Get Mystery Box with random crypto!

ሰይጣን በጣም ብልጥ ነው።ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን ድነት አምነው እንዳይቀበሉ እ | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

ሰይጣን በጣም ብልጥ ነው።ሰዎች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን ድነት አምነው እንዳይቀበሉ እድሜ ልካቸውን በኃይማኖት እየተከራከሩ እንዲኖሩ እውነትም ሳያውቁ እንዲሞቱ ይፈልጋል።በመጽሐፍ የተጻፈውን ጭምር ወደ ጎን በመተው ያልተጻፈን ሐሰት እውነት ነው ተብሎ ርዕስ ተበጅቶለት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ብዙዎች ጊዜአቸውን በክርክር በማሳለፍ እግዚአብሔር የሰጣቸውን እድል ሳይጠቀሙ አልፈዋል።ያስታረቃቸውን ጌታ እርሱ አስታራቂ አይደለም ፈራጅ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ሳይታረቁ ሲሞቱ ያሳዝናል።ፍራጅ ብቻ እንደሆነ ስላመኑ ተፈረደባቸው።አማላጅም እንደሆነ ቢያምኑ ከፍርድ ባመለጡ ነበር።ሁለት አማላጅ የላከ እንዳይመስልህ አንድ ነው እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።ኢየሱስ ፈራጅ ነው ሲባል አሜን ብለህ አማላጅም ጭምር ነው ስትባል ግን እንዴት ትላለህ? እንዴት ፈራጅም አማላጅም ይሆናል? ካልከኝ፥ መልሱ ልክ አንዱ ኢየሱስ ሰውም አምላክም እንደሆነው ነዋ።አንተ ያልተጻፈን ሐሰት ይዘህ ባይጻፍም እስኪ አታማልድም የሚል ጥቅስ አሳየኝ በማለት እውነት ላይ ውሃ ቸለስ በማድረግ እውነትን ለመሸፈን መሞከር ነውር ነው።መጽሐፍ ኢየሱስ ያማልዳል ሲልህ እስኪ ድንግል አታማልድም የሚል አሳየኝ ማለት ምን ማለት ነው!? እንደዛ ካልክ እኔም እይዲህ ልበላ፤ ጼጥሮስ አማላጅ ነው።መጽሐፍ እኮ አማላጅ ኢየሱስ እንደሆነ ነው የሚናገረው፥ ቢናገርም እስኪ ጼጥሮስ አያማልድም የሚል ጥቅስ አሳየኝ? ታሳየኛለህ? ጴጥሮስ አያማልድም የሚል!? አንዱ ከመሬት ተነስቶ እኔ አማላጅ ነኝ አለ።እረ አይደልህም ብንለውና እርሱም እስኪ እኔ አማላጅ እንዳልሆንኩ ጥቅስ አሳዩኝ ስላለን እርሱ አማላጅ ነውን? ጥርት ያለ የተጻፈለት አማላጅ ኢየሱስ።ተጫማሪ ሮሜ
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet