ ሁሌም ድምፅ አለ እሱን ተከተለህ
በሶስተኛው በሙሉ አይንህ ታያለህ


@Zephilosophy
@Zephilosophy
750 viewsedited  18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 22:41:41 ፍራንሲስ ቤከን

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ሀሁ
ፀሀፊ ፦ በላይ ደስታ

ፍራንሲስ ቤከን እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 1561 ለንደን ውስጥ ከአባቱ ከ ኒኮላስ ቤከን እና በዘመኑ በጣም የተማረች ሴት ከነበረችው እናቱ አኔ ኩክ ተወለደ። በ14 ዓመቱ ወደ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ገባ፡፡ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ፣ ሥላሴ ኮሌጅ ለሁለት ዓመታት የተማረ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ በእንግሊዝ አምባሳደር ባልደረባነት ለሦስት ዓመታት በፈረንሳይ ቆይቷል፡፡ ከዚያ በ1579 በአባቱ ሞት ምክንያት ወደ እንግሊዝ ለመመለስ ተገደደ፡፡

በ23 ዓመቱ፣ ቀድሞውኑ ንግስት ኤልሳቤጥን በበርካታ ጉዳዮች ተቃዋሚ በመሆን 1584 የእንግሊዝ ፓርላማ የምክር ቤት አባል ሆነ፡፡ እስከ 1614 ድረስ በኢንግሊዝ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ፣ ክርክሮች ውስጥ የጎላ ሚና የነበረው ስለመሆኑ ተጽፏል።

በንግስት ኤልዛቤት ፍርድ ቤት፣ ከፍተኛ ባለስልጣን መካከል አንዱ የሆነው የኒኮላስ ቤከን ልጅ ፍራንሲስ ቤከን 1621 ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነ። እ.ኤ.አ በ 1621 ፍራንሲስ ቤከን በጉቦ ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ለሁለት ቀናት ከታሰረ በኋላ በንጉሱ ምህረት የተደረገለት ቢሆንም፣ ከዚያ በኋላ ወደ ህዝባዊ አገልግሎት አልተመለሰም፡፡ የአስተዳደር፣ የፍልስፍና እና የጥበብ ስራዎችን በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ሲያዘጋጅ ቆይቶ በ1618 በሞት ተለየ::

ቤከን በዘመኑ፣ በእንግሊዝ ውስጥ የሀሳብ ባህልን ፈጠረ፤ ሬኔ ዴካርት ደግሞ በፈረንሳይ ተመሳሳይ ንቅናቄ አመጣ፡፡ እነዚህ ሁለት ታላላቅ የአዉሮፓ አሳቢዎች፣ ለዘመናዊው ዓለም መወለድ እንደጀርባ አጥንት የሚወሰዱ ናቸው።

በእንግሊዝ የነበረው ከፍተኛ የሀይማኖት አማኝ ዜጋ፣ የቤከንን የተራቀቀ አእምሮ ለመጠቀም የተዘጋጀ አልነበረም፡፡ በወቅቱ የነበረው የእንግሊዝ ህዝብ፣ ነገስታቱ ሲያዙት ለጦርነት ይወጣል ፤ ወይም ለአንዳች ግዳጅ ይነሳል እንጂ በራሱ ሀሳብ አይመራም ነበር፡፡ ቀሳውስቱ የሚወስኑለትን ጉዳይ እሺ ብሉ ያገለግላል እንጂ፣ “ይሄ እንዴት ይሆናል?” ብሎ የመሞገት ልምድም፣ አቋምም አልነበረውም፡፡

እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን፣ እንዲህ አይነት ኋላ ቀር ልማድ በእንግሊዝ መሬት ላይ በግልጽ ይታይ ነበር። ፍራንሲስ ቤከንና ዊሊያም ሼክስፒር ወደ እንግሊዝ ምድር ሲመጡ፣ ነገሮች አዲስ መልክ ያዙ፡፡ በተለይ ደግሞ ቤከን፣ ፍልስፍናዊ ዳራ በማስያዝ ያቀረባቸው ጥቁምታዎች፣ ለሹማምንቱም ገዢ ሀሳብ ነበር፡፡

“ስልጣኔን የምንፈልግ ከሆነ ከልማድና ዶግማዎች መውጣት አለብን። በማህበረሰብ ውስጥ በተለያየ መልኩ የሚገለጹ ዶግማዎች አሉ፤ ኃይማኖት አንዱ ነው! ፊዉዳላዊ የከበርቴ ኢኮኖሚ ሌላው ነው! ነገዴነት ወይም በጎሳ ማመን ሌላው ነው...” እያለ እያንዳንዱን ልማድ በጥልቀት መረመረ። እንዴት ተደርጎ ባለ ጥበብ መሆን እንደሚቻልና እነዚህን ቀኖናዊ ባህሎች አስተካክሎ የላቀ ህዝብ መፍጠር እንደሚቻልም ተነተነ፡፡

እናም በእንግሊዝ ስርዓት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ ከፈተ። በተጓዳኝ የተነሱት እንደ ቶማስ ሆብስና ሎክ ያሉ ፈላስፎችም መፈጠር ስለሚገባው የመንግስት ቅርጽና ባህሪ ፍልስፍናቸውን አንፀባረቁ፡፡ ዊሊያም ሼክስፔር ደግሞ በምናቡ ሩቅ ተጓዘና የማህበረሰቡ ህይዎት እንዴት ባለ የባህል ቅርፅ ውስጥ መግባት እንዳለበት የሚያወሳ የጥበብ ፈርጥ ሆነ፡፡ ይህ ክስተት፣ እንግሊዝ ከረዥም ዘመናት የልማድ እንቅልፍ አነቃት፡፡ “ጥቂት ማሰብ የሚችሉ ግለሰቦች ሲነሱ የሚፈጠር አብዮት ሰፊ ህዝብን ይቀርጻል” እንዲሉ፣ እነዚያ ጥቂት የእንግሊዝ አሳቢዎች በእንግሊዝ ምድር ድንቅ ብርሃን አበሩ።

እንግሊዝ እስከአንደኛው የዓለም ጦርነት፣ በዓለም ታላቅ ኢምፓየር ነበረች። በአዉሮፓም ኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂን በመፍጠርና በመጠቀም ቀዳሚ ናት። ዛሬ ድረስ፣ የምድርን የሀሳብ ቅርጽ የቀየሩ ሳይንቲስቶችና ፈላስፎች አፍርታለች። ለዚህ አስደናቂ ታላቅነት እንድትበቃ ታዲያ፣ ወደ ሀሳብ አብዮት ያስገባት ፍራንሲስ ቤከን የተባለ ፈላስፋ ነው፡፡ እሱ እስከተነሳበት አንዳንድ ብልጭታዎች ቢኖሩም ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ የተፈጠረው ግን በሱ ተጽዕኖ ምክንያት ነው፡፡

ቤከን፣ የዓለም ጠቢባንና ሳይንቲስቶችን ስራዎችና ታሪክ በማጥናት፣ በማስታወሻው ላይ ያስቀር ነበር፡፡ በዚህ ስራው ያዳበረውን የአመታት የንባብና ማሰላሰል ልምድ ተጠቅሞ፣ በሀገሩ ያለውን መውጫ መግቢያ የሚያሳጣ የጎሳ ጦርነት፣ ርሃብና ኋላ ቀርነት እንዴት መታደግ እንደሚችል ያስብ ጀመር። የተለያዩ ስልጣኔዎችንና የእድገት ሚስጢሮችንም ፈተሽ።

በዚያው ሳይቆም፣ ልምዱን በሚኖርበት ማህበረሰብ ለውጥ ለመጠቀም ወሰነ። የመንግስት አማካሪ እስከመሆንም ደረሰ፡፡ ወቅቱ አሁን ላይ እንደምናስበው የሀሳብ ነጻነት ያለገደብ የተንበሻበሸበት አልነበረም፡፡ በአንድ በኩል የፕሮቴስታንት እምነት ከፍተኛ ንቅናቄ አለ፤ በሌላ በኩል የካቶሊክ ጳጳሳት ከትዕዛዛቸው ውጪ የሆነ እምነትም ሆነ ጥበብ ለሚያራምድ ሰው ምህረት አያውቁም፡፡ ከነህይወቱ ጭምር የሚያቃጥሉበት ዘመን ነበር፡፡

ቢሆንም ግን ቤከን የነሱን ክፋ ተግባር አልፈራም። ይልቁንም ጭንቀቱ የነበረው የነገዋ ሀገሩ በሳይንስና ፍልስፍና ልቃ እንዴት ትውጣ የሚለው ነበር። አእምሮውን በሚገባ ተጠቀመበት፤ ብዙ አነበበ፤ ብዙ አስተዋለ፤ በመጨረሻም የሀሳቦችን ጉልበት አወቀ። እናም ሀገሩ ከትዉፊት ልማድ ወጥታ፣ በምክንያት የሚያምን አሳቢ ትውልድ ካልተፈጠረባት ሩቅ ሳትራመድ የማይጨበጥ ሀሳብን በሚያራምዱ ህዝቦች እንደምትጠፋ አበክሮ ተናገረ። ማሳመኛዎቹንም አቀረበ፡፡

ሀሳቦቹን በደምሳሳው አላቀረበም፡፡ በጥልቀት የመረመረውን ታሪክ፣ ስልጣኔ፣ ፍልስፍናና የጥበብን ኃይል በጥንቃቄ አደራጅቶና አሰናድቶ፣ ነገስታቱ ለሚገባቸው ልኬት ስላሳያቸው ዓላማውን ተቀበሉት፡፡ በአዉሮፓ የስልጣኔ መነቃቃት እንዲፈጠር መነሻ የሆኑት ሁለት አሳቢዎች ሲሆኑ፣ አንዱ ፍራንሲስ ቤከን ሲሆን፣ ሌላኛው ፈረንሳዊው ዴካርት ነው፡፡

አይዛክ ኒውተን፣ አንቶኒ ቫን ሊዮን ሁክ፣ ቮልቴር፣ ሩሶ፣ ኢማኑኤል ካንትና ሌሎችም ታላላቅ የዘመናዊው ዓለም መስራች አሳቢዎች ሲነሱ፣ በኩር መንገድ ጠራጊዎቹ ቤከንና ዴካርት ናቸው፡፡ “እውቀቶችን ሁሉ ሳልመርጥ እንደሰፈሬ ነበር የማያቸው” ይለናል ቤከን፡፡ እውቀቶችን አብዝቶ መጠጣት ወደ ነገ ለመሻገር የሚያበቃ ኃይል መሆኑን ለማስረዳት፡፡

ፍራንሲስ ቤከን ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ፣ መንታ ስኬቶችን ማቀፍ ችሏል። አንድም በአሰላሳይነት ከታላላቅ ፈላስፎችና አሳቢዎች መሃል ሲመደብ የሀሳብ ምህዋሩን ለሀገሩ ብልጽግና እንዲሆን በመቃኘቱ ደግሞ የስልጣኔ አርበኛ ሆኖ ይወሳል።

ሬኔ ዴካርት፣ ከፍራንሲስ ቤከን እኩያ ዘመን ላይ የኖረ ፈላስፋና የሂሳብ አዋቂ ነው። ራሺናሊዝም፣ የተሰኘ ፍልስፍና ያስተዋወቀ አዉሮፓዊ ነው። ካርቴዢያን ጠለል የተሰኘ የሂሳብ ማንጠሪያ ሀሳብንም ፈጥሯል። ራሺናሊዝም የዘመናዊ ፍልስፍና መነሻ ነው፡፡ በምክኒያትና ትንተና ላይ የሚመሰረት የፍልስፍና ቅርጽ ነው፡፡ የፈረንሳይ አብዮት ቀንዲሎች እንዲወለዱ ረኔ ዴካርት በኩር መምህር ነው። ትልቅ መነቃቃትና ለውጥ ፈጥሯል።

ከፍራንሲስ ቤከን ፍጹም ከእምነት የሚወለድ ስርዓት ላይ የተማከለው ሀገረመንግስት በምክኒያትና አሰላሳይ አእምሮ እንዲበለጽግ መሰረት ጥሏል። ነፍስን ጭምር ሳይቀር በፍልስፍና የማየት መንገድ ያሳየ ፈላስፋ ነው፡፡ ፍራንሲስ ቤከን እንግሊዝን ማንቃት እንደቻለ ሁሉ፣ ዴካርት የፈረንሳይን ዜጎች አንቅቷል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
1.6K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 13:56:25 ሾፐንሀወር

ምንጭ ፦ የፍልስፍና ሀሁ
ፀሀፊ ፦ በላይ ደስታ

የሾፐንሃወርን የትውልድ ቦታ አንዳንዶቹ፣ ጀርመን ውስጥ ፍራንክፈርት በተባለ ቦታ የተወለደ መሆኑን ሲገልጹ፣ ሌሎቹ ደግሞ፣ በፖላንድ ዳንዚግ በተባለ ቦታ ከነጋዴ ቤተሰብ እ.ኤ.አ የካቲት 22 ቀን 1788 የተወለደ መሆኑን ይገልጻሉ። ሾፐንሀወር በህይወት ዘመኑ፣ ልጅም ሚስትም ሳይኖረው፤ ከነጋዴ አባቱ የወረሰውን ሀብት ነግዶ ለማብዛት ሳይጥር፣ ለፍልስፍናው ታማኝ ሆኖ በመኖር እ.ኤ.አ. መስከረም 21 ቀን 1860 ጀርመን ፍራንክፈርት በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ማረፉ ተዘግቧል፡፡

ሾፐንሃወር በፍልስፍና ዘመኑ፣ የፕላቶ እና የኢማኑኤል ካንት አምላኪ፣ እንዲሁም የጆርጅ ዊልሄልምና የፍሬድሪክ ሄግል ተቀናቃኝ ነበር። ሾፐንሃወር፤ ምንም እንኳን በሕይወት ዘመኑ በሰራቸው ሥራዎች ብዙም ትኩረት ባይሰጠውም፣ ህይወቱ ካለፈ በኋላ፣ በዘመኑ ፍልስፍና፣ ሥነ ጽሑፍና ሳይንስ እይ ተጽዕኖ አሳድሯል። ተጽዕኖ ካሳደረባቸው ፈላስፎች መካከል፤ ፍሬድሪክ ኒቼ፣ ሪቻርድ ዋግነር፣ ሊዮ ቶልስቶይ፣ ሉድቪግ ዊትገንስቴይን፣ ኤርዊን ሽሮዲንገር፣ ጉስታቭ ማህለር፣ ጆሴፍ ካምቤል፣ አልበርት አንስታይን፣ ካርል ጁንግ፣ ቶማስ ማን፣ ጆርጅ ሉዊስ ቦርግስ እና ሳሙኤል ቤኬት እንደሚገኙበት ተጽፏል።

በሾፐንሀወር አስተሳሰብ፣ “የማናቸው ነገሮች ምንነት(ኢሴንስ)፣ ሰዎችንም ጨምሮ፣ እውቀታቸው፣ ምክንያታዊነታቸው ወይም መንፈሳቸው ሳይሆን ፈቃዳቸው ነው” ይል ነበር። ፈቃድ ሲል “ማናቸውንም ነገሮች፣ ከአለቶች ጀምሮ እስከ ሰው ልጅ ኅልው እንዲሆኑ የሚገፋቸውን ጉልበት ነው:: ይህ ጉልበት ምንም ምክንያት የለውም፣ ኅልው ለመሆኑም ምክንያት የለውም፣ ስለሆነም የሰው ልጅ ስቃይ ከዚህ ምክንያት የለሽ እውር ጉልበት ይመነጫል” ብሎ ሾፐንሀወር ያስተምር ነበር።

ሾፐንሀወር ለዚህ ስቃይ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የዘየደው ፈውስ፣ ሰዎች የተሻለ ንቃተህሊና እንዲኖራቸው መምከር ነበር፡፡ የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዴት ይገኛል፣ ለሚለው የእርሱ መልስ “የሰው ልጅ ፍላጎቱን ማሟላትን እንዲክድ፣ ጊዜ ሰውቶ እራሱን እንዲመረምርና ምን ቢሰራ ከስቃዩ እንደሚያመልጥ በማሰብ ነው” ይላል። ሾፐንሀወር፣ ለስቃይ ማምለጫ ሊሆን ያስችላል ብሎ ከአዘዘው ተግባር ውስጥ፣ የኪነት ስራዎችን መስራትና የተሰሩትን ማድነቅ፣ በተላይ ሙዚቃ ላይ ማተኮርን ይጠቅሳል። ሙዚቃ፣ በሾፐንሀወር አስተሳሰብ፣ ለሰው ልጆች በሰላምና በፍቅር መኖር አንዱ ምክንያት ነው ብሎ ያምናል።

በፍልስፍና ታሪክ ውስጥ፣ እንደ ሾፐንሃወር ያለ ጨለምተኛ ፈላስፋ ያለ አይመስልም:: ለጨለምተኝነቱ ምክንያት ከአስተሳሰቡ ይመነጫል። ሾፐንሃወር እንዲህ ይላል ፤ “17 አመት ሲሆነኝ የህይወትን አሰቃቂ ገፅታ ለመጀመሪያ ግዜ ተመለከትኩ:: ወጣቱን ቡድሃ ከውብ ቤተመንግስቱ አስወጥተው ጫካ ያስገቡት በሽታ እና ስቃይ እርጅና እና ሞት እኔንም እንቅልፍ ነሱኝ:: እውነታው ይቺ አለም የተሰራችው ሁላችንን በሚወድ ደግ አምላክ ሳይሆን፤ ፍጡራንን ምድር አምጥቶ በስቃያቸው በሚዝናና ክፉ አምላክ መሆኑ ነው" በማለት ይገልጻል።

እንደ ሾፐንሀወር አገላለጽ፣ “ይህን ለአይን የሚያታክት ዝብርቅርቅ አለም፣ ከኋላ ሆኖ የሚዘውር፣ ባይናችን የማናየው አንድ ታላቅ ሃይል አለ:: ፍጡራንን ሁሉ በምድር ላይ የሚያንከራትተው፤ ምድርንም በፀሃይ ዙሪያ የሚያሽከረክረው ይኸው ሃይል ነው። ይህን ሃይል ለማየት፣ እስኪ አንዴ አይናችሁን ጨፍኑና ወደውስጣችሁ ተመልከቱ። ይሄንን ያዝ፣ ያንን አባር የሚል፣ ርካታ የለሽ፣ ዘወትር ወደፊት የሚገፋ፣ በሁላችንም ውስጥ የሚርመሰመስ ሃይል ታያላችሁ” ይላል።

“ይህ ደመነፍሳዊ ኃይል፣ ስለኔም ሆነ ስላንተ ግድ አይሰጠውም። ወደዚህ ምድር አምጥቶ በዚህ እና በዚያ ሂድ እያለ እያታለለ ጉልበታችን እስኪዝል ይጋልበናል፤ ጉልበታችን ሲደክም ሌላ ፈረስ እንድንተካለት ያረግና እኛን አሰናብቶ እሱ ግልቢያውን ይቀጥላል። ይህ ነው የሚባል መዳረሻ የለውም፤ ምኞቱ ዘላለም መጋለብ ነው፡፡ እኛ ሞኞቹ ግን ሀብት፣ ዝና፣ እውቀት ወይም ስልጣን ለመጨበጥ እየሮጥን ነው፤ ይቺን ወይም ያቺን ሴት ያፈቀርነው፣ ይሄን ጥለን ያንን ያባረርነው፣ በራሳችን ምርጫና ፍላጎት፣ ለራሳችን ጥቅም እና ደስታ ይመስላችኋል? ... ይቺ አለም የተፈጠረችው ለሰው ልጅ ደስታ አይደለም። ይህን ለመረዳት ልክ ሴክስ አርገን ስንጨርስ የሚሰማንን ቀፋፊ ስሜት ማየት ብቻ በቂ ነው::” እያለ ያለምን የእሽክርክሪት ህይወት ያማርራል፡፡

እንደ ሾፐንሀወር አስተሳስብ፣ “የተሻለው አኗኗር ይሄን ሃይል በጥንቃቄ ተረድቶ በሱ ላይ ማመፅ ነው” ይላል። “ይሄን ወይም ያንን አባረህ ስትይዝ ደስተኛ ትሆናለህ” ለሚለን ሃይል ጆሮ ሳንሰጥ ምንም ሳንፈልግ ምንም ሳናባርር በርጋታ መኖር። ችግሩ ግን እንዲህ ለመኖር ስንሞክር ድብርት እና ተስፋ መቁረጥ በራችንን ያንኳኳሉ። ለዚህ ደግሞ መፍትሔው በጥበብ እና በተፈጥሮ ውበት መደመም ነው” ይለናል፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy
2.6K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:14:26 • በፍልስፍና መደመም •
• በዋለልኝ እምሩ •

• ማመን ሚከብዱና ሚያመራምሩ
• አስገራሚ የፍልስፍና አስተሳሰቦችና
• አስደናቂ የፈላስፋዎች ግለ-ታሪኮች


@Zephilosophy
4.2K viewsedited  20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:48:51 ፍልስፍና -1
ደራሲ - ብሩህ አለምነህ

በሀገራችን ፀሀፊዎች ከተፃፉ የፍልስፍና መፅሀፎች ውስጥ በአንደኝነት የማስቀምጠው ግሩም መፅሀፍ ነው።አንብበው ይደመሙ!!

ፓለቲካዊ ፍልስፍና
ዲበ- አካላዊ ፍልስፍና
ማህበራዊ ፍልስፍና
የስነ-ፍቅር እና የስነ-ውበት ፍልስፍናዊ ሀሳቦች
በጥልቀት ይዳሰሳሉ !!

@Zephilosophy
4.8K viewsedited  19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 22:04:48
ክረምቱን በንባብ እንድታሳልፉ ምርጥ pdf መፅሀፎችን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።

@Zephilosophy
4.1K viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 23:09:42
መጽሐፍ ውስጥ የተሰወረው መዝገብና ኃብት!

“አንድን ነገር ከጥቁሮች ለመሸሸግ ከፈለጋችሁ በመጽሐፍ ውስጥ አስቀምጡት”

“If You want to hide something from a black person, put is in a book”

ይህንን ከዚህ በፊት ሰምታችት ይሆናል፡፡ ይህ አባባል ጥቁሮች ማንበብ እንደማይወዱ፣ በዚያም ምክንያት ብዙ ነገር እንደሚቀርባቸውና ሕይወታቸውን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ የሚችልን እውቀት ችላ በማለት ኋላ ቀር እንደሆኑ ለማሳየት የሚጠቀሙበት አባባል ነው፡፡

ይህ አባባል በእኔና በእናንተ ላይ አየሰራም! ምክንያቱም እናነባለን! እውቀትን እንቀስማለን! እንለወጣለን! እናድጋለን!

ሁሉም ሰው ግን ይህንን አይለማመደውም፡፡ ላለማንበብ ደግሞ የማይሰጠው ምክንያት የለም፡፡ ማንበብ ስጀምር እንቅልፍ እንቅልፍ ይለኛል፤ ምንም የሚነበብ ጠቃሚ ነገር የለም፤ ማንበብ እጀምርና መቀጠል ግን አልችልም፣ ማንበብ እጀምርና የተወሰኑ ገጾች ካነበብኩኝ በኋላ ያነበብኩትን አላስታውሰውም . . . እና የመሳሰሉት ምክንያቶች የተለመዱ ናቸው፡፡

አንብቡ! እደጉ! ተሻሻሉ! ተለወጡ! እናንተ ለእናንተ ካላነበባችሁለት ማንም ለእናንተ አያነብላችሁም!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.1K viewsedited  20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:21:24 ደስተኛ አለመሆንን ለምን እንመርጣለን?
...የቀጠለ

ሰዎች ደስተኛ ከሆኑ በገንዘብ ልትደልሏቸው አትችሉም፤ መላ ህይወታቸውን ገንዘብ በማከማቸት አያጠፉምና፡፡ ለእነሱ ጠቅላላ ህይወትን ገንዘብ ለማከማቸት ሲባል ማባከን እብደት ነው፡፡ ሰውየው ሲሞትኮ ገንዘብ አብሮት አይሞትም።ይህ ፍፁም እብደት ነው። ደስተኛ ካልሆናችሁ በስተቀር ይህ እብደት አይታያችሁም።

ሰዎች ደስተኛ ከሆኑ የህብረተሰብ ጠቅላላ ቅርፅም ይቀየራል። ይህ ህብረተሰብ በስቃይ ነው የሚኖረው። ለዚህ ህበረተሰብ ስቃይ ትልቅ ኢንቨስትመንት ነው።ልጆቻችንን ስናሳድግ ከመጀመሪያው ጀምሮ ወደ ስቃይ እንዲያደሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ የስቃይን መንገድ ይመርጣሉ፡፡

ሁለም ሰው ማለዳ ከዕንቅልፉ ሲነሳ ምርጫ አለው። ንጋት ላይ ብቻ አይደለም በእያንዳንዱ ቅፅበት የስቃይን ወይም የደስታን መንገድ የመምረጡ እድል አለ፡፡ ይሁንና ዋጋ ሰላለው ሁልጊዜ የስቃይን መንገድ ትመርጣላችሁ:: ልምዳችሁ የዘውትር ተግባራችሁ ሆኗልና ሁልጊዜ ስቃይን ትመርጣላችሁ። በመሰቃየት ብቁ ሆናችኋል፤ መንገዳችሁ ሆኗል፡፡ አዕምሮአችሁ የመምረጥን እድል ሲያገኝ ወዲያውኑ ወደ ስቃዩ መንገድ ያደላል::

ስቃይ ቁልቁለት፤ ደስታ ደግሞ ዳገት ይመስላሉ። ደስታ የማይደረስበት ተራራ ቢመስልም ግን እውነት አይደለም:: እውነታው ከዚህ ተቃራኒ ነው። ደስታህ ቁልቁለት ነው ፤ ስቃይ ደግሞ ዳገት ነው። ስቃይ የማይደረስበት አስቸጋሪ ነገር ቢሆንም እናንተ ደርሳችሁበታል፤ የማይቻለውን ችላችኋል፤ ምክንያቱም ስቃይ ኢ -ተፈጥሯዊ ነውና፡፡ ሁሉም ሰው ስቃይን ባያፈልግም ሁለም ሰው እየተሰቃየ ነው::

ህብረተሰቡ በዚህ ረገድ ትልቅ ስራ ሰርቷል:: ትምህርት ፣ ባህል፣ የባህል ተቋማት ፣ ወላጆች፣ መምህራን. . . ሁሉም ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ ከደስታ ፈጣሪዎች፣ የሚሰቃዩ ፍጥረታትን አስገኝተዋል፡፡ ሁለም ሰው ሲወለድ ደስተኛ ሆኖ ነው፤ ሁሉም ህፃን ሲወለድ አምላክ ሆኖ ነው:: ሁሉም ሰው ሲሞት ደግሞ እብድ ሆኖ ነው:: ህፃንነትን መልሶ ማግኘት፣ መልሶ መያዝ የእናንተ ሃላፊነት ነው:: በድጋሚ ህፃን መሆን ከታደሉ ስቃያ ይጠፋል፡፡


ከአንድ ነገር ጋር ስትዋሃዱ ደስተኛ ትሆናላችሁ፡፡ ራሳችሁን እንድ ነገሩ: ስትነጥሉ (ከደስታ ቢሆን እንኳን) ትሰቃያላችሁ::ስለዚህ ቁልፉ ይህ ነው:: የራስ ኩራትን (ለራስ የሚሰጥ ከፍተኛ ግምትን) ይዞ መነጠል የሁሉም ስቃይ መነሻ ነው::

ህይወት ከምታመጣው ነገር ጋር አንድ ሆናችሁ ፣ ራሳችሁን በመተው የምትፈስሱ፣ ከሚመጣው ነገር ጋር የምትዋሃዱ ከሆነ ግን ሁሉም ነገር አስደሳች ይሆናል፡፡

ምርጫው እለ፡፡ እናንተ ግን ምርጫ መኖሩን አላስተዋላችሁም:: የተሳሳተውን መንገድ መምረጥን ልማዳችሁ አድርጋችሁታል፡፡ የቀረ ምርጫ መኖሩን አታስተውሉም::

ንቁ ሁኑ:: የስቃይን መንገድ በመረጣችሁ ጊዜ ሁሉ ምርጫውን የመረጣችሁት እናንተ መሆናችሁን አትዘንጉ:: ‹‹ምርጫውን የመረጥኩት እኔ ነኝ፣ ሃላፊነቱም የእኔ ነው፣ ይህ ሁሉ የእኔ ስራ ነው።"ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው:: ይህን ስታደርጉ ወዳያወኑ ልዩነቱ ይገለፅላችኃል:: የአዕምሮአችሁ ባህርይ ይለወጣል። ወደ ደስታ የሚወስደው መንገድ ቀላል ይሆንላችኋል፡፡

አንዴ ምርጫችሁ ይህ እንደሆነ ካወቃችሁ ሁሉም ነገር ጨዋታ ይሆናል:: ስለዚህ መሰቃየት ከፈለጋችሁ ተሰቃዩ፡: ያን ምርጫ የራሳችሁ መሆኑን በመገንዘብ ምንም ወቀሳ አታቅርቡ። ሀላፊነቱ የሌላ የማንም አይደለም ፤ ይህ የራሳችሁ ድራማ ነው:: ያንን የስጋት መንገድ ከመረጣችሁ፣ በዚህ የስቃይ ህይወት ውስጥ ማለፍ ከፈለጋችሁ
ምርጫው ፣ ጨዋታችሁ የራሳችሁ ነው ማለት ነው:: የምትጫወቱት እናንተ ናችሁ፡፡ እናም በደንብ ተጫወቱት ከዚህች ቅፅበት ጀምሮ ግን ደስተኛና በሀሴት የተሞላ ለመሆን ደጋግማችሁ ጣሩ::

ደራሲ ኦሾ
ምንጭ አካለ አእምሮ
@Zephilosophy
@Zephilosophy
4.3K views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ