Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ:ቆጣሪው ብዙ ኃይል ተጠቅማችዋል ብዙ ክፍያ ይሆንባችዋል ብሎ መቁጠር አያቆምም።በተጠቀማችሁበ | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

የቀጠለ:ቆጣሪው ብዙ ኃይል ተጠቅማችዋል ብዙ ክፍያ ይሆንባችዋል ብሎ መቁጠር አያቆምም።በተጠቀማችሁበት ልክ ሒሳብ ይወራረድባችዋል።ሕግም ልክ እንደዚህ ነው።ለአዳም አንድ ሕግ ከተሰጠው በኃላ እስከ ሙሴ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ሕግ አልተሰጠም ነበር።በሙሴ ጊዜ አስርቱ ሕግጋት መጡ።እነዚህ ሕጎች ከሙሴ በፊት አይታወቁም አልመጡም ነበር።አትግደል አትስረቅ ወዘተ የሚሉት ሕጎች የመጡት ከሙሴ በኃላ ከሙሴ በፊት አልነበሩም።ቃየን አቤልን ከገደለው በኃላ እግዚአብሔር አቤል የታል ሲለው ቃየን ቀለል አድርጎ እኔ የአቤል ጠበቃ ነኝ እንዴ አላውቅም የት እንዳለ ብሎ የመለሰው።መግደል ኃጢአት እንደሆነ መቆጠር የጀመረው ከሙሴ በኃላ ነው።

እንድያውም ሰዎች ቃየን አቤልን ስለገደለ ብለው ሊገድሉን ሲያሴሩ እግዚአብሔር በቃየን ግንባር ማንም እንዳይገድለው ምልክት አደረገበት።ቃየን አቤልን የገደለው ኃጢአት በአለም ስለነበር ነው።ያ ኃጢአት ግን ሕግ እስኪመጣ ድረስ አይቆጠርም ነበር።የሚቆጥር ሕግ በዛን ጊዜ ስላልመጣ።ቃየን በአለም የነበረውን ኃጢአት ነበር በወንድሙ ላይ የፈፀመው ነገር ግን እርሱ ላደረገው ኃጢአት የሚቆጥር ሕግ አልነበረም።ሕግ ካልነበረ ደግሞ ሮሜ እንደሚለው ኃጢአት አይቆጠርም ነበር።ነገር ግን ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ የነበሩ ሰዎች ኃጢአት ባይሰሩም ሞት በእነርሱ ላይ ነግሦ ነበር።ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።ሮሜ 5፥14

ሕግ ስላልነበር ተብሎ እስከ ሙሴ ያሉ ሰዎች ኃጢአት እንኳን ባይሰሩ እንኳን በአዳም መተላለፍ ምክንያት ኃጢአትን ማድረግ የሚችል ማንነት ወርሰዋልና በእርሱ መተላለፍ ምክንያት የተቆጠረው ኃጢአት ሰለባ ሁነዋል።ከሙሴ በኃላ ግን ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራ ኃጢአቱ ይቆጠርበታል።የሚቆጥር ሕግ ስለመጣ።በሙሴ ጊዜ እንደ ቃየን ሰውን እገድላለው የሚል ሰው ተወግሮ እራሱም ይሞታል።ምክንያቱም ከሙሴ በኃላ ሁሉም ሕጎች ስለመጡ።አንዳንድ ሰዎች ሕግን እንደማጽደቅያ ያስቡታል።ሕግ ለአንዳንድ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማስገብያ መንገድም አድርገው ይቆጡሩታል።ሕጉ ደግሞ በተዘዋዋሪ እነርሱ የሚሰሩትን ኃጢአት አንድ ሳያስቀር ሳይሸፍን ይቆጥርባችዋል።ይገርማል! ያጸድቀናል ያሉት ሕግ፥ የሚሰሩትን ኃጢአት እየቆጠረ ሲያስቀምጥ!?

በቤታችሁ ያለው የመብራት ቆጣሪ፥ መብራት ከተጠቀማችሁ በኃላ ቆጣሪው እንደማይራራላችሁ ሁሉ፥ ያጸድቀኛል የምትሉት ሕግም ኃጢአት ስታደርጉ ከመቁጠር ወደ ኃላ አይልም።ስለዚህ ሕግ አፅዳቂ ሳይሆን ኃጢአት የሚያደርጉትን ሰዎች ኃጢአታቸውን የሚቆጥር ነው።ታድያ የሚያፀድቀው ማነው? እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።ሮሜ 5፥18-21
Contact @eternallife12
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet