Get Mystery Box with random crypto!

☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

የቴሌግራም ቻናል አርማ yezelalemhiywet — ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE
የቴሌግራም ቻናል አርማ yezelalemhiywet — ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE
የሰርጥ አድራሻ: @yezelalemhiywet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

🔊ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል
እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤|1ኛ ዮሐ 1፥2
🔊ሕይወት ከሞት በኃላ ከጌታ ጋር ይቀጥላል፡፡ቻናሉ የተከፈተው ሰዎች በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን ሕይወት እንዲካፈሉና የቃሉን እውነት ተምረው አርነት እንዲወጡ ነው፡፡You can contact me📲 @YesZoelife

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-13 07:09:22 የዘላለም✞ሕይወት||ETERNAL LIFE pinned « የዘመን-መጨረሻ! ክፍል አንድ መጀመርያ ያለው ነገር ሁሉ መጨረሻ ሊኖሮው ግድ ነውና፤ አሁን እየኖርንባት ያለቺው ዓለም ካለመኖር ወደመኖር እንደመጣቺው ሁሉ፥ ከመኖር ወዳለመኖር ልትሸጋገር የግድ ነው፡፡ዓለም በዚህ ሰዕት መጨረሻዋ በታላቅ ምጥ ላይ ትገኛለች፡፡ምክንያቱም ምንም እንኳን ለዘመናት በእግዚአብሔር ቸርነት ብትኖርም አሁን የመጥፍያ ወደ ባህር እሳት የመጣልዋ ጊዜ እንደደረሰ ስለምታውቅ በጭንቅ…»
04:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 11:57:05
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
Share and forward it in all Groups
All Christian use this Pp in your telegram ተባረኩ
2.6K viewsedited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 06:47:38 የምስክርነት ጊዜ!
ስም ተመስገን
በወንድማችን!
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
602 viewsedited  03:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 07:02:20 የምስክርነት ጊዜ!
ከአርባ~ምንጭ
በወንድማችን!
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
599 viewsedited  04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:43:00 የቀጠለ: አሁን ያሉት ሰማይና ምድር በዛን ሰዕት ይሸሻሉ።ስፍራም አይገኝላቸውም።ምክንያቱም በሰው ልጅ ኃጢአት ምክንያት ቆሸዋልና ዘላለም መኖር ሆነ ማኖር አይችሉም።ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ራእይ 20፥1 ካለመኖር ወደመኖር እንደመጡ ሁሉ ከመኖር ወዳለመኖር ይሸጋገራሉ።ታድያ የት ነው የምንሆነው እነዚህም ከተወገዱ፥ ዮሐንስ በራእይ ባየው አዲስ ሰማይና ምድር ነዋ።"አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም።"ራእይ 20፥1 ዮሐንስ በራእይ ያየው ይሄ አዲስ ሰማይና ምድር አሁን ለእኛ ስላልተገለጠ እንጂ በመንፈሳዊ አለም ያለቀለት ጉዳይ ነው።ለእኛ የሚገለጠው በዛን ሰዕት ነው፡፡ሙሽራዋ ቤተ-ክርስትያን ዘላለም የምትኖረውም በዚህ አዲስ ምድር ላይ ይሆናል።ታድያ አዲሱ ሰማይ አሁን እንዳለው ሰማይ አይደለም።በአዲሱ ሰማይ ለአዲስትዋ ምድር(ለአዲስትዋ ኢየሩሳሌም) የፀሐይ ብርሃን አትሆናትም።በጉ ብርሃንዋ ነው።

ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።ራእይ 20፥2 አሁን ካለቺው ምድር ፍጽሞ የተለየች በቃላት ለመግለጽ የምትከብድ አዲስ ምድር ላይ ሙሽራዋ ዘላለም ከሙሽራው ጋር ትኖራለች።አንዳንድ ሰዎች ዘላለም የምንኖረው በሰማይ የሚመስላቸው አሉ፤ ነገር ግን ዘላለም የምንኖረው በአዲሱ ምድር ላይ ነው።ለዚህ ነው መጽሐፍ እንዲህ ያለው፤ ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።”ራእይ 22፥5 በነገራችን ላይ ከኢየሱስ የሚወጣው ብርሃን አሁን ካለቺው ፀሐይ ሰባት እጥፍ የሚያበራ ነው።ታድያ ይሄ ብርሃን ለዘላለም ላይጠልቅ የሚበራ የሕይወት ብርሃን ነው።አሁን ያለቺው ፀሐይ አንዳንዴ በደመና ትሸፈናለች ብርሃንዋም የምትሰጠው በየቀኑ ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ ነው።ይሄ ብርሃን ግን አንዳች ነገር ሳይጋርደው፥ ላይጠልቅ ለዘላለም ብርሃን ይሆነናል።

ኢየሱስ ከዛን ጊዜ በኃላ ለዘላለም በአካል ከእኛ ጋር ስለሚኖር፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።ራእይ 21፥22-23 አሁን በምድር ስንኖር እነዚህ ተፈጥሮ የሚባሉት ለመኖር ያስፈልጉናል።ለምሳሌ የፀሐይ ብርሃን፣ ውሃ፣ ኦክሲጂን ወዘተ።እነዚህ ነገሮች አሁን ለመኖር አስፈላጊ የሆኑበት ምክንያት አሁን ያለው አካላችን የተሰራው በእነዚህ የተፈጥሮ አገልግሎቶች እንዲኖርና እንዲያድግ ተደርጎ ስለተሰራ ነው።በአዲሱ ምድር ዘላለም ከበጉ ጋር ስንኖር ግን እነዚህ ነገሮች ሳይሆኑ ኢየሱስ ነው የሚያኖረን።ምክንያቱም በንጥቀት ጊዜ የምንለብሰው አካል ይሄንን አለም ሳይሆን ያንን አለም ታስቦ ስለሆነ የሚሰጠን በዛ አለም በሕይወት ዘላለም እንድንኖር የሚያደርገው በጉ ነውና ከእርሱ ውስጥ በሚፈሰው የሕይወት ውሃ ወንዝ ዘላለም እንኖራለን።

ታላቅም ድምፅ ከሰማይ፦ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።ራእይ 21፥3-4 በዛን ጊዜ ራሃብ የለ፣ ቸገረኝ የለ፣ ጠማኝ የለ፣ ቀናብኝ የለ፣ ሞት የለ፣ በሽታ የለ፣ ማልቀስ የለ፣ መንከራተት የለ።ለምን? የቀድመው ስርዕት አልፍዋልና።ፍጹም በሆነ ሕይወት ለዘላለም ከኢየሱስ ጋር መኖር! ኦ! እንዴት ያለ መታደል ነው።ሁሌም ቢሆን መፈጠሬን ብሎም በጌታ መሆኔን እንድወደው የሚያደርገኝ ነገር፥ ለዘላለም ከኢየሱስ እንደምኖር ሳስብ ነው።በዚህም ሐሴት አደርጋለሁ።

በዚህ ዓለም ላይ ምድነው የሚያጓጓህ ብባል መልሴ ከጌታየ ጋር በአካል ዘላለም የምንኖርበት ቀን መገለጥ።የእናንተም ጉጉት ይሄ ነው።ዘላለም እንዴት ያለ ኑሮ እንደምንኖር አሁን ላይ ሁኖ መናገር አይቻልም።ምን ተብሎስ ይገለፃል እንዲህ አይነት ሕይወት ከመኖር በፊት እንዲህ ይመስላል ብሎ መግለፅ አይቻልም።በቃላት ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው።ካልተኖረ በቀር።ተባረኩ! ለተከታታይ አራት አምስት ሳምንታት ሲቀርብ የነበረው የዘመን መጨረሻ ትምህርት አጠር ባለ አቀራረብ ይሄንን ይመስላል።ክብር ሁሉ ለኢየሱስ ይሁን።ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።ራእይ 21፥5

ማራናታ_ ጌታ _ ሆይ _ ቶሎ _ ና!

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
1.2K viewsedited  10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 13:33:45 የቀጠለ: ለዚህ ነው በአንድ ሺህ አመት ውስጥ የአለም የሕዝብ ቁጥር በፍጥነት የሚጨምረው።ብዙ ሕፃናትም ይወለዳሉ።አስቡት ለአንድ ሕፃን ተወልዶ በሺህ አመት ውስጥ ስንት እንደሚወለዱ! እነዛ የተወለዱት ስንት እንደሚወልዱ! ከምናስበው በላይ ነው።አንድ ሺህ አመት በጣም ብዙ ጊዜ ነው።አንደኛ ሴቶች በዛን ወቅት ፅንስ ማስወረድ አይችሉም።ንጉሱ በምድር አለ።ኃጢአት ሳይሆን ጽድቅ ስለሚገለጥ።ሰዎች እራሳቸውን አያጠፉም።አሳቹ ዲያቢሎስ ታስርዋልና።ሰላምም ይሰፍናል።እነዛ ሁለቱ ምስክሮች መንግስቱ ከመመስረቱ በፊት ሲመሰክሩት የነበረው የሺህ አመት መንግስት አካል ለብሶ በእስራኤል ምድር ይገለጣል።ልክ ስለኢየሱስ ዮሐንስ እየመሰከረ ሳለ ክርስቶስ በእስራኤል ምድር ከሴት ልጅ እንደተወለደ።ኢየሱስ በምድር ከተገለጠም በኃላ ብዙ ሰዎች በእርሱ በማመን ድነዋል።እየዳኑም ነው።በሺህ አመት ጊዜም በአራቱም አቅጣጫ በሚሞተው አካላቸው የሚኖሩ አሕዛቦች በእስራኤል ምድር ስለተመሰረተው የእግዚአብሔር መንግስት ሰምተው በማመን ንጉሱን በመቀበል የሚዲኑ ሰዎች አሉ።

እነዚህ በዛን ሰዕት መንግስቱን አይተው የሚዲኑ ሰዎች በሚበሰብሰው አካል ስለሆኑ ሺህ አመት ሳይፈፀም ሊሞቱ ይችላሉ።ታድያ ትንሳኤቸው የሚሆነው እስከ ዛ ቀን ድረስ ሳያምኑ ከሞቱት ጋር ነው።ኋለኛው ትንሳኤ ላይ።ሺህ አመት ከክርስቶስ ጋር የሚነግሱት ትንሳኤን በንጥቀት ጊዜ ያገኙት ላይሞቱ ለዘላለም ሕያው ሁነው እንዲኖሩ ነው።እንዲሁም አካላቸው ሞት የማይዘው በመሆነ ይሞቱ ዘንድ አይቻላቸውም።ነገር ግን ሺህ አመት ያልነገሱት በስጋ ይሞቱ ዘንድ ግድ ነው።ምክንያቱም እነርሱ የሚኖሩበት አካል የቀድመው አካል ሲወለዱ ከአዳም በወረሱት በሚበሰብሰው አካል ነው።ነገር ግን የሚሞቱት ልክ እንደአሁኑ በሃምሳ በሳላሳ በአርባ አመታቸው ሳይሆን ከዛ ባለፈ እንድሜ ነው።ምክንያቱም እርግማኑ ለአንድ ሺህ አመት ከዚህ ምድር ስለሚወገድ።ታቃላችሁ የሰው ልጅ እድሜ መጀመርያ በዘፍጥረት የሚኖረው እድሜ በትንሹ መቶ ሃያ ከፍ ሲል 619 አመት ከዛም በላይ ነበር።ኃጢአት እየሰራ በመጣ ቁጥር ግን እግዚአብሔር ሰባ ስልሳ አመት አደረገባቸው።በሺህ አመት ጊዜ ያ እድሜ ይመለሳል።

ልክ አስደናቂ የሆነው የሺህ አመት መንግስት ሲጠናቀቅ።ታስሮ የነበረው አውሬ ለተወሰነ ጊዜ ይፈታል።ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤ ራእይ 20፥7 ታድያ የሚፈታው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ላይመለስ በስህተት እንኳን ላይታይ ወደጥልቁ ባህር ሊጣል ስለሆነ ነው።አጅሬ ግን ስትፈታ አመልዋን ስለምታውቅ የሺህ አመት መንግስት የተመሰረተበትን የጺዮንን ከተማ ከአራቱም መዕዘን አሕዛብን ለሰልፍ ያስነሳል።ኢየሱስና ቅዱሳን ያሉበትን ውብ ከተማ ለማጥፋት ከአራቱም አቅጣጫ አሕዛብን ያሰልፋል።በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው።ወደ ምድርም ስፋት ወጡ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ ራእይ 20፥8-9 ምንም እንኳን ቢከባትም ጫፍዋን ሳይነክዋት፥ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው።ራእይ 20፥9


ለመጨረሻ ጊዜም ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ።ራእይ 20፥10 ይሄ ፍርድ ዘላለማዊ የሆነ ፍርድ ነው።ዳግመኛ ላይታዩ ላይታወሱ ወደ ዲኑ ለዘላለም ይጣላሉ።ልክ ይሄ ስርዕት ከተፈጸመ በኃላ ኢየሱስ ፈራጅ ሁኖ የሚቀመጥበት ጊዜ ይሆናል።ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም።ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።ራእይ 20፥11-12 በነጩ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ኢየሱስ ነው።ነጭ ዙፋን የሚለው እርሱ ሲፈርድ በእውነተኛና በጽድቅ እንደሚፈርድ ለማመልከት ነው።በፊተኛው ትንሳኤ ያልተካፈሉ ነገር ግን በስጋ የሞቱ ሰዎች ለፍርድ ያን ጊዜ ይነሳሉ።

ኋለኛው አልያም የመጨረሻ ትንሳኤ የሚባለው።እስከ አሁን ብሎም እስከ ሺህ አመት እስኪፈጸም ሳያምኑ የሞቱ ሰዎች የዘላለም ፍርድና ቅጣን ለመቀበል ከመቃብር እንዲወጡ ይደረጋል።“የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም።ራእይ 20፥5 እነዚህ ኢየሱስ ነጭ ዙፋን ሲሆን ለፍርድ ይነሳሉ።ሲነሱ ታድያ እነርሱ ብቻ አይነሱም ከንጥቀት እስከ ሺህ አመት ንግስ ጊዜ ያመኑት አብረው ይነሳሉ።ኢየሱስም ያመኑት በቀኝ ያላመኑት በግራ የሚያደርጋቸው ያን ጊዜ ነው።ያላመኑት ወደ ጥልቅ በማይሞት አካል ለመሰቃየት በሚሆን አካል ተደርገው ዘላለም ይጣላሉ።በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ።ራእይ 20፥15 በቀኝ ያሉቴ ደግሞ የትንሳኤ አካል ለብሰው ከቅዱሳን ጋር ይቀላቀላሉ።ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ።ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።ራእይ 20፥13-14

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
510 viewsedited  10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:39:22 የዘመን መጨረሻ!
ክፍል~ስምንት

በዘፍጥረት ላይ ምድር የሰው ልጅ በሰራው ኃጢአት ምክንያት እንደተረገመች ይታወቃል።ነገር ግን በሺህ አመት እርግማኑ አይሰራም።ምድርም ለዘሩባት ሁሉ በእጥፍ ፍሬን ትሰጣለች።የምትከለክለው ነገር አይኖርም።ምን ምድር ብቻ በዛን ጊዜ ወንጀል የሚሰራ አይኖርም።ምክንያቱም የአለም መንግስት ኢየሱስ ነው።ሰው ሰውን አይገድልም።ጦርነት አይኖርም።ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።ኢሳይያስ 2፥3-4

የአለም መንግስት የሚሆነው ኢየሱስ ነውና ልክ አሁን እንዳሉት መንግስታት ለጦር መሳርያ ተብሎ የሚመደብ በጀት በዛን ጊዜ አይኖርም።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሳም።አሁን ሰው በጦርነት ይሁን በተለያየ ነገር እርስ በእርሱ እየተጫረሰ ነው።ይሄ የሆነበት ምክንያት አንዱ አውሬው ስላለና ስላልታሰረ ነው።በሺህ አመት ጊዜ ግን አውሬው ለሺህ አመት ስለሚታሰር ሕዝብ በሕዝብ ላይ አይነሳም።በሺህ አመት የሚገርመው በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ ፍትህ የሚሰፍንበት ጊዜ ነው።ምክንያቱም ፈራጁና ዳኛው ቅዱስ የሆነው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ።መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ባለጠጎች ድሆች፥ ድሆችም ባለጠጎች ይሆናሉ የሚለው ቃል የሚፈጸመው በዚህ ጊዜ ነው።በዛን ጊዜ ሙስና አይኖርም።በነገራችን ላይ አንድ ሺህ አመት በጣም ብዙ ጊዜ ነው።በዛን ጊዜ የአለም ሕዝብ አሁን ካለው በጣም ብዙ ይሆናል።በእጥፍ ሊጨምር ይችላል።ምክንያቱም የዚህ አለም ነገር ወደቀድመው ስርዕት ስለሚመለስ የሰው ልጅ የሚሞተው በጣም ብዙ አመት ከኖረ በኃላ ነው።

በሽታ ስልጣን አይኖረውም።ምን አለፋችሁ ኢየሱስ መንግስት የሆነበት አለም ላይ ጉስቁልና ድህነት፣ ማጣት፣ መራብ የለውም።በአጭሩ አሁን በዚህ አለም ያሉት በተፈጥሮ ይሁን በሰው ሰራሽ የሚመጡ መጥፎ ነገሮች በዛን ጊዜ ስፍራም አይኖራቸውም።ኢየሩሳሌም ያን ጊዜ ከአለም ሁሉ ክፍ ብላ ትታያለች ምክንያቱም የሺህ አመት መንግስት ምስረታው በአካል በዛች ምድር ስለሚሆን።አሕዛብ ሁሉ ወደዛች ምድር በየቀኑ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማየት ይጎርፋሉ።መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ የሚል ቃል አለ፥ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።ሮሜ 8፥19 ይሄ ቃል ትንቢት ነው።የሚፈጸመው በሺህ አመት ንግስ ጊዜ ነው።ፍጥረት አንድ የሚጠባበቁት ነገር አለ እርሱም አመኞች(የእግዚአብሔር ልጆች የሆነው እኛ) በአዲሱ ማንነታችን በአዲሱ አካላችን በፍጽምና እስክንገለጥ ይጠባበቃሉ።

ምን ማለት መሰላችሁ በማይበሰብሰው አካላችን በሺህ አመት ንግስ ጊዜ በአካል ከበጉ ጋር የምንኖረው ኑሮ የሚያስደንቅ ነው።ከአንድ ቦታ ወደአንድ ቦታ ለመንቀሳቀስ ስንፈልግ ትራንስፖርት አያስፈልገንም።ከኢየሱስ ጋር ወደምድር ስንመጣ በፕሌን እንዳልመጣነው ሁሉ፥ በዚህ በሺህ አመት ንግስ ጊዜም በኢየሩሳሌም በቤተመንግስቱ ስንኖር እንዴት ልግለጽላችሁ ቃላት ይመርጣል።ኑሮአችን የማሆነው በዛን ጊዜ ከሚኖሩት አሕዛቦች የተለየና የማይገናኝ ነው።ኢየሱስ ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት በተዘጋ በር እንደገባ አካሉ ምድራዊ ነገሮች ምንም ከማድሰግ እንዳልገደቡት፤ የእግዚአብሔር ልጆችም ያን ጊዜ በዚህ ማንነት ይገለጣሉ።ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።ዕንባቆም 2፥14 እና ኢሳይያስ 11፥9 አዎ! ምድር ያን ጊዜ አምላክዋን በማወቅ ትሞላለች ምክንያቱም መንግስቱን በመካከልዋ ስለመሰረተ።

በዛን ወቅት በዚህ ምድር ላይ ሁለት አይነት ሰዎች ነው የሚኖሩት።ከመንግስቱ ውጪ የሚኖሩት አሕዛቦች ማለትም በሚሞተውና በሚበሰብሰው አካል ውስጥ የሚኖሩ፣ ከቁጣው የተረፉ ሰዎች ሲሆኑ።ሁለተኛዎቹ ደግሞ በተለወጠው አካል በአዲሱ ማንነት ከንጉሱ ጋር አብረው ለሺህ አመት የሚነግሱ አማኞች(እኛ) ናቸው።ታድያ እነዚህ በፊተኛው ትንሳኤ ማለትም በንጥቀት ጊዜ የተለወጠ አካል ያላቸው አማኞች ናቸው።አማኞች ለአንድ ሺህ አመት ከኢየሱስ ጋር በመንግስቱ ሲኖሩ “ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና፥”ሉቃስ 20፥35 በሺህ አመት ጊዜ እየተጋቡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ።እነዚህ የሚጋቡት በዚህ የሺህ አመት ንግስ ላይ አብረው ያልነገሱ አሕዛብ ናቸው።እኛ ግን በንጥቀት ጊዜ ከሙታን ተነስተን የማይበሰብሰው ሰማያዊውን አካል ለብሰናልና እንደእነርሱ ልንሆን ከቶ አይቻለንም።

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
2.1K viewsedited  18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:41:27 ከፊታችን ባለው ሐሙስ የዘመን መጨረሻ ተከታታይ ትምህርት የመጨረሻው ክፍል ስምንት ከምሽቱ 2:00 ላይ ይቀርባል።ተባረኩ! ሙሽራው በቅርቡ ሙሽሪትን ሊወስድ ይመጣል...አሜን! መልካም ምሽት።
498 views20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 23:25:52 የዘሪው_ምሳሌ!

ሉቃስ 8፥5 ጀምሮ ኢየሱስ ይከተሉት ለነበሩት ሰዎች እንዲህ የሚል ምሳሌ ነገራቸው፥ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ።ሲዘራም አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ተረገጠም፥ የሰማይ ወፎችም በሉት።ነገር በምሳሌ ከገባቸው ብሎ ነበር ነገር ግን አልተረዱትምና ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል(ወንጌል) ነው አላቸው።ወፎቹም ሰይጣኖች ናቸው።በመንገድ ዳርም ያሉት የሚሰሙ ናቸው፤ ከዚህ በኋላም ዲያብሎስ ይመጣል አምነውም እንዳይድኑ ቃሉን ከልባቸው ይወስዳል።ብዙ ሰዎች በዚህ ዘመንየወንጌልን ቃል ሰምተዋል።

ታድያ ሰምተው እያለ ለምድነው አምነው የማይድኑት ብየ መጽሐፍን ስጠይቅ? ለካ ዲያቢሎስ የሰሙት ቃል፥ ከልባቸው እየነጠቀ ሌላ ያልሰሙት ቃል የማይጠቅማቸው ቃል እየሰጣቸው ነው።በሆነ አጋጣሚ የኢየሱስ አዳኝነት ሰምተው እያለ በዛን ሰዕት ሰይጣን የሰሙትን ወንጌል አምነው እንዳይቀበሉ፥ ሌላ ጥቅም የሌለው ወንጌልን የሚያጠለሽ ሐሳብ ለልባቸው በማቃበል እነርሱ የሰሙትን ቃል ከልባቸው ይወስድባችዋል።ስለዚህ ልባችሁን ለወንጌል ሐሳብ እንጂ ለዚህ አለም ሐሳብ አትክፈቱ።የሰማችሁት ቃል ዘር ነውና ዘር ደግሞ የሚበቅል የሚበዛ ነው።ታድያ ይሄንን ዘር የሰማይ ወፎች እንዳይበሉባችሁ ተጠንቀቁ።

በዚህ አለም ላይ ከሰማይ በታች እንደ ዲያቢሎስ ብልጥ ያለ ማንም የለም።ብልጠት ብቻ ሳይሆን የስድስት ሺህ አመት የሥራ ልምድ ያለው ከሰማይ የወደቀ ፍጡር ነው።ድግሪ ሳይኖረው ነገር ግን ለየትኛውም የክፋት ሥራ የሁለት የአራት አመት የስራ ልምድ ሳይሆን የስድስት ሺህ አመት የስራ ልምድ ያለው ነው።ታድያ ይሄንን ጠላት ድል ለማድረግ የዘላለም የስራ ልምድ ያለውን እግዚአብሔር መያዝ አለባችሁ።ዲያቢሎስ
የሚጠቅማችሁን ሐሳብ ወደጎን እንድትተውና የእርሱን ሐሳብ እንድታሰላስሉ ሲፈልግ በስጦታ መጠቅለያ የተጠቀለቀለ ሲታይ አሪፍ ሐሳብ የሚመስል ነገር በመያዝ የልባችሁን በር ያንኳኳል።በዛን ሰዕት ከከፈታችሁለት በልባችሁ ውስጥ አስቀድሞ የነበረውን ቃል ይነጥቃችሁና ይዞት የመጣውን የራሱ ሐሳብ ይሰጣችዋል።

የእርሱ ሐሳብ ደግሞ ታውቃላችሁ እንኳን ለእኛ በዚህ ዘመን ላለነው ለአዳምና ለሔዋን እራሱ አልጠቀመም።አንድ ነገር እውነትም ውሸትም ሁኖ ሊገኝ ይችላል።የዲያቢሎስ ሐሳብ ግን መቶ ፐርሰንት ውሸትና ውሸት ነው።የእርሱ ሐሳብ የሚያጠፋ እንደሆነ ስለሚያውቅ ሰዎች የሚሰሙትን ወንጌል ውሸት እንደሆነና አምነውም እንዳቀበሉ ያደርጋል።የሰሙት ወንጌል እውነት ነው ወይስ ሐሰት ነው? ብለው እንኳን ለማሰብ እድል አይሰጣቸውም።ስራውን ሰለሚያውቅ ሁሌም ቢሆን ከእግዚአብሔር የሚሰሙት ነገር የውሸት እንደሆነ በመናገር በራሱ ውሸት ከሌላው ሰው ልብ ውስጥ እውነትን ይወስድባችል።ስለዚህ ወገኖቼ ልባችሁን የምትሰሙትን የእውነት ቃል ከሚሰርቁ መናፍስቶች ተጠበቁ።

@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
@Yezelalemhiywet
1.9K viewsedited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:23:06
አንድ ነገር የእናንተ አለመሆኑን የምታውቁት ነገሩ ከእናንተ ጋር ባለው የጊዜ ቆይታ ነው።በዚህ አለም ሰዎች የእኔ ነው ብለው የሚመኩበት ነገር ሁሉ ለጊዜው ከእነርሱ ጋር ስላለ የእነርሱ ይመስላችዋል።ነገር ግን እውነት የእነርሱ እንዳልሆነ የሚታወቀው በስጋ ይሄንን አለም ሲሰናበቱ ነው።የእኔ ነው ብለው የሚመኩበት ነገር ሁሉ ሲሞቱ ይዘውት አይሄዱም።ገንዘቡ ይሁን፣ መኪናው፣ G+5 ቤቱ ይሁን፣ ዝና ይሁን ታዋቂነት እነዚህንና እነዚህን የመሰሳሰሉ ቁሶች ያለው ሰው ሲሞት እኛ እኮ የአንተ ነን ብለው እርሱ ወደሚሄድበት አይሄዱም።እንኳን እነዚህ ቁሳቁሶች ቀርቶ፥ አሁን ያላችሁ አካል(ስጋችሁ) እራሱ የእናንተ አይደለም።ስትሞቱ ጥላትታችሁት ትሄዳላችሁ።የእናንተ የሆነ ነገር ብትሞቱ እንኳን ከእናንተ ጋር ዘላለም የሚቆይ የሚኖር ነው።በዚህ አለም ሆነ በሚመጣው አለም የእናንተ የሚባለው ኢየሱስ ነው።መመካት ያለባችሁ በዚህ ነው።እርሱ የእናንተ፤ እናንተም የእርሱ ናችሁ።በዚህ ምድር የእኔ ከምትሉት ነገር ሞት ይለያያችዋል።ከኢየሱስ ጋር ግን ማን ይለያያችዋል? ሞት? ልክ ነው! ሞት ከአለም ጋር የተላመደው አካላችሁ ጋር ለዘላለም ይለያያችዋል።ምክንያቱ አሁን ያላችሁበት አካል የተበጀው ለወደቀው አዳም እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ለሆነው ማንነታችሁ አይደለም።ስለዚህ ይሄ አካል የእናንተ አይደለም።ልክ ነው! ሞት ከዚህ አለም ያስወጣችዋል።ምክንያቱም እናንተ ዳግመኛ የተወለዳችሁት በዚህ አለም ዘላለም እንድትኖሩ ሳይሆን በሚገለጠው አዲስ አለም ውስጥ ነው።በነገራችን ላይ ሞት አንድም የእናንተ ካልሆኑ ነገሮች ሁሉ ከስጋችሁ ጀምሮ ለዘላለም እንድትለያዩ በማድረግ፥ የዘላለም የእናንተ ወደ ሆነው ጌታ ደግሞ የሚያደርስ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ነው።የእናንተ የሆነ ነገር ስትሞቱ እራሱ ታገኙታላችሁ።share it
1.1K viewsedited  15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ