Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

የሰርጥ አድራሻ: @zephilosophy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18.78K
የሰርጥ መግለጫ

"Strong minds discuss ideas, average minds discuss events, weak minds discuss people."
Rinu Ruzvelt

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-08-19 20:53:00 ስለ ፍቅር

“ሙሉ የሚያደርግህን አትፈልግ ይልቁንም ፣በሙሉ ልብ የሚቀበልህን ምረጥ።” እንደሚመስለኝ፤ ሰዎች ጎዶሎዎች አይደለንም፤ የፍቅር አጋር የምንፈልገው ጎዶሎ ስለሆንን ሳይሆን ልናካፍለው የምንፈልገው ብዙ ፍቅርና ደስታ ስላለን መሆን አለበት። ከጉድለት የሚመመነጭ ፍቅር ከባድ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ እንዲያደርገን ስልጣኑን እና አቅሙን የምንሰጠው ለሌላ ሰው ስለሆነ። ፍቅር ማለት እራሱን የቻለ ጉዞ ነው፤ እንደመዳረሻ ስንቆጥረው ነው ስህተት የሚሆንብን። መንገዱን አብሮን ሊጓዝ የሚወድ ሰው፤ እሱ ይመስለኛል የነፍስ አጋር የሚባለው።

በመውደድና በማፍቅር መካካል ምን ልዩንት አለ? አንድን አበባ ስንወደው ወይም ደስ ሲለን ቀጥፈን እንወስደዋለን፤ ከልብ ስናፈቅረው ግን በመቅጠፍ ፋንታ ባለበት ውሃ እናጠጣዋለን።”- ይህ ነጻ የሚያደርግ አስተሳሰብ ነው። እውነተኛ ፍቅር ማለት ለምንወደው ሰው ሰላምና ደስታ እንዲሁም ነጻነት መታገል ማለት ነው። ፍቅር የወደዱትን የራስ በማደረግ ብቻ ላይ የተመሰረተ አይደለም። ከእውነተኛ ፍቅር ጋር ነጻነት ሁሌም አብሮ አለ። ነጻነት የጎደለው ፍቅር የራስ ወዳድነት ነጸብራቅ ይመስለኛል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.2K views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:11:43 እውነትን ፍለጋ

የሰው ልጅ እውነትን በመሻት ሂደቱ፡ ውስጥ በተለያየ አቅጣጫ ሲያካሄድ የቆየው ውስጣዊና ውጫዊ ጉዞ የታሪኩን እኩሌታ አስቆጥሯል ለማለት ይቻላል፡፡ አንዳንዱ ሀይማኖትንና መንፈሳዊነትን መሰረት በማድረግ፣ ገሚሱ ፍልስፍናን በመንተራስ የተቀረውም ሳይንስን በመሞርኮዝ ሁሉም በየፊናው የህይወትን ትርጓሜ ለመረዳትና በዙሪያው ያለውን እውነታ ለመገንዘብ፣ ግንዛቤውንም በመሰሎቹ ዘንድ ለማስረጽ ታትሯል፡፡ ይህም ሆኖ ሁሉንም ከሚያስማማ፣ በሁሉም ሰው ዘንድ ተቀባይነት ካለው የጋራ ድምዳሜ መድረስ የተሳነው ይመስላል፡፡

በመሆኑም በዚህ የረዥም ዘመን ሂደት እውነት በሶስት መልክ ተተርጉሞ ከሶስት የተለያዩ ድምዳሜዎች ተደርሷል፡፡ አንዳንዶች እውነት ከሁኔቶችና ከሰዎች አመለካከት ጋር የማይለዋወጥ ፍጹም ሀቅ ነው ሲሉ ሌሎች በበኩላቸው እውነት እንደየሰዉ አመለካከትና ግላዊ ስሜት የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ በሶስተኛው ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት ከቶውኑ ሊታወቅ የሚችል አይደለም ከሚል ድምዳሜ ደርሰዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የእውነትን አንጻራዊነትና ፍጹማዊነት በተመለከተ ከሶቅራጥስ ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የማያባራ ሙግት አሁንም መቋጫ ያልተገኘለት ነው፡፡ በርግጥ ብዙዎች ነባር እንጂ አዲስ እውነት የለም እንደሚሉት በዚህ ዘመን ስለ እውነት እንጻራዊነት የሚካሄዱ ሰጣ ገባዎች የጥንቱን መሰረት ያደረጉ ቅጥያዎች ናቸው፡፡


እውነት ከሰው ሰው የሚለያይ አንጻራዊ ክስተት ነው ብለው ከሚያምኑ ጥንታዊ ፈላስፎች ውስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚነሳው የአፕዴራው ሱፊስት ፕይታጎረስ ነው፡፡ የፕይታጎረስ የአንጻራዊነት ድምዳሜ መሰረት ያደረገው የሰው ልጅ ስለ ገሀዱ አለም ያለው እውቀት በህጸጽ የተሞላ መሆኑ ላይ ነው፡፡

ሰው የገሀዱን አለም እውነታዎች መገንዘብ የሚችለው በስሜት ህዋሳቱ አማካኝነት ነው፡፡ ሆኖም የሰው የስሜት ህዋሳት ከሰብአዊ የአፈጣጠር ገደብ አኳያ ነገራትን ሙሉ ለሙሉ መመልከት አይችልም፡፡ ቀጥ ያለ ብረት ውሀ ውስጥ ሆኖ ሲታይ የተጣመመ መስሎ ይገኛል፡፡ የብረቱን መጣመም የሚፈጥረው የሰዎች የእይታ ግድፈት ነው፡፡ ስለሆነም የስሜት ህዋሶቻችን አቅምና ሀያል ነገራትን በትክክል ለመመልከትና ለመገንዘብ የሚያስችል አይደለም፡፡

ነገራትን በትክክል ለመገንዘብ በሚል እሳቤ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የተለያዩ ማሽኖች ቢኖሩም የነገራትን ትክክለኛ ህልውና ለማሳየት ብቁ አይደሉም፡፡ በርግጥ ማይክሮስኮፕና ቴሌስኮፕን የመሳሰሉ በሰው ልጅ የተፈበረኩ የማጉያ መነጽሮች ያለጥርጥር የእይታ አድማሳችንና አቅማችንን ያሰፋሉ፡፡ ድምጽን የሚያጎሉ ድምጽ ማጉያዎች የሰው ልጅ ከመስማት ችሎታው በላቀ እንዲያደምጥ ያስችሉታል፡፡ ይህም ሆኖ እነዚህ ሰው የፈበረካቸው መሳሪያዎች ፍጹምና እንከን የለሽ ባለመሆናቸው የነገራትን እውነተኛ ህልውና በትክክል የሚያመላክቱ አይደሉም፡፡

በመሆኑም የሰው ልጅ በጎዶሎ ሀይሉ ማግኘት የሚችለው እውቀት ጎዶሎ ይሆናል፡፡ የሚያገኘውም እውቀት ሌሎች ከሚያገኙት የተለየ ነው፡፡ ሁለት ሰዎች አንድን እውነት ፍጹመ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሊመለከተ፡ አይችሉም፡፡ በዚህ የተነሳ እውቀት እንደየሰዉ አተያይና ግላዊ ስሜት የሚለያይ ይሆናል:: ለእኔ እውነት የሆነው እውነትነቱ፡ ለእኔ ብቻ ሲሆን ለአንተ እውነት የሆነው እውነትነቱ ላንተ ብቻ ይሆናል፡፡

ከዚህም ባሻገር የሊዮንቲየሙ ጆርጂየስ የፕሮታጎረስን የአንጻራዊነት አስተሳሰብ ይበልጥ በማስፋት ለኒሊዝምና ስኬፕቲዝም እመለካከት መሰረት ጥሏል፡፡ በኒሊዝም አራማጆች ዘንድ እውነት የሚባል ነገር ከነአካቴው የለም፡፡ እውነት የሚለው አስተሳሰብ በራሱ ውሸት ነው፡፡ ፌይራቤንድ እንዳስቀመጠው «ፍጹም የሆነው እውነት ፍጹም የሆነ እውነት አለመኖሩ ብቻ ነው»

ከስኬፕቲክስ ጎራ የሚፈረጁት ደግሞ እውነት የሚባል ነገር ቢኖር እንኳ ማወቅ አይቻልም ባይ ናቸው፡፡ እውነት የሚባል ነገር የለም ቢኖርም እውነትን ማወቅ አይቻልም የሚለው የነጆርጂየስ አመለካከት ፍሬድሪክ ኒቼንም የሚያስማማ ይመስላል፡፡ ኒቼ እውነተኛውን መንገድ አስመልክቶ እንዳስቀመጠው - «እኔ የራሴ የሆነ መንገድ አለኝ፤ አንተም የራስህ መንገድ ይኖርሀል፡፡ ብቸኛውን፣ ትክክለኛውንና እውነተኛውን መንገድ በተመለከተ - የለም»

ከዚህ አመለካከት በመነሳት ጆርጂየስ ሶስት መሰረታዊ መርሆዎችን አስቀምጧል፡፡ አንድ - እውነተኛ ህልውና የለም፡፡ ሁለት - ሊኖር ቢችል እንኳ ሰው እውነታውን ማወቅ አይችልም፡፡ ሶስት - በሆነ አጋጣሚ እውነትን ማወቅ ቢችል እንኳ ያወቀውን ለሌሎች ማሳመን አይችልም፡፡

እነዚህን የኒሊዝምና ስኬፕቲዝም አመለካከቶች አጥብቀው የሚቃረኑ ፈላስፎች በበኩላቸው አመለካከቶቹ በራሳቸው መስፈርት ውድቅ የሚሆኑ፣ እርስ በርሳቸው የሚጻረሩ አመለካከቶች
መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ ምክንያቱም እውነት የሚባል ነገር ከሌለ የኒሊዝም እውነቶችም እውነት አይደሉም ማለት ነው፡፡ ማንኛውንም ነገር ማወቅ አይቻልም ብለን ካሰብን ደግሞ ቢያንስ ማወቅ እንደማይቻል ማወቃችን በራሱ ምን ሊባል ነው?!

ምንጭ- ከፍልስፍና ዓለም
@Zephilosophy
@Zephilosophy
5.0K viewsedited  04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 21:28:39 መዋቲነት- ሃይዲገር

በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ ቀናቶቹ በሙሉ ትርጉም አልባ ናቸው፡፡

ጀርመናዊው የሃያኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ ማርቲን ሃይድገር ይህ ሰው “ሰውነትን” አጥቷል ይልናል። በቀን ውሎህ ውስጥ የምትፈጽመው ነገር አለና ጠዋት ላይ ከአልጋህ በጥድፊያ ተወርዳለህ፤ በጥድፊያ ውስጥ ሆነህ ሁሉ ነገርህን ትከውናለህ። ከእያንዳንዱ ድርጊቶችህ ጀርባ ጊዜ ባላንጣህ ነው።


በተቻለህ አቅምም ጊዜን ለመቅደም ትሮጣለህ፡፡ ሆኖም ጊዜ 'ማያሳስብህ ቢሆን በሕይወትህ ላይ ምን ይፈጠራል? ዘላለም ኗሪ ብትሆን እና ከጊዜ ጋር መሽቀዳደምህን ብታቆምስ?

ሰዎች በዘመናችንን በሙሉ ሙዋቲነታችንን አውቀን እንዳላወቀ ሆነናል። በእርግጠኝነት መጨረሻህ ሞት እንደሆነ ታውቃለህ ፤ ሆኖም ከሟችነት ራስህን ታርቃለህ። ከሞት መሸሺያ መንገዶችንም ትጠቀማለህ። ሲያምህ ሆስፒታል ትሄዳለህ... ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወትን እንደምትኖር ታምናለህ...
ሞትን እንሸሸዋለን፣ እንደበቀዋለንም አንድ ሰው ስለ ሞት ካነሳም “አቦ አታሟርት!” እንለዋለን።

ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም ሃይድገር ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ይለናል፡፡ ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡ አብዛኛው የሕይወት ክፍልህን ብዙ ጉዳዮችን ለመጨረስ ስትራራጥ ታሳልፋለህ ፤ ሆኖም ኢ-መዋቲ ከሆንክ ማርጀትም ሆነሞትና የማያስጨንቅህ ከሆነ ስለምን ከአልጋህ ላይ ትወርዳለህ? ጉዳይህን ጨረስከው ወይም በጅምር ተወከው ምን ለውጥ ያመጣል?

ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ። አይንህን ጨፍንና ዘላለም ኗሪ እንደሆንክ አስብ... ይህ የሰውነት ዓለም አይደለም... በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል። ሰው ይሮጣል፣ ይደክማል፣ ያሸንፋል፣ ይሸነፋል... ሩጫ እና ድካም በሌለበት ዓለም ላይ “ሰውነት” ይታጣል፡፡

ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ለማያልቅ ምግብ የሚስገበገብ ሰው አይኖርም... በወንዝ ውስጥ ያለ አሳም ውሃ ብርቁ አይደለም... ጊዜያችንም ዋጋ ካጣ ለመኖር ያለን ፍላጎት ይረግባል። የሚያኖረን ፍርሃታችን ነው ! የጸሐይ ግብአት ውበት ያለው ከመጥለቋ ላይ ነው፤ የፍቅር ግለቱ ያለው ከማለቁ ላይ ነው ... የእያንዳንዱ ደቂቃ ማለፍ የተሻለ ነገን እንድናልም ምክንያት ይሆነናል፡፡


ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
6.3K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:14:52 ራስን ማታለል (Bad Faith)

በሕይወትህ ለምን ያህል ጊዜ ለውድቀትህ ሌሎች ሰዎችን ወይም ሁነቶችን ወቅሰህ ታውቃለህ? እንዲህ ባይሆን ኖሮ እንዲህ እሆን ነበር' ብለህስ ታውቃለህ? አለቃህ፣ መምህራኖችህ፣ ወላጆችህ የሆነ ነገር እንድታደርግ አስገድደውህ ያውቃሉ?

የሃያኛው ክ/ዘመን ፈላስፋ የሆነው ዣን ፖል ሳርት እነዚህን ሃሳቦች በአንድ ሰብስቦ “bad faith' ብሎ ይጠራቸዋል። ይህም ራስን ማታለልን ያመላክታል። ብዙውን ጊዜ በሕይወት ላይ አማራጭ እንደሌለን ለራሳችን እናሳምነዋለን፡፡ ይህን ያደርግነው እንዲህ ስለሆነ ነው የሚል ምክንያትም ከድርጊቶቻችን ጀርባ እናስቀምጣለን። አሁን ላለንበት ደረጃ ያበቁንን አስገዳጅ ምክንያቶች እና ሰበቦች እንደረድራለን፡፡ ራስን ማታለል በዙሪያችን እስር ቤት የመገንባት ያህል ነው።

ማህበረሰቡ ባስቀመጠልን አስገዳጅ ህጎች አልያም ልማዶች ራሳችንን ወስነን በነጻነት ከመምረጥ እንገደባለን፡፡ ለምሳሌ ሜሴጅ እንደላከልሽ ወዲያውኑ አትመልሽለት” አይነት ተራ ሕጎች ጀምሮ እስከ በዳኛ የተደነገጉ ሕጎች ድረስ - የመምረጥ ነጻነታችን ይገደባል።

እናም ራስን ማታለል (bad faith) የሚጀምረው ለውድቀታችን እነዚህን ህጎች ተጠያቂ ስናደርግና በእነርሱ ውስጥ ስንሸሸግ ነው::

እናም ከማህበረሰቡ ተውስን የምንወስዳቸው ብዙ ጭንብሎች አሉን፡፡ በብዙ የሕይወት ክፍሎቻችን ላይ እንዲህ መሆን አለብህ ስለተባልን ልክ እንደ ተዋናይ ሆነን እንተውናለን፡፡
ነገር ግን ይለናል ሳርት፤ ህግ፣ ደንብ፣ ባህል እና ወዘተ... ከመምረጥ አያግዱንም፡፡ ምርጫዎችን የመምረጥ እና የመወሰን ፈቃዱም በእኛ እጅ ላይ ነው ያለው፡፡

በእያንዳንዷ ቅጽበት፣ በእያንዳንዱ ቀን ምርጫዎች አሉን። በእያንዳንዱ ሰከንድም የወደድነውን የመምረጥ ነጻነት አለን። ይህንን ነፃነት ምንም አይነት ነገር ከእኛ ሊቀማን አይችልም፡፡ ነጻ ለመሆንም የተገባን ነን።

በዚሁ ልክም ለእያንዳንዱ ምርጫዎቻችን ውጤት የምንጠየቀው እኛ ብቻ ነን። ቀድሞውኑ በሚገባ አመዛዝነን ካልወሰንን እና መንገዳችን ወደ መጥፎ መዳረሻ ካደረሰን፣ ከእኛ ውጪ ልንከሰው የሚገባ አካል አይኖርም፡፡ ጥፋታችንንም ከማመን ውጪ ማንም ላይ ማላከክ የለብንም፡፡

ነጻ ነህ ... ነጻነትህን ተጠቅመህ መንገድህን ምረጥ...

ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
8.6K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 21:23:55 መሐል ሰፋሪ- አርስቶትል

ሁላችንም ብንሆን ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ቦታ እና ጊዜ ላይ ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ ሁሌም ቢሆን ምን ማለት እና ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቅ፣ በነውጥ ውስጥ የሚረጋጋ፣ በራሱ የሚተማመን ግን ጉረኛ ያልሆነ መሆን ይቻላልን?

ድፍረቴ መቼ ነው እንደ ሞኝ የሚያስቆጥረኝ? ጦር ሜዳ ሄዶ የተዋደቀም፣ የሚነድ እሳት ውስጥ ዘሎ የገባም ሁለቱም ደፋር ናቸው - አንደኛው ጀግና ሲባል፣ ሌላኛው ሞኝ ይባላል፡፡ መቼስ ነው ትዕግስት እንደ ፍርሃት የሚቆጠረው? የለጋስነት ልክስ የቱ ጋር ነው? መቼ ነው ለጋስ፣
መቼስ ነው አባካኝ የምትባለው? - በሞኝ እና ጀግና፣ በፈሪ እና ትዕግስተኛ፣ በራስ መተማመን እና በጉራ አልያም በለጋስ እና በአባካኝ መሃል ያለው መለያ መስመር የቱ ጋር ነው? . . ..

ለምሳሌ ጨለማ በወረሰው መንገድ ላይ እየሄድክ ሳለ አንድ ሌባ አንዲትን ሴት አስፈራርቶ ሲዘርፋት ተመለከትክ፡፡ እናም ምን ብታደርግ ነው ፈሪ የምትባለው፣ አልያም ምን ብታደርግ ነው ደፋር የምትባለው? ዘራፊው ካንተ የገዘፈ እና በእጁ ጦር መሳሪያን የያዘ ከሆነ ከሴቷ የቀማውን ቦርሳ ለማስመለስ መሞከርህ ሞኝነት ይሆንብሃል። ሸሽቶ መሮጥም አማራጭህ ይሆናል።

ሁላችንም ፍጹም መልካም ሰው መሆን እንፈልጋለን። ሆኖም አርስቶትል የሞራል ልዕልናን መላበስ (virtue) ወይም መልካምነት የሚመጣው መሐል ሰፋሪ ከመሆን ነው ይለናል። የፕሌቶ ተማሪ የሆነው አርስቶትል (Nicomachean Ethics) በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ይህን የመሐከል ስፍራ ወርቃማ አማካይ (Golden mean) ሲል ይጠራዋል፡፡

አርስቶትል ስነ ምግባራዊ ተግባራት (ወይም ትክክለኛውን ነገር ማድረግ) ከሁሉም ነገር መሐል ላይ ከመሆን ይገኛል ይለናል፡፡ አበባ ከመጠን በላይ ውሃን ካጠጣነው ይሞታል። ከመጠንም አሳንሰን ብንሰጠው ይደርቃል። እናም በቂ የሆነ እና ያልበዛ ወይም ያላነስ የውሃ መጠን ለዚህ አበባ መፍካት ያስፈልገዋል፡፡ በሕይወታችንም ውስጥ የሞራል ልዕልናን ለመላበስ ድርጊታችን ልክ ያለው ሊሆን የተገባ ነው። ይህን ልክነት እንዴት ማምጣት እንችላለን?

በልምምድ እና ሌሎች ሰዎችን በመመልከትም ራሳችንን ማሰልጠን እንችላለን። ይቅር ባይ መሆን ትፈልጋለህ? የምታውቀውን ይቅር ባይ ሰው ተመልከት፤ እንደ እርሱም አድርግ፡፡ ደግ መሆንንም ከፈለግክ፣ ደግነትን ደጋግመህ ፈጽም፡፡ አርስቶትል በእጅጉ በሚታወቅበት አባባሉ እንዲህ ይለናል

"We are what we repeatedly do. Excellence, then, is not an act, but a habit.” (እኛ ደጋግመን የምንፈጽመውን ነን። ምርጥነት ተግባር አይደለም፤ ልማድ እንጂ)

አርስቶትል መልካም ተግባራት ከሁለት ተጻራሪ ተግባራት በመካከለኛው ስፍራ ላይ ይገኛሉ ብሎ ይሞግታል። በእጅጉ ያልተትረፈረፈ፣ በእጅጉም ያላነሰ፡፡ ጀግንነት - ከአጉል ድፍረት እና ከቦቅቧቃነት መሐከል ላይ ይገኛል። ልግስና - በስግብግብነት እና ከአባካኝነት መሃል ይገኛል።

ባለ ቅኔው ሄሶድም “በሁሉ ነገሮችህ ላይ የአማካዩን ስፍራ ውሰድ።” ይለናል።

ወርቃማውን የአማካይ ስፍራ ለማግኘት ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር መለማመድ ነው፡፡ ይህን ከልምድ የሚገኝ ጥበብም አርስቶትል "phronesis" ሲል ይጠራዋል። ትክክለኛውን ነገር በትክክለኛው ቦታ እና ትክክለኛው ጊዜ ለመከወን እንደ ስፖርተኛ ልንስለጥን ይገባል።

ምንጭ-ፍልስፍና ከዘርዓ ያዕቆብ እስከ ሶቅራጠስ
ዝግጅት-ፍሉይ አለም

@Zephilosophy
@Zephilosophy
7.0K viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 20:21:10 የታላላቅ ፈላስፎች ሀሳቦች እና አባባሎች
@Zephilosophy

1."ገንዘብ የማይገዛው ነገር እስከሌለህ ድረስ ባለፀጋ አይደለህም።"

2."የሰው ልጅ ነፃ ነኝ ብሎ የሚያምን የልማድ ባሪያ ነው።"

3."ጉድለትህን ወደ ፍፁምነት የሚቀይረው ፤ ፈጣሪህ እንጂ ሀይማኖትህ አይደለም።"

4."የመገለጥን ብርሃን ትጨብጥ ዘንድ የሥጋን ጨለማ አሸንፍ።"

5.እያንዳንዱ ሰው ልክ እንደጨረቃ ነው፡፡ ለማንም የማያሳየው ግማሽ ጎን አለው ።

6."በፍቅር የተሰራ ኃጢያት፤ ፍቅር ከሌለበት አምልኮ ይበልጣል።"

7."ፈላስፋ በሕይወት ጨዋታ ላይ የተገኘ ተመልካች ነው።"

8."የእኔ ፍላጎት የፈጣሪን ሀሳብ ማወቅ ነው ፤ ሌላው ሁሉ ዝርዝር ጉዳይ ነወ።"

9."የምትኖረባትን ሕይወት በቅጡ ሳታውቅ ስትሞት ሌላ ዓለም መኖሩን እንዴት ታውቃለህ።"

10."ታላላቅ እምነቶች ሁሉ መነሻቸው መናፍቅነት ነው።"

11."ያልተመረመረ ህይወት ሊኖሩት የማይገባ ነው። "

12."የእግዚአብሔር ፍቃድና እውቀት በእኛ አላዋቂነት ሊፈተን አይችልም።"

13."ለማመን እንጂ ላለማመን ምክንያት አያስፈልግም።"

14."የሞት ፍርሃት የሕይወት ማጣፈጫ ቅመም ነው።"

15."መልካምነት የተደረገልህን ሳይሆን ያልተደረገልህን የመክፈል ብቃት ነው።"

16."ከፍቅር ሁሉ የሚበልጠው ምላሽ ሳያገኙ ማፍቀር መቻል ነው።"

17."የሰው ልጅ ሐሳብ እንጂ እውነት አትለዋወጥም።"

18."የሰው የነፍስ አርነት በሥጋ ባርነት የሚገኝ ልምምድ ነው።"

19."እኔ የሚል አእምሮ በጨለማ እንዳልተለኮሰ ሻማ ነው።"

20."አዕምሮ እንደፈሳሽ ወንዝ ነው ፤ መገደብ ባትችልም አዲስ መንገድ አብጅለት።"

ምንጭ- ጥበብ ከጲላጦስ

@Zephilosophy
@Zephilosophy
19.8K viewsedited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 16:43:35 አስተሳሰቦችና ፍልስፍናዎች
@Zephilosophy

«ፍቅር ቤቱን የሠራበት ልብ እንዴት የታደለ ነው? ምክንያቱም ከዓለም ጭንቀት ሁሉ መዳኛው ፍቅር ነውና። ፍቅር ትዕግስትና ማመዛዘንን ወደ ምንምነት የሚቀይራቸው የነጐድጓድ ኃይል ነው። አፍቃሪ ስለራሱ ደህንነት ማሰብ አያውቅበትም፤ የትችት ተራራ ለእሱ ከገለባ ክምር የቀለለ ነው። እንዲያውም ትችት የፍቅሩን ኃያልነት የሚጨምርለት ጉልበቱ ይሆናል።»

ሱፊስቶች

«ዓለም በሙሉ ዕብድ ነው ይለኛል። በእርግጥም ዕብድ ነኝ። አናንተም ደግሞ ዕብድ ናችሁ። ዓለም በሙሉ ዕብድ ነው። ለመሆኑ ዕብድ ያልሆነስ ማን ነው? ይሁንና እነዚህ ዕብዶች ደግሞ እኔን ዕብድ በማለት ይጠሩኛል። ከእነሱ አንዳንዶቹ ለስማቸውና ለክብራቸው ያበዱ ናቸው። አንዳንዶቹ ገንዘብ በመከተል አብደዋል። ሌሎቹ ደግሞ ሥጋን ውበትን እየተከተሉ ያብዳሉ። እሱ ፈጣሪውን ተከትሎ ያበደ ግን በእርግጥም የተባረከ ነው። እኔ እንዲህ ዓይነቱ ዕብድ ነኝ።»

ባንግ አቫድሁት

"የሰው ልጅ ምኞት ገደብ የለሽ ነው። ምኞት በጥም የተቃጠለ ሰው የሚጠጣው ጨዋማ ውሃ ነው፤ ጨዋማ ውሃ የውሃ ጥምን አለማርካት ብቻ ሳይሆን ጥሙ እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉ የማይቀር ነውና። ስለዚህም የሰው ልጅ የእርካታ ምንጩ ከውስጡ ነው፤ በምኞቱ ግን አለመርካታ ብቻ ሳይሆን ስቃዩም እየጨመረ ይሄዳል። እናም ለምኞትህ ገደብ አበጅለት"

ሃይዲገር

"ስለሦስተኛው የዓለም ጦርነት አላውቅም፧ ስለአራተኛው ግን ልነግራችሁ እችላለሁ አራተኛው የዓለም ጦርነት ብሎ ነገር የለም፤ ምክንያቱም ሦስተኛው ሁሉን ነገር ይጨርስዋልና!"

አልበር አንስታይን

"ሰው የሚያፈቅረውን ነገር ይሆናል። ድንጋይ ካፈቀረ ድንጋይ ይሆናል፤ የሰውን ልጅ ካፈቀረ ደግሞ ሰው ይሆናል፤ ፈጣሪን ካፈቀረ ደግሞ... ከዚህ በላይ እንኳን ማተት የለብኝም... አለበለዚያ በድንጋይ ልትወግሩኝ ትችላላችሁ።"

ኦውግስቲን

"በሰዎች ክፉ ተግባርም ሆነ ምግባር ለመፍረድ ስንነሳ የእኛም ክፉነት እየተገለጠ ይሄዳል። ለማንኛውም የሰው ልጅ የምግባር በሽታ ጠንካራው መድኃኒት ፍቅር ብቻ ነው»

ራማያና

"የሰው ልጅ የፈጣሪውን ማንነት ተረድቶ በእሱ ማንነት በምድር ላይ ለመመላለስና የእሱንም ዘላለማዊነት ለመልበስ ዋስትና የሚሆነው ሃይማኖቱ ሳይሆን የተሰጠውን ተፈጥሮአዊ ብቃት ለመግለጥ በፈጣሪ መንገድ ላይ መገስገስ ብቻ ነው።።"

ሂንዱይዝም

«ራስን አለማወቅ ይጎዳል፤ ራስን አለማወቅ ሕይወትን በሙሉ ትርጉም አልባ ያደርገዋል። ሁሉን ነገር ልታውቁ ብትችሉ እንኳ ራሳችሁን ግን አላወቃችሁም፤ የሚገርመው ግን ከእውቀታችሁ በፊት ልታውቁት የሚገባው ራሳችሁን ነበር።"

ኦሾ

«አብዛኛው የሰው ልጅ የሚከተላቸው እምነቶችና በእምነቱ ውስጥ የሚፈፅማቸው ድርጊቶች መነሻቸው ልማድ ነው። እምነት በዕውቀት መገለጥን ካልያዘ የሚጠይቀውም ሆነ ምላሽ የሚያገኝለት ጥያቄ ስለማይኖር ሌሎች ስለሚያደርጉት ብቻ የሚደረግ ከንቱ ተግባር ሆኖ ይቀራል።»

ዜኖች

"የሰው ልጅ ሊኖር የሚገባው ዛሬን ነው፤ ስለነገ እያሰቡ ዛሬን መኖር ዛሬ ልንጨብጠው የምንችለውን ነገር ለነገ አሳልፎ የመስጠት ተግባር ይሆናል። ብዙዎች እምነታቸውን በነገ ላይ በማንጠልጠላቸው ምክንያት ዛሬ እምነታቸው ሊሰጣቸው የሚችለውን በረከት እያጡት ይገኛሉ። "

ዜኖች

"ቀላል፣ የተዋበ፣ ፀጥታ የሞላበት፣ ተደሳችና የተባረከ ሕይወት መኖር የምትሻ ከሆነ የአእምሮን ስግብግብ ጥያቄዎች ጣላቸውና በምትካቸው የልብህ መልሶች ተካባቸው። የአእምሮ ጠቢብነት ነገሮችን እያወሳሰበ ዕለት ተዕለት ጥያቄን መከመር ነውና የሕይወትህ ጌታ ልብህን አድርገው። "

ኦሾ

"ፍቅር በውስጥህ ቦታን ሲያገኝ የውበት መገለጫው ትሆናለህ። ፍቅር የያዘው ሰው ውበት የሚንፀባረቅበት መስተዋት ነው። ምክንያቱም ውበትም ሆነ ነፀብራቁ መነሻቸው ፍቅር ነውና... የሁለቱም ምንጭ ፍቅር ነው።"

ሱፊስቶች

#Abel
@Zephilosophy
@Zephilosophy
11.8K views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 16:04:09 ሀገር ማለት ምንድ ነው ?

ዘረኝነት በጨለማ ውስጥ እንደመፋለም ነው።የጨለማ ፍልሚያ ማለት ደግሞ የራስን ወንድም ጭምር ቢሆን እንደመፋለም ነው። ከማን ጋ እየተዋጋን እንደሆነ አንረዳም። ሀገር ሲባል ቋንቋ:ልማድ ወይም እምነት የሚመስለን ሰዎች ፍጹም ስህተት ውስጥ ነን። ዘር ወይም ጎሳ ጭምር ሀገር ማለት አይደሉም ። ባህሎች ናቸው።ሲወርድ ሲዋረድ ከትውልድ ትውልድ በትውፊት የሚሻገሩ እምነቶች ናቸው።
ሀገር ግን ሀሳብ ነው።በውስጡ አላማ አለው።ፍልስፍና አለው።ራዕይ አለው።ዜግነት የሚሰኝ ከጎጥ ውጪ የሆነ ግለሠብነት አለ። የሀገር ምንነት ፍልስፍናዊ ነው። ፍጹም ልማዳዊ መሆን የለበትም።መሆንም አይችልም።ከልማድ የሚነሳ መንግስት የለም።የጎሳ ቲኦክራሲ ልንፈጥር እንችላለን ። ዘመናዊ አለም የሚገዳደር ጠንካራ የመንግስት ይዘት ግን አናገኝም።
ኢትዮጵያን ማሠብ ያለብን ልንፈጥር ከምንችለው አብዮትና አንድ መሠረት ያለው የዜግነት ቅርጽ አንጻር እንጂ በቀበሌ ቋንቋና ትውፊት ላይ የምንተራስ ከሆነ ሀገር የሚለው ቃል አልገባንም ማለት ነው።የተለያዩ ጎሳዎች በሚናገሩት ቋንቋ:እምነት ወይም ልማድ ሀገር የሚለውን ጥልቅ ሀሳብ ሊዳኙ ሲሞክሩ ማየት ተለምዷል።ነውር ነው!! ሀገርና ልማድ የማይለይ ትውልድ ተፈጥሯል ማለት ነው።ልማድ ምክንያት የሌለው የማይለወጥ ግን እንዲሁ በህዝቦች ሽግግር የሚያልፍ ስርዐት ነው።ሀገር ግን ከዚህ ይለያል።በየዘመኑ እያደገ በሚመጣ ፍልስፍና : ርዕዮት አለም ወይም ዕሳቤ የሚጎላበት ትርጉምና ምንነት የሚኖር የብዙ ህዝቦች አንድነት መጠሪያ ነው።

➦መሀመድ አሊ ቡርሀን
➦"የዘር ካርድ"

@Zephilosophy
@Zephilosophy
18.5K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 22:02:18 እውነተኛ እርካታ ያለው ህይወት

ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ( ክሪሽና ሙርቲ)
ተርጓሚ ፦ ተስፋሁን ምትኩ


ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳታደርጉ በፀጥታ ተቀምጣችሁ ታውቃላችሁ? ሞክሩት ጀርባችሁን ቀጥ አድርጋችሁ ተቀመጡና አዕምሯችሁ ምን እንደሚሰራ አስተውሉ፡፡ ልትቆጣጠሩት አትሞክሩ፤ ከአንዱ ሃሳብ ወደሌላው፣ ከአንዱ ፍላጎት ወደሌላው መዝለል የለበትም አትበሉ፤ ዝም ብላችሁ ብቻ አዕምሯችሁ እንዴት እንደሚዘል አስተውሉ። ዝም ብላችሁ አስተውሉት፤ የወንዝ ዳርቻዎች በውስጣቸው የሚያልፈውን ውሀ ዝም ብለው እንደሚመለከቱት ተመልከቱት። በሚወርደው ወንዝ ውስጥ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ - ዓሶች፣ ቅጠሎች፤ የሞቱ እንስሳት - ወንዙ ግን ሁልጊዜ እንደተንቀሳቀሰ ነው:: አዕምሯችሁም ልክ እንደዛ ነው፡፡ ዘላለሙን ዕረፍት የለውም፤ እንደ ቢራቢሮ ከአንዱ ወደ አንዱ ይዘላል፡፡

አንድ ዘፈን ስታደምጡ እንዴት ነው የምታዳምጡት? የሚዘፍነውን ሰው ልትወዱት ትችላላችሁ፣ ፊቱ የሚያምር ይሆናል፤ የሚያወጣቸውን ቃላት ትርጓሜ ትከተሉ ይሆናል፤ ከዚህ ሁሉ ጀርባ ግን አንድ ዘፈን ስታደምጡ ምቶቹን በምቶቹ መካከል የሚገኙትን ፋታዎት ነው የምታዳምጡት፣ አይደለም እንዴ? በተመሳሳይ መልኩ ቁጭ በሉና የትኛውንም አካላችሁን ሳታንቀሳቅሱ አዕምሯችሁን አስተወሉት። እጅግ የሚያስደስት ነገር ነው፡፡ እንደ ጨዋታ፣ እንደ መደሰቻ ነገር ካያችሁት አዕምሯችሁ ምንም ጥረት ሳታደርጉበት ራሱ መረጋጋት ሲጀምር ታዩታላችሁ፡፡ ይሄን ጊዜ ፈራጅ ፣ መዛኝ፣ ፈታሽ አይኖርም፡፡ አዕምሮ በፍፁም ርጋታ ውስጥ ሲሆን ደስታ ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ። ደስታ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ወይ? ሳቅ ነው፤ በሆነ ወይም በምንም ነገር መደሰት ነው፤ የመኖርን አስደሳችነት ማወቅ ነው፤ ፈገግታ ነው፤ ሌላውን ያለ ፍርሃት ፊት ለፊት መመልከት ነው፡፡

የሰው ፊት በፅሞና አይታችሁ ታውቃላችሁ? የመምራችሁን፣ የወላጆቻችሁን፣ የአንድን ትልቅ ባለስልጣን፣ የአንድን ምስኪን ሰራተኛ ፊት አይታችሁ ታውቃላችሁ? አብዛኞቻችን የሌላን ሰዉ ፊት ፊት ለፊት ለማየት እንፈራለን፤ ሌሎችም በዚያ መልኩ እንድናያቸው አይፈልጉም- ምክንያቱም ይፈራሉ፡፡ ማንም ሰው ራሱን ማሳየት አይፈልግም። ሁላችንም ተከልለናል፤ በስቃይ፣ በመከራ፣በናፍቆት፣ በተስፋ መጋረጃዎች ተጋርደናል፡፡ ፊት ለፊት አይተዋችሁ ፈገግ የሚሉ ጥቂቶች ናቸው። ፈገግ ማለት፣ መደሰት በጣም አስፈላጊ ነው - ምክንያቱም በልቡ ዜማ የሌለ ህይወቱ ጨለማ ነው:: አንድ ሰው ከአንድ ቤተ መቅደስ ወደሌላው፣ ከአንዱ ባል ወይም ሚስት ወደሌላው፣ ከአንድ መምህር ወደሌላው መሄድ ይችላል፤ ነገር ግን ውስጣዊ ደስታ ከሌለው ህይወት እምብዛም ትርጉም አትሰጠውም፡፡ ይህን ውስጣዊ ደስታ ማግኘት ቀላል አይደለም- ምክንያቱም አብዛኞቻችን ደስታ የራቀን ከላይ ከላይ ብቻ ነው::

ደስታ ማጣት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ደስታ ማጣትን መረዳት ከባድ ነው - ምክንያቱም አብዛኞቻችን በአንድ አቅጣጫ ወስነን ከልለነዋል። ብቸኛው ትኩረታችን እንዳንረበሽ በደንብ በተደራጁ ፍላጐቶችና ኩራቶች ራሳችንን በአስተማማኝ ሁኔታ ማደራጀት ነው። በመኖሪያ ቤቶችና በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ ነው፡፡ መምህራኑ መረበሽ አይፈልጉም፤ ለዛም ነው አሮጌውን መንገድ የሚጠቀሙት - ምክንያቱም አንዱ እርካታ ባጣ ቅፅበትና መጠየቅ በጀመረ ጊዜ ረብሻ ይኖራል፡፡ ይሁን እንጂ መነሳሳት የሚመጣው እውነተኛ እርካታ በጠፋ ጊዜ ብቻ ነው።

መነሳሳት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አንድ ነገር ያለ ማንም ገፋፊነት ለማድረግ ስትነሱ ተነሳሳችሁ ይባላል፡፡ በኋላ የሚመጣው ነገር በጣም ትልቅ የሆነ ወይም የተለየ ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ችግኝ ስትተክሉ፣ ቀና ሰዎች ስትሆኑ፣ ሸክሙ የከበደው ሰው ስታዩ ፈገግ ስትሉ፣ ከመንገድ ላይ ድንጋይ ስታነሱ ወይም በመንገድ ላይ የምታገኙትን እንስሳ ስትደባብስ ያን ጊዜ የመነሳሳት ፍንጣቂ ይታያል፡፡ ይህን ፈጠራ የሚሉትን ልዩ ነገር ማወቅ ካለባችሁ የግዙፉን መነሳሳት ጅማሮ ልታዩ የግድ ነው፡፡ ጥልቅ የሆነ አለመርካት ሲኖር ብቻ ዕውን በሚሆነው መነሳሳት ውስጥ ፈጠራ ስሮቹን ዘርግቶ ይኖራል፡፡

አለመርካትን አትፍሩት፤ ከዚሀ ይልቅ ፍሙ ነበልባል እስኪሆን ድረስ ተንከባከቡት፡፡ በሁሉም ነገር አትረኩም- በስራችሁ፣ በቤተሰባችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በስልጣናችሁ፣ በሀይላችሁ - ስለዚህም ለማሰብ፣ ለማወቅ፣ ተነሳስታችኋል። በእድሜ እየገፋችሁ ስትሄዱ ግን ይህን የመርካት መንፈስ መቋቋም ፈተና ይሆንባችሗል። ከእናንተ እርዳታ የሚጠብቁ ልጆች አሏችሁ፤ ከፍተኛ የስራ ውጥረት አለባችሁ፤ የጎረቤታችሁ፣ የማህበረሰቡ አስተሳሰብ እየዋጣችሁ ነው፤ እናም ይህ የአለመርካት ስሜት ነበልባል መውጣት ይጀምራል:: ደስታ ሲጠፋችሁ ሬድዮ ትከፍታላችሁ፤ ወደ መምህራችሁ ትሄዳላችሁ፤ ወደ አንድ ቡና ቤት ጎራ በማለት ትጠጣላችሁ፣ ሴቶችን ታሳድዳላችሁ - ያን ነበልባል ለማዳፈን። ነገር ግን ያለዚህ ያለመርካት ነበልባል የፈጠራ መነሻ የሆነው መነሳሳት አይኖራችሁም፡፡ እውነቱን ለማወቅ በተደራጀው ደንብ ላይ ማመፅ ይኖርባችኋል፤ ነገር ግን ወላጆቻችሁ ያላቸው ሃብት ብዙ ሲሆንና መምህራኖቻችሁ ይበልጥ በስራቸው ደስተኞች ሲሆኑ የእናንተን ተቃውሞ የመቀበላቸው ነገር ይቀንሳል፡፡

ፈጠራ ሲባል ዝም ብሎ ስዕል መሳል ወይም ግጥም መፃፍ አይደለም፤ ይህ በራሱ ጥሩ ቢሆንም በራሱ ትንሽ ነው:: አስፈላጊው ነገር ሙሉ በሙሉ እርካታ ማጣት ነው - ምክንያቱም ይህ አይነቱ ምሉዕ የእርካታ እጦት ነው ወደ መነሳሳት የሚወስደው:: መነሳሳት ሲበስል ደግሞ ፈጠራ ይሆናል፡፡ በዚህ መንገድ ብቻ እውነት፣ እግዚአብሔር ይገኛል።

ስለዚህም ማንም ሰው ይህ ምሉዕ የእርካታ እጦት ያስፈልገዋል - ከደስታ ጋር፡፡ ገብቷችኋል? ማንም ሰው በደስታ፣ በሃሴት፣ በፍቅር ሙሉ በሙሉ አለመርካት አለበት፡፡ እርካታ ያጡ አብዛኞቹ ሰዎች በአስፈሪ ሁኔታ የተሰላቹ ናቸው ፤ ሁልጊዜ ይህ ትክክል ነው፣ ይህ ትክክል አይደለም ሲሉ ይነጫነጫሉ፤ ወይም በተሻለ ቦታ መገኘት ነበረብኝ ይላሉ፤ ወይም የአለመርካታቸው ሁኔታ ከላይ ከላይ ስለሆነ ብቻ ሁኔታዎች እንዲለወጡ ይፈልጋሉ፡፡ የእርካታ እጦት የሌለባቸው በሙሉ የሞቱ ናቸው፡

ልጆች ሳላችሁ ማመፅ ከቻላችሁ ስትጎለምሱ አለመርካታችሁን ከደስታና ከታላቅ ፍቅር ጋር ህያው አድርጋችሁ ታቆዩታላችሁ። እናም ያለመርካት ነበልባል እጅግ ልዩ ጠቀሜታ ይኖረዋል- ምክንያቱም አዳዲስ ነገሮችን ይገነባል፣ ይፈጥራል፤ ህያው ያደርጋል። ስለዚህም ትክከለኛ ትምህርት ያስፈልጋችኋል- አንድ ስራ እንድታገኙ፤ ወይም የስኬትን መሰላል እንድትወጡ የሚያዘጋጃችሁ ሳይሆን እንድታስቡ የሚያግዛችሁና ቦታ የሚሰጣችሁ- አንድ ትልቅ መኝታ ቤት የሚያክል ወይም ጣራው ከፍ ያለ ክፍል የሚመስል ቦታ ሳይሆን አዕምሯችሁ በማህረሰብ ወይ በማንኛውም አይነት ፍርሃት ውሱን እንዳይሆን በደንብ የሚያንቀሳቅሰው ቦታ ያስፈልጋችዋል።

@Zephilosophy
@Zephilosophy
7.8K viewsedited  19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ