Get Mystery Box with random crypto!

ሕ-ግ ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈ | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

ሕ-ግ

ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤ ሮም 5፥12 ሰሞኑን ሮሜ ሳነብ በጣም ከደነቅኝ ቃል ይሄ ነው።ኃጢአት ሕግ ሳይመጣ በፊት በዓለም ነበር።ነገር ግን ያ ኃጢአት አይቆጠርም ነበር።አዳምና ሔዋን በምድር በገነት በጽድቅ ሲኖሩ ሳለ፥ ኃጢአት ደግሞ በአለም ነበር።ኃጢአት ወደ ሰው ልጅ የገባው አትብሉ የተባሉት ፍሬ የበሉ ዕለት ነው።ይሁን እንጂ፥ ከዛ በፊት ኃጢአት በአለም ነበር።ወደ ኤዴን ገነት በእባብ ተመስሎ ቢገባም፥ ከመግባቱ በፊትም ነበር።መቆጠር የጀመረው ግን ሕግ ከመጣ በኃላ ነው።ምክንያቱም ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም ነበርና።

አንድ ሕግ በገነት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ልጅ መጣ።ከዚህ የፍሬ ዛፍ እንዳትበሉ በበላችሁ ጊዜ የሞት ሞትን ትሞታላችሁ የሚል ሕግ።ሕግ ከመጣ በአለም የነበረ ኃጢአት ሊቆጠር ግድ ነው።የሰው ልጅም በአለም የነበረውን ኃጢአት ይሻለኛል በማለት እግዚአብሔር የሰጠውን ሕግ ከመፈጸም ይልቅ ያልተቆጠረውን ኃጢአት ወደራሱ በማስገባት አስቆጠረው።ኃጢአት ወደ ሰው ልጅ ገባ፥ ያ ኃጢአትም ተቆጠረ።ምክያቱም አንድ ሕግ ስለነበር።"አትብሉ" የሚል።ኃጢአት መቆጠር ሲጀምር፥ ለተቆጠረው ኃጢአት ቅጣት ያስፈልገዋልና የሰው ልጅ ከኤደን ገነት እንዲባረር ተደረገ።በነገራችን ላይ አዳም እንደ ሰይጣን ከሰማይ ወደምድር አልተጣለም።ሰይጣን ኃጢአት ካደረገ በኃላ ወደምድር ነው የተጣለው።ምክንያቱም ይኖር የነበረው በሰማይ ስለነበር።

የሰው ልጅ ግን ኃጢአት ከሰራ በኃላ ከኤደን ገነት ነው የተባረረው።አልተጣለም።ምክንያቱም ይኖር የነበረው በምድር ስለሆነ።ሕግ የኃጢአት ቆጣሪ ነው።ምን ማለት መሰላችሁ፤ እናንተ ቤት የምትጠቀሙት የመብራት አገልግሎት ቆጣሪ ከሌለው መብራት ሃይል የሚሰሩ ሰዎች እናንተ ምን ያህል መብራት እንደተጠቀማችሁ፣ ምን ያህል ኃይል ለተለያዩ አገልግሎቶች እንደዋሉ ማወቅ ያዳግታችዋል።የተጠቀማችሁበት መጠን ካላወቁ ሒሳብ አስልተው እናንተን ለማስከፈል ያስቸግራችዋል።እንድያውም እናንተ ምንም አልተጠቅምን ብትሉ እራሱ ተጠቅማችዋል ብለው ሊከራከርዋችሁ አይችሉም ምክንያቱም እንደተጠቀማችሁ ማሳየት የሚችለው ቆጣሪ እናንተ ስላላስገባችሁ።እነርሱም በቀላሉ ምን ያክል ኃይል እንደተጠቀማችሁ የሚያሳይ ቆጣሪ ስላልገጠሙላችሁ።

ሕግም አለ ቃሉ፥ ልክ እንደ ቆጣሪ ነው።ኃጢአት በአለም ነበር ነገር ግን አይቆጠርም ነበር።የሚቆጥረው ሕግ ስላልመጣ።መብራት ኃይል ቆጣሪ በቤታችሁ ከገጠሙ በኃላ የምትጠቀሙበት መብራት መቆጠር ይጀምራል።ቆጣሪ ሳይመጣ በፊት ግን የምትጠቀሙት መብራት አይቆጠርም ነበር።ሕግም ሳይመጣ በፊት ኃጢአት በአለም ሳለ አይቆጠርም ነበር።ቆጣሪ ከተገጠመ ማንም ሰው መብራት ኃይልን ማጭበርበር ሆነ መሸወድ አይችልም።ሰዎች ቆጣሪ እያለ ምንም ያክል የኃይል አገልግሎት ቢጠቀሙ ቆጣሪው ከመቁጠር ወደኃላ አይልም።በዛው ልክ ትንሽ የኃይል አገልግሎት ቢጠቀሙም ቆጣሪው አሁንም ከመቁጠር ወደኃላ አይልም።

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet