Get Mystery Box with random crypto!

☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

የቴሌግራም ቻናል አርማ yezelalemhiywet — ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE
የቴሌግራም ቻናል አርማ yezelalemhiywet — ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE
የሰርጥ አድራሻ: @yezelalemhiywet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

🔊ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል
እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤|1ኛ ዮሐ 1፥2
🔊ሕይወት ከሞት በኃላ ከጌታ ጋር ይቀጥላል፡፡ቻናሉ የተከፈተው ሰዎች በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን ሕይወት እንዲካፈሉና የቃሉን እውነት ተምረው አርነት እንዲወጡ ነው፡፡You can contact me📲 @YesZoelife

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 07:41:51 የዘላለም✞ሕይወት||ETERNAL LIFE pinned « __ለምን ግን በመጽሐፍ ቅዱሳች ዘሌዋውያን ላይ ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ እግዚአብሔር ለሙሴ የተናገረው ሙሴም ለእስራኤል ሴቶች እንዲናገር የታዘዘው ቃል አለ፡፡ቃሉም እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡፡እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ሴት ብታረግዝ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረከሰች ናት፤ እንደ ሕመምዋ መርገም ወራት ትረክሳለች፡፡ በስምንተኛውም…»
04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:34:13
ሰይጣን በጣም ብልጥ ነው።ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን ድነት አምነው እንዳይቀበሉ እድሜ ልካቸውን በኃይማኖት እየተከራከሩ እንዲኖሩ እውነትም ሳያውቁ እንዲሞቱ ይፈልጋል።በመጽሐፍ የተጻፈውን ጭምር ወደ ጎን በመተው ያልተጻፈን ሐሰት እውነት ነው ተብሎ ርዕስ ተበጅቶለት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ብዙዎች ጊዜአቸውን በክርክር በማሳለፍ እግዚአብሔር የሰጣቸውን እድል ሳይጠቀሙ አልፈዋል።ያስታረቃቸውን ጌታ እርሱ አስታራቂ አይደለም ፈራጅ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ሳይታረቁ ሲሞቱ ያሳዝናል።ፍራጅ ብቻ እንደሆነ ስላመኑ ተፈረደባቸው።አማላጅም እንደሆነ ቢያምኑ ከፍርድ ባመለጡ ነበር።ሁለት አማላጅ የላከ እንዳይመስልህ አንድ ነው እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ኢየሱስ ፈራጅ ነው ሲባል አሜን ብለህ አማላጅም ጭምር ነው ስትባል ግን እንዴት ትላለህ? እንዴት ፈራጅም አማላጅም ይሆናል? ካልከኝ፥ መልሱ ልክ አንዱ ኢየሱስ ሰውም አምላክም እንደሆነው ነዋ።አንተ ያልተጻፈን ሐሰት ይዘህ ባይጻፍም እስኪ አታማልድም የሚል ጥቅስ አሳየኝ በማለት እውነት ላይ ውሃ ቸለስ በማድረግ እውነትን ለመሸፈን መሞከር ነውር ነው።መጽሐፍ ኢየሱስ ያማልዳል ሲልህ እስኪ ድንግል አታማልድም የሚል አሳየኝ ማለት ምን ማለት ነው!? እንደዛ ካልክ እኔም እይዲህ ልበላ፤ ጼጥሮስ አማላጅ ነው።መጽሐፍ እኮ አማላጅ ኢየሱስ እንደሆነ ነው የሚናገረው፥ ቢናገርም እስኪ ጼጥሮስ አያማልድም የሚል ጥቅስ አሳየኝ? ታሳየኛለህ? ጴጥሮስ አያማልድም የሚል!? አንዱ ከመሬት ተነስቶ እኔ አማላጅ ነኝ አለ።እረ አይደልህም ብንለውና እርሱም እስኪ እኔ አማላጅ እንዳልሆንኩ ጥቅስ አሳዩኝ ስላለን እርሱ አማላጅ ነውን? ጥርት ያለ የተጻፈለት አማላጅ ኢየሱስ።ተጫማሪ ሮሜ
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
1.4K viewsedited  10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:55:20 #እግዚአብሔር ወደ ሰው
ሰውም ወደ እግዚአብሔር ማየት እንዲችሉ፤ ከሦላሴ መሐል እግዚአብሔርና ሰው ሆነ ቃሉ፡፡አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤1ኛ ጢሞ 2፥5
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
264 viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:14:00 የቀጠለ:ቆጣሪው ብዙ ኃይል ተጠቅማችዋል ብዙ ክፍያ ይሆንባችዋል ብሎ መቁጠር አያቆምም።በተጠቀማችሁበት ልክ ሒሳብ ይወራረድባችዋል።ሕግም ልክ እንደዚህ ነው።ለአዳም አንድ ሕግ ከተሰጠው በኃላ እስከ ሙሴ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ሕግ አልተሰጠም ነበር።በሙሴ ጊዜ አስርቱ ሕግጋት መጡ።እነዚህ ሕጎች ከሙሴ በፊት አይታወቁም አልመጡም ነበር።አትግደል አትስረቅ ወዘተ የሚሉት ሕጎች የመጡት ከሙሴ በኃላ ከሙሴ በፊት አልነበሩም።ቃየን አቤልን ከገደለው በኃላ እግዚአብሔር አቤል የታል ሲለው ቃየን ቀለል አድርጎ እኔ የአቤል ጠበቃ ነኝ እንዴ አላውቅም የት እንዳለ ብሎ የመለሰው።መግደል ኃጢአት እንደሆነ መቆጠር የጀመረው ከሙሴ በኃላ ነው።

እንድያውም ሰዎች ቃየን አቤልን ስለገደለ ብለው ሊገድሉን ሲያሴሩ እግዚአብሔር በቃየን ግንባር ማንም እንዳይገድለው ምልክት አደረገበት።ቃየን አቤልን የገደለው ኃጢአት በአለም ስለነበር ነው።ያ ኃጢአት ግን ሕግ እስኪመጣ ድረስ አይቆጠርም ነበር።የሚቆጥር ሕግ በዛን ጊዜ ስላልመጣ።ቃየን በአለም የነበረውን ኃጢአት ነበር በወንድሙ ላይ የፈፀመው ነገር ግን እርሱ ላደረገው ኃጢአት የሚቆጥር ሕግ አልነበረም።ሕግ ካልነበረ ደግሞ ሮሜ እንደሚለው ኃጢአት አይቆጠርም ነበር።ነገር ግን ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የነበሩ ሰዎች ኃጢአት ባይሰሩም ሞት በእነርሱ ላይ ነግሦ ነበር።ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።ሮሜ 5፥14

ሕግ ስላልነበር ተብሎ እስከ ሙሴ ያሉ ሰዎች ኃጢአት እንኳን ባይሰሩ እንኳን በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአትን ማድረግ የሚችል ማንነት ወርሰዋልና በእርሱ መተላለፍ ምክንያት የተቆጠረው ኃጢአት ሰለባ ሁነዋል።ከሙሴ በኃላ ግን ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራ ኃጢአቱ ይቆጠርበታል።የሚቆጥር ሕግ ስለመጣ።በሙሴ ጊዜ እንደ ቃየን ሰውን እገድላለው የሚል ሰው ተወግሮ እራሱም ይሞታል።ምክንያቱም ከሙሴ በኃላ ሁሉም ሕጎች ስለመጡ።አንዳንድ ሰዎች ሕግን እንደማጽደቅያ ያስቡታል።ሕግ ለአንዳንድ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማስገብያ መንገድም አድርገው ይቆጡሩታል።ሕጉ ደግሞ በተዘዋዋሪ እነርሱ የሚሰሩትን ኃጢአት አንድ ሳያስቀር ሳይሸፍን ይቆጥርባችዋል።ይገርማል! ያጸድቀናል ያሉት ሕግ፥ የሚሰሩትን ኃጢአት እየቆጠረ ሲያስቀምጥ!?

በቤታችሁ ያለው የመብራት ቆጣሪ፥ መብራት ከተጠቀማችሁ በኃላ ቆጣሪው እንደማይራራላችሁ ሁሉ፥ ያጸድቀኛል የምትሉት ሕግም ኃጢአት ስታደርጉ ከመቁጠር ወደ ኃላ አይልም።ስለዚህ ሕግ አፅዳቂ ሳይሆን ኃጢአት የሚያደርጉትን ሰዎች ኃጢአታቸውን የሚቆጥር ነው።ታድያ የሚያፀድቀው ማነው? እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።ሮሜ 5፥18-21
Contact @eternallife12
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
1.3K viewsedited  09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 12:12:12 ሕ-ግ

ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤ ሮም 5፥12 ሰሞኑን ሮሜ ሳነብ በጣም ከደነቅኝ ቃል ይሄ ነው።ኃጢአት ሕግ ሳይመጣ በፊት በዓለም ነበር።ነገር ግን ያ ኃጢአት አይቆጠርም ነበር።አዳምና ሔዋን በምድር በገነት በጽድቅ ሲኖሩ ሳለ፥ ኃጢአት ደግሞ በአለም ነበር።ኃጢአት ወደ ሰው ልጅ የገባው አትብሉ የተባሉት ፍሬ የበሉ ዕለት ነው።ይሁን እንጂ፥ ከዛ በፊት ኃጢአት በአለም ነበር።ወደ ኤዴን ገነት በእባብ ተመስሎ ቢገባም፥ ከመግባቱ በፊትም ነበር።መቆጠር የጀመረው ግን ሕግ ከመጣ በኃላ ነው።ምክንያቱም ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም ነበርና።

አንድ ሕግ በገነት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ልጅ መጣ።ከዚህ የፍሬ ዛፍ እንዳትበሉ በበላችሁ ጊዜ የሞት ሞትን ትሞታላችሁ የሚል ሕግ።ሕግ ከመጣ በአለም የነበረ ኃጢአት ሊቆጠር ግድ ነው።የሰው ልጅም በአለም የነበረውን ኃጢአት ይሻለኛል በማለት እግዚአብሔር የሰጠውን ሕግ ከመፈጸም ይልቅ ያልተቆጠረውን ኃጢአት ወደራሱ በማስገባት አስቆጠረው።ኃጢአት ወደ ሰው ልጅ ገባ፥ ያ ኃጢአትም ተቆጠረ።ምክያቱም አንድ ሕግ ስለነበር።"አትብሉ" የሚል።ኃጢአት መቆጠር ሲጀምር፥ ለተቆጠረው ኃጢአት ቅጣት ያስፈልገዋልና የሰው ልጅ ከኤደን ገነት እንዲባረር ተደረገ።በነገራችን ላይ አዳም እንደ ሰይጣን ከሰማይ ወደምድር አልተጣለም።ሰይጣን ኃጢአት ካደረገ በኃላ ወደምድር ነው የተጣለው።ምክንያቱም ይኖር የነበረው በሰማይ ስለነበር።

የሰው ልጅ ግን ኃጢአት ከሰራ በኃላ ከኤደን ገነት ነው የተባረረው።አልተጣለም።ምክንያቱም ይኖር የነበረው በምድር ስለሆነ።ሕግ የኃጢአት ቆጣሪ ነው።ምን ማለት መሰላችሁ፤ እናንተ ቤት የምትጠቀሙት የመብራት አገልግሎት ቆጣሪ ከሌለው መብራት ሃይል የሚሰሩ ሰዎች እናንተ ምን ያህል መብራት እንደተጠቀማችሁ፣ ምን ያህል ኃይል ለተለያዩ አገልግሎቶች እንደዋሉ ማወቅ ያዳግታችዋል።የተጠቀማችሁበት መጠን ካላወቁ ሒሳብ አስልተው እናንተን ለማስከፈል ያስቸግራችዋል።እንድያውም እናንተ ምንም አልተጠቅምን ብትሉ እራሱ ተጠቅማችዋል ብለው ሊከራከርዋችሁ አይችሉም ምክንያቱም እንደተጠቀማችሁ ማሳየት የሚችለው ቆጣሪ እናንተ ስላላስገባችሁ።እነርሱም በቀላሉ ምን ያክል ኃይል እንደተጠቀማችሁ የሚያሳይ ቆጣሪ ስላልገጠሙላችሁ።

ሕግም አለ ቃሉ፥ ልክ እንደ ቆጣሪ ነው።ኃጢአት በአለም ነበር ነገር ግን አይቆጠርም ነበር።የሚቆጥረው ሕግ ስላልመጣ።መብራት ኃይል ቆጣሪ በቤታችሁ ከገጠሙ በኃላ የምትጠቀሙበት መብራት መቆጠር ይጀምራል።ቆጣሪ ሳይመጣ በፊት ግን የምትጠቀሙት መብራት አይቆጠርም ነበር።ሕግም ሳይመጣ በፊት ኃጢአት በአለም ሳለ አይቆጠርም ነበር።ቆጣሪ ከተገጠመ ማንም ሰው መብራት ኃይልን ማጭበርበር ሆነ መሸወድ አይችልም።ሰዎች ቆጣሪ እያለ ምንም ያክል የኃይል አገልግሎት ቢጠቀሙ ቆጣሪው ከመቁጠር ወደኃላ አይልም።በዛው ልክ ትንሽ የኃይል አገልግሎት ቢጠቀሙም ቆጣሪው አሁንም ከመቁጠር ወደኃላ አይልም።

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
1.1K viewsedited  09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 00:41:19 ኢየሱስ ሊመጣ ነው ንቁ! እንንቃ! እንዘጋጅ።
406 views21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:39:56 የዘላለም✞ሕይወት||ETERNAL LIFE pinned an audio file
18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 14:50:46
አንዱ ምን አለ መሰላችሁ ሕይወት በB ተጀምራ በD ታቆማለች፥ ማለትም ሕይወት Birth(በመወለድ) ትጀመርና Die(በሞት) ትጠናቀቃለች።ነገር ግን አለ በመካከለቸው C አለች።እርሷም Choice(ምርጫ) ነች አለ።የዚህ ምድር ሕይወት በመወለድ ጀምሮ ከዛን ሰው ያዋጣኛል ያለው በመምረጥ በስተመጨረሻም የስጋን ሞት ይላበሳል።እኔ ደግሞ አንድ ነገር ልጨምር ፈለኩ፥ ሕይወት በD ብቻ አያበቃም አልኩ።ሕይወት ከD በኃላ በE(Eternal) ይቀጥላል።በመወለድ የጀመረ ሕይወት በመምረጥ ይቆይና በመሞት የምድራዊው ሕይወት ያበቃና በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት ይቀጥላል አልኩ።ከላይ የምትመለከትዋቸው ሶስት ሰዎች አሁን በገሃዱ ዓለም በዚህ ማንነት እየኖሩ ያሉ ናቸው።ከሶስተኛው ሰው ስንጀምር፥ በሕይወት በምድር ሳለ በስጋ ብሞት ሲዖል እገባለው ብሎ የሚኖር ሰው ነው።ይሄ ሰው ከቤተሰብቹ የወረሰው ሃይማኖት አለ፤ ነገር ግን ሃይማኖቱ የሚነግረው ኃጢአተኛ እንደሆነ ለመዳንም ብዙ ሥራ መስራት እንዳለበት፥ የምትድነው ሕግን ሁሉ አንዳች ሳታጓድል ስትጠብቅ ነው ይለዋል።በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን ጽድቅ አምኖ መቀበል ያቃተው፣ ኢየሱስ የከፈለው ዋጋ በቂ አይደለም የእኔም ይጨመርበት የሚል፥ ነገር ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ እንደማይችል ስለሚያውቅ መጨረሻውን ያስቀመጠ ሰው ነው።ሁለተኛው ሰው ቢሞት የት እንደሚገባ የማያውቅ ከሞተ በኃላ የሕይወት ምርጫ ያለ የሚመስለው ልክ በስጋ ስሞት ሥራየ ታይቶ ነው ገነት or ሲዖል ግባ የምባለው ብሎ የሚያምን ነው።አንደኛው ግን ከሁለቱም ሰዎች የተለየ ነው።ገና ሳይሞት የመንግስቱ ወራሽ እንደሆነና ጽድቅን በልጁ በማመን እንዳገኘ የሚያምን መሆኑ ነው።ይሄን ያመነው ታድያ ገና በምድር በሕይወት ሳለ ባነበበው ቃል ነው።ታድያ እናንተ ከሶስቱ ሰዎች የትኞቹ ናችሁ?
@Yezelalemhiywet
2.5K viewsedited  11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 09:02:55 ኢየሱስ ለእናንተ ከሞተ፥ እናንተም ለእርሱ ኑሩ።
516 viewsedited  06:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 12:45:48
በልጆች መዳንና መነጠቅ ጉዳይ ልጆች ከአማኝ ቤተሰቦቻቸው ጋር ይነጠቃሉ ወይስ አይነጠቁም? ልጆች ክፉና ደጉን ሳያውቁ ቢሞቱ መንግስተ ሰማይ ይገባሉ ወይስ አይገቡም? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነጠቁና መንግስቱን እንደሚወርሱ ይናገራል።እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና፦ ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው።ማርቆስ 10፥13-15 በማለት ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደሚገቡ ይናገራል።በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈው የታላቁ ትዕዛዝ ላይ ጌታ ያለው የፍርድ ነገር ሕፃናትን አይመለከትም።ወደ አለም ሁሉ ሂዲ ወይጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል።በማያምን ሰው ላይ የገኃንም ፍርድ አለበት።ጥያቄው ሕፃናት ክፉና ደጉን ወደ መለየት እስኪደርሱ ድረስ በአይናቸው የማያዩት የማይዳስሱት ነገር አለ ብለው ሊያምኑ ይችላሉን? በፍጹም አይችሉም።ምንም እንኳን ሕፃናት እንደአዋቂዎች ጆሮ ቢኖራቸውም የሚሰሙት ነገር አመዛዝነው ውሸትና እውነቱን መለየት የሚያስችል ብስለት ሰለማይኖራቸው እምነት ስለሚባለው ነገር አይገባቸውም።ስለዚህ ሕፃናት አድገው ወደማስተዋል ደረጃ እስኪደርሱ ሳያምኑ ቢሞቱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ይገባሉ፤ በንጥቀት ጊዜም ይነጠቃሉ።አንድ ልጅ ክፉና ደጉን ወደማወቅ ደረጃ ቢደርስ ለሚሠራው ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናል።እድሜው ስለደረሰም ለሰራው ኃጢአት በወንጌል በማመን ንሰሐ በመግባት ድነትን ያገኛል።ነገር ግን እስከዚያ የዕድሜ ክልል ድረስ ባለው ጊዜ ቢሞት ወይም ንጥቀት ቢሆን በእግዚአብሔር መንግስት ተቀባይነት ያገኛል።
1.7K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ