Get Mystery Box with random crypto!

Yismake Worku

የቴሌግራም ቻናል አርማ yismakeworku — Yismake Worku Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yismakeworku — Yismake Worku
የሰርጥ አድራሻ: @yismakeworku
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ እኔ . . .

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-05-15 12:19:27
10.8K views09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 20:20:56
18.4K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 14:03:28
እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን
#ሼር

@yismakeworku
15.2K views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 15:21:09
ኪርያላይሶን

ይብላኝ ለኔ ፣ ለሰነፍኩት።
#ሼር
@yismakeworku
16.1K viewsedited  12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 21:23:25
“አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድሃለሁ።”
— መዝሙር 17፥1
ሕማማቱን እንዴት እያሳለፍን ነው?
#ሼር
@yismakeworku
12.4K viewsedited  18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 13:37:06
ለዚህ ብዙዎች ለሚባርቁበት ዘመን፣ አንተ ተፈጥረሃል:: ታምራት ነገራ! ( ዕወቀው ንገረው) ማለት ይሆን ትርጉሙ? ... ለነዚህ ለዛ ቢሶች ደዌዎች እንደዚህ ይሻላልን?
@yismakeworku
14.3K views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 08:05:39 "ፌስቡክ" በሚለው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ "ሚካኤል አዝመራው" የሚባል ደራሲ አለ። ፅሁፎቹ ደስ ይላሉ። እነሆ አንዱን ልጋብዛችሁ . . .

- - -

መንገድ ላይ የጀበና ቡና የምትሸጥ ሴት ማፍቀርኮ ችግር የለውም። ችግሩ ፉክክርህ ከግንበኛ፣ ከተራ አስከባሪ፣ ከአናፂ ምናምን ጋር ነው።

የማስተርስ ዲግሪ ሰርቼ...ስምንት አመት ሙሉ የባንክ ስራን ቀጥቅጨ...ያሰብኩትን ሁሉ ጨብጬ...የአልማዝ ልብ ግን ከመንገድ ወያላዎች ለይቶ አያዬኝም።

"የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው" የሚለው የእማዬ ምክር እዚህ ላይ አይሰራም። በኑሮ ሰባት እጥፍ የምበልጣቸውን ሰዎች በምላስም በልጨ መገኘት አለብኝ። ችግሩ መሰሎቼ ስላልሆኑ ያ ባለጌ ሽመልስ እንደ ኮሜዲያን የሚታይበት ዳስ ውስጥ የኔ ቀልድ እጅ እጅ ይላቸዋል። አንዳንዶቹማ እያወራሁ በፈጠጣው አቋርጠውኝ ሁላ ሌላ ወሬ ይጀምራሉ። ሽመልስ ማውራት ሲጀምር ግን አልሚ ራሱ ቡና መቅዳቷን ቆም ታደርጋለች (ስትስቅ እንዳያስደፋት መሆኑ ነው። ገና ሲጀምር እንደሚያስቃት እርግጠኛ ነች።) እኔ በበኩሌ ከሚያሰቀው ነገሩ ብልግናው ስለሚበዛብኝ ሁሌ እንደተሸማቀኩ ነው።

<<አባቴ 'ሽመልስ' ያለኝ ከበቶቼን የሚጠብቅ እረኛ ተወለደልኝ ብሎ ነው። እኔ ደግሞ የህይወቴ ጥሪ ከዚህም በላይ ነው ብዬ ጠፍቼ መጣሁ። እረኝነት እጣፈንታዬ እንደሆነ የገባኝ ግን እዚህም መጥቼ መኪና ሳግድ ነው!>>
<<ታዲያ የትኛው ተሻለህ...የከተማው ወይስ የገጠሩ እረኝነት?>> ይለዋል አንዱ ሰው መስሎት።
<<ተመልሼ መግቢያ የለኝም እንጂ የገጠሩ ይሻለኝ ነበር። እዛኮ ቢያንስ ሲደብረኝ አህያ እበ*ለሁ!>> ብሎ በሰላሳ አመት የሰበሰብነውን ቀልብ ይገፈዋል።

የፈለገው እንስሳ ጋር ሴክስ ማድረግ ይችላል...እሱ የኔ ጉዳይ አይደለም። ችግሩ ምንም የመጀናጀኛ አየር እየሰጠኝ አይደለም። እሱ ባለበት አይደለም መጀንጀን ወሬ መጨረስ ራሱ አልቻልኩም።

<<ባለፈው መኪናዬ ስታክ አድርጋብኝ...>> ብዬ ስጀምር
<<አይይ!... አሁን እዚህ ማን ስለመኪና ያውቃል ብለህ ነው?>> ብሎ ያናጥበኛል።
<<የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ።>> ብዬ ረጅም ሳክስ ስጀምር
<<ቡና በስኳር እየጠጣህ የተፈጥሮ አድናቂ ነኝ ብትለኝ አላምንህም>> ብሎ ባጭሩ ይቀጨኛል።

አሁን አሁን ገና ከሩቅ ሳዬው እንደ ስፔን ኮርማ ተንደርድሬ ልወጋው ሁሉ ያምረኛል። ወዲያው ከሀሳቤ ብንን ስል ፍቅር የት ድረስ እንዳወረደኝ አስብና እገረማለሁ።

እንዲህ አብሮ መዋል ሳያናንቀን በፊት በፊት ሽመልስ ይመቸኝ ነበር። መኪናዬን ይዤ ስመጣ ቆንጆ የፓርኪንግ ስፓት እንዳገኝ ይረዳኛል።
የሆነ ቀን ከመኪናዬ ሳልወርድ <<እስኪ ቡና እዘዝልኝ>> አልኩት። አንዲት ቀይ ልጅ የጀበና ቡና ይዛ መጣች። ከቡናዋ ጋር ምን እንዳቀመሰችኝ አላውቅም ከዛ ቡኃላ ልክ አይደለሁም።

ፈገግ ስትል ብቅ የሚለው የተነቀሰ ድዷ አብስትራክት ስዕል ይመስል በየ ደቂቃው የአንገቴን አቅጣጫ እየቀየርኩ አየዋለሁ። ፓንቷ ውስጥ ሻጥ አድርጋው የምትሔደው ሺቲ በተንቀሳቀሰች ቁጥር በዳሌዋ ሲያስገለምጠን ይውላል። ስትስቅ ድዷ...ስትራመድ ዳሌዋ! እህህ ሁኗል የኔ ኑሮ!

ታዲያ እኔ እሷን...እሷ ደግሞ ሽመልስን እንደምትወድ ለመረዳት ብዙ አልፈጀብኝም። በብልግና ቀልዱ መሳቅ ብቻ አይደለም...ጭራሽ <<ብልግናቸውን የማይደብቁ ሰዎች ጨዋ ነው የሚመስሉኝ>> ብላ ልትደግፈው ትሞክራለች። ፍቅር የሚባለው የበሽታ አይነት ሲይዝ መጀመሪያ የሚያጠቃው መለኪያ ሚዛንህን ሳይሆን አይቀርም። ለኔ አልማዝን አለም ላይ የትም መገኘት የማትችል እንቁ አድርጎ ያሳዬኛል። ለሷ ደግሞ ሽመልስን አርብ ሮብ የሚፆም ጨዋ አድርጎ ያሳያታል።

ቢሆንም...ቢሆንም! እሷን የመጥበስ እድሌ ተንጠፍጥፎ እንዳላለቀ ይሰማኛል።

አንድ ጧት እንደመጣሁ አምስት መቶ ብር የሻይ ሰጠሁትና ራቅ ወዳለ ሰፈር ላኩት። አልሚን ብቻዋን አገኘኋት።

<<የሆነ ቆንጆ ሬስቶራንት አለ። ዛሬ የሚመችሽ ከሆነ ራት ልጋብዝሽ!>> አልኳት...ስለማመድ የዋልኩት ይሔ መሆኑን ለራሴም ማመን እያቃተኝ።
<<ውይ ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዛሬ አክሴቴ ከገጠር ትመጣብኛለች። ወይ ሌላ ቀን እናድርገው?>>
<<ኧረ ችግር የለውም። ያን ያህል አንገብጋቢ ነገር አስመሰልሺውኮ!>> ከረባቴን አላላሁትና መልሼ አጠበኩት። ተነስቼ ወጣሁ። ደሜ ፈልቷል። ውስጤ አላመናትም።

ሽመልስ እንደመጣ <<ዛሬ የት ነህ? ከስራ ስወጣ ለምን አንድ ሁለት እንልም?>> አልኩት።
<<ውይ በጣም ደስ ይለኝ ነበር። ግን ዝናቡን እንደምመጣ ቃል ገብቼለታለሁ!>> አለ የሰጠሁትን ብር አገላብጦ እያዬ!

አያውቅም ብሎ ስም እየፈጠረ እንደሆነ ገብቶኛል።

<<ዝናቡ ዝናቡ?>>
<<ዝናቡ ይሔ ባለፈው 'ቶሎ ባይነሳ አፉ ላይ ያለው የጠጅ ሽታ ሊያሰክረኝ ነበር' ብለህ የቀለድክበት>>
እውነት ለመናገር ሊያስመልሰኝ ነው የነበረው።
<<አስታወስኩት! ታዲያ ለምን እኔ እናንተ ጋር አልመጣም?>>
<<ኧረ አይሆንህም!>>
<<ግዴለም! ይልቅ ቆንጆ ጠጅ ቤት ውሰዱኝ!>> ሳይመልስልኝ ጥዬው ገባሁ።

ከስራ እንደወጣሁ ባኮረፈ ፊት ይዞኝ መሔድ ጀመረ። ጠጅ ቤት ከገባን ቡኃላ ከሁሉም ተነጥለን የራሳችንን ወሬ ለመጀመር ሁለት ብርሌ ነው የፈጀብን። ያለ ሰበብ እንዳልመጣሁ ገብቶታል።

<<አልሚን ትወዳታለሀ?>> አለኝ ሌሎች እንዳይሰሙን እየተጠነቀቀ!

በጥያቄው አልተገረምኩም።

<<ፍቅር የሰው ልክ አያውቅም ወዳጄ። ያንንም ያንንም ሲጨብጥበት በቆየበት እጁ ነው የሚጨብጥህ! መጨበጡን እንጂ ማንን እንደጨበጠ አያውቅም። እውር ነው። የሚመመራን ግን እሱ ነው። የምለው ገብቶሀላ?>>

<<ይሔ ቢገባኝ የመኪና እረኛ ሁኜ እቀር ነበር ብለህ ነው?>>
<<ልልህ የፈለኩት ፍቅር ደረጃ የማይለያይ ደጋሽ ነው። የመኪናውን ባለቤት ከመኪናው እረኛ ጋር ጠጅ ያስጠጣል!>>

ፈገግ አለ።

<<ተውልኝ ልትለኝ እንደመጣህ ገብቶኛል። እኔም ልልህ ነበር።>>
<<እና ለምን አላልከኝም?>>
<<ትርፉ ድካም ነው። እሷ የምትወደው አንተን!...ለምን ጊዜዬን አባክናለሁ?!>>
ከስካሬ ነቃ አልኩ።
<<እኔን እንዳጫዋች ነው የምታዬኝ። አንተ ስትመጣ ግን ያለባህሪዋ ቆጠብ ትላለች። እንድትወዳት ለማድረግ ትጥራለች። እኔ ምንም አይነት ሰው ብሆን ለሷ አይን አልሞላም።>> እንባ አቀረረ።

ይሔን ንግግር እኔ ቀድሜው ባለማለቴ ደስ አለኝ።

<<ይገባኛል ስሜትህ>> አልኩት ውስጤ እየተፍነከነከ። ፊቴን ያዘንኩ ላስመስል ሞከርኩ ግን አልቻልኩም። የሚታየኝ የአልሚ ቀሚስ ውስጥ ገብቼ አሸሸ ገዳሜ ስል ነው።
ወዲያው ጥግ ላይ የነበረው ዝናቡ እየተንገዳገደ ተነስቶ ወደኛ መጣ። <<አንድ ሁለት መቶ ብር አላችሁ አንዴ?>> አለን
<<ለምንህ?>>
<<አሁን አይደል እንዴ ትዝ የሚለኝ? ለካስ ያቺን ቅንዝራም አልማዝን ቀጥሬያታለሁ! ህእ!>>
ሁለታችንም ደንዝዘን ቀረን። ደመናውን ሳናዬው ዝናቡ ከዬት መጣ? ሰማይ ሳያስገመግም መብረቁ እንዴት መታን?

ብሩን ተቀብሎን ሲወጣ ባለማመን እናየዋለን። በሩ ላይ ሲደርስ ዞር ብሎ <<ጠጅ እስቀምጡልኝ! ጠቅ ጠቅ አድርጊያት እመለሳለሁ>> አለንና በሁለቱም አይኑ ጠቀሰን። በህመም ስሜት አይናችንን ጨፈንን። "የሴት ልጅን ልብ የሚያሸንፈው ያልተጫወተ ነው!"

@yismakeworku
15.2K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 13:00:56
መሆን ከተመኘህ ፣ ዛፍነትን ምረጥ
ቆርጠዉህ ሲሄዱ ፣ ሺ ሆነህ አቆጥቁጥ

(ይስማዕከ ወርቁ)
@yismakeworku
12.8K views10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ