Get Mystery Box with random crypto!

በልጆች መዳንና መነጠቅ ጉዳይ ልጆች ከአማኝ ቤተሰቦቻቸው ጋር ይነጠቃሉ ወይስ አይነጠቁም? ልጆች ክ | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

በልጆች መዳንና መነጠቅ ጉዳይ ልጆች ከአማኝ ቤተሰቦቻቸው ጋር ይነጠቃሉ ወይስ አይነጠቁም? ልጆች ክፉና ደጉን ሳያውቁ ቢሞቱ መንግስተ ሰማይ ይገባሉ ወይስ አይገቡም? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነጠቁና መንግስቱን እንደሚወርሱ ይናገራል።እንዲዳስሳቸውም ሕፃናትን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ያመጡአቸውን ገሠጹአቸው።ኢየሱስ ግን አይቶ ተቈጣና፦ ሕፃናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሉአቸው፤ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና።የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አላቸው።ማርቆስ 10፥13-15 በማለት ሕፃናት ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደሚገቡ ይናገራል።በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈው የታላቁ ትዕዛዝ ላይ ጌታ ያለው የፍርድ ነገር ሕፃናትን አይመለከትም።ወደ አለም ሁሉ ሂዲ ወይጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ግን ይፈረድበታል።በማያምን ሰው ላይ የገኃንም ፍርድ አለበት።ጥያቄው ሕፃናት ክፉና ደጉን ወደ መለየት እስኪደርሱ ድረስ በአይናቸው የማያዩት የማይዳስሱት ነገር አለ ብለው ሊያምኑ ይችላሉን? በፍጹም አይችሉም።ምንም እንኳን ሕፃናት እንደአዋቂዎች ጆሮ ቢኖራቸውም የሚሰሙት ነገር አመዛዝነው ውሸትና እውነቱን መለየት የሚያስችል ብስለት ሰለማይኖራቸው እምነት ስለሚባለው ነገር አይገባቸውም።ስለዚህ ሕፃናት አድገው ወደማስተዋል ደረጃ እስኪደርሱ ሳያምኑ ቢሞቱ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ይገባሉ፤ በንጥቀት ጊዜም ይነጠቃሉ።አንድ ልጅ ክፉና ደጉን ወደማወቅ ደረጃ ቢደርስ ለሚሠራው ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናል።እድሜው ስለደረሰም ለሰራው ኃጢአት በወንጌል በማመን ንሰሐ በመግባት ድነትን ያገኛል።ነገር ግን እስከዚያ የዕድሜ ክልል ድረስ ባለው ጊዜ ቢሞት ወይም ንጥቀት ቢሆን በእግዚአብሔር መንግስት ተቀባይነት ያገኛል።