Get Mystery Box with random crypto!

አንዱ ምን አለ መሰላችሁ ሕይወት በB ተጀምራ በD ታቆማለች፥ ማለትም ሕይወት Birth(በመወለድ) | ☦የዘላለም ✞ ሕይወት¤ETERNAL LIFE

አንዱ ምን አለ መሰላችሁ ሕይወት በB ተጀምራ በD ታቆማለች፥ ማለትም ሕይወት Birth(በመወለድ) ትጀመርና Die(በሞት) ትጠናቀቃለች።ነገር ግን አለ በመካከለቸው C አለች።እርሷም Choice(ምርጫ) ነች አለ።የዚህ ምድር ሕይወት በመወለድ ጀምሮ ከዛን ሰው ያዋጣኛል ያለው በመምረጥ በስተመጨረሻም የስጋን ሞት ይላበሳል።እኔ ደግሞ አንድ ነገር ልጨምር ፈለኩ፥ ሕይወት በD ብቻ አያበቃም አልኩ።ሕይወት ከD በኃላ በE(Eternal) ይቀጥላል።በመወለድ የጀመረ ሕይወት በመምረጥ ይቆይና በመሞት የምድራዊው ሕይወት ያበቃና በኢየሱስ በማመን የዘላለም ሕይወት ይቀጥላል አልኩ።ከላይ የምትመለከትዋቸው ሶስት ሰዎች አሁን በገሃዱ ዓለም በዚህ ማንነት እየኖሩ ያሉ ናቸው።ከሶስተኛው ሰው ስንጀምር፥ በሕይወት በምድር ሳለ በስጋ ብሞት ሲዖል እገባለው ብሎ የሚኖር ሰው ነው።ይሄ ሰው ከቤተሰብቹ የወረሰው ሃይማኖት አለ፤ ነገር ግን ሃይማኖቱ የሚነግረው ኃጢአተኛ እንደሆነ ለመዳንም ብዙ ሥራ መስራት እንዳለበት፥ የምትድነው ሕግን ሁሉ አንዳች ሳታጓድል ስትጠብቅ ነው ይለዋል።በክርስቶስ በማመን የሚገኘውን ጽድቅ አምኖ መቀበል ያቃተው፣ ኢየሱስ የከፈለው ዋጋ በቂ አይደለም የእኔም ይጨመርበት የሚል፥ ነገር ግን ይሄንን ሁሉ ማድረግ እንደማይችል ስለሚያውቅ መጨረሻውን ያስቀመጠ ሰው ነው።ሁለተኛው ሰው ቢሞት የት እንደሚገባ የማያውቅ ከሞተ በኃላ የሕይወት ምርጫ ያለ የሚመስለው ልክ በስጋ ስሞት ሥራየ ታይቶ ነው ገነት or ሲዖል ግባ የምባለው ብሎ የሚያምን ነው።አንደኛው ግን ከሁለቱም ሰዎች የተለየ ነው።ገና ሳይሞት የመንግስቱ ወራሽ እንደሆነና ጽድቅን በልጁ በማመን እንዳገኘ የሚያምን መሆኑ ነው።ይሄን ያመነው ታድያ ገና በምድር በሕይወት ሳለ ባነበበው ቃል ነው።ታድያ እናንተ ከሶስቱ ሰዎች የትኞቹ ናችሁ?
@Yezelalemhiywet