Get Mystery Box with random crypto!

የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenemanchester — የኔ ማንችስተር/Yene Manchester
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenemanchester — የኔ ማንችስተር/Yene Manchester
የሰርጥ አድራሻ: @yenemanchester
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 3.96K
የሰርጥ መግለጫ

© ይህ የ የኔ ማንችስተር ይፋዊ ቻናል ነው፡፡ ስለ እንግሊዙ ሃያል ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎችም ፕሮግራሞች ባማረ እና በሚስብ ሁኔታ የሚቀርብበት ቻናል ነዉ፡፡ ለቢዝነስ ጥያቄዎች በዚህ ያግኙን።
👇👇👇
@samson21

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-24 09:07:37
የወንዶች Dog Pattern ሹራብ

Best Quality
Size: Medium, Large
Multicolor

price: 3,100 2800 birr

እዘዙን ባሉበት እናደርሳለን

@samson21

0913424435
1.6K views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:20:26
ዳሎትን በፎቶው ላይ እንደምታዩት ሳንቾ የሊቨርፑልን ጎል ጀርባ ሰጥቶ እራሱ ጎሉን እንደሚያገባው ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ አላደረበትም ነበር። ልምምድ ላይ አይቶታላ ምን እንደሚያደርግ!! የዳሎትን ወኔ እዩልኝ የመጨረሻው ፎቶ ላይ
#ኮንፊደንስ_አባቴ
1.4K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:20:04
"እያንዳንዱን ኳስ በኔ ቁጥጥር ስር ማድረግ እፈልጋለሁ። ኳሷን ለማግኘት ምንም ነገር ይሁን ምን አደርገዋለሁ!" ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ዩናይትድን እንደተቀላቀለ ከተናገረው ቃል በቃል የወሰድኩት ነው። ከመጀመሪያዋ ደቂቃ ጀምሮ ሞሃመድ ሳላህን ሲያስፈራራው ለየትኛውም ተጫዋች እንደማይመለስና ያገኘውን 50 በ 50 እድል ሰብሮም ሆነ ገድሎ እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ነበርኩ። አያክሶች 100 ሚሊየን መጠየቅ የነበረባቸው ለዚ ነበር አቦ!!
ልጁ ለማማማንም የሚመለስ አይመስልም።
#አራጅ
1.2K views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:19:33
ክሉፕ ናና ሬሳህን ሰብስብ ብሎሃል ቫራን እቺ ወይ ኳሱ ወይም ተጫዋቹ ማለፍ የለበትም የሚለው ሃሳብ አንዳንዴ ተግባራዊ ሲደረግ ያስደስታል። ቫራን ኢንስታግራም ላይ የለጠፈው ፎቶ ነው።
1.2K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:20:43
ሪዮ ፈርዲናንድ ስለ ፈርጉሰን "የሁላችንንም ቤተሰቦች ያውቃል ፣ ትንሽ ነገር ይመስላል ይሄ ነገር ግን ከኛጋ ለነበረው ግንኙነት ብቻ ስንል የማናደርግለት ነገር አልነበረም። ከሌሎቹ ለየት የሚያደርግ ነገር አለው ፤ ከሰዎች ጋር መግባባት መቻሉ እንደ አሰልጣኝነት በጣም ረድቶታል።"
ከብዙ አመታት በኋላ ይሄው የመልበሻ ክፍል ውስጥ እና ሜዳ ላይ በተጫዋቾቻችን መሀል ያለው ኬሚስትሪ ነፍስ እየዘራበት እንደሆነ አስባለሁ። ለመልካም ያድርገው
3.4K viewsSa M Son, 16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:04:51
ፖውል ስኩልስ ስለ ብሩኖ "ብሩኖ ከኔ ተለይቶ የተሻለ ተጫዋች ነው ፤ እኔ ከማስቆጥራቸው ጎሎች በላይ ያገባል ፣ ከአሲስቶቼ በላይ አሲስት ያደርጋል ፤ ምናልባትሞ ከሱ ጀርባ ሆኜ ብጫወት ደስ ይለኝ ነበር። ብሩኖ ከመምጣቱ በፊት ዩናይትዶች የጎል እድሎችን ለመፍጠር በጣም ሲቸገሩ ነበር ፤ አሁን ግን በየጨዋታው 3 ፣ 4 ወይም 5 ጎል ማግባት የሚችል ቡድን ነው የሆነው።"
2.9K viewsSa M Son, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:04:20
ዋናውን?!
አሁንም አስረግጬ እናገረዋለሁ ማርሲያል በሊጉ ካሉ በቴክኒክ ጥበብ የሚደርስበት ማንም ተጫዋች የለም። አሁን ካልተገለጠልህ ግን ጠብቅ ትንሽ አንድ ላይ እናያለን...አሽሊ ያንግ ይለወጣል ብዬ ስንት አመት እንደጠበኩት እኔ ነኝ የማቀው...አሽሊን ያን ያህል ጠብቄ ለአንቶኒ ጊዜ መስጠት አያቅተኝም።

እመኑም አትመኑም አንድ ሀቅ አለ...ቀስ በቀስ ሙሉ የጨዋታ ሙዱ እየመጣለት ነው። ተጭኖ መጫወት ፣ ኳስ አያያዝ(ተጋጣሚ ክልል ውስጥ ወሳኝ ብቃት!) እንደ እሱ ኳስን የሚይዝ ተጫዋች ቡድናችን ውስጥ የለንም፣ የፓስ ስኬቱ ፣ እንቅስቃሴው እና የጨዋታ አረዳዱ ባለፉት ሲነቀፍባቸው በነበሩ ሳምንታት ውስጥ ከማርሲያል ያየሁት ለውጥ ነበር። ዋናውን በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሚና በቅርቡ እንጠብቃለን። ሼፊልድ ላይ 1 ጎል 1 አሲስት ፣ ሊድስ ላይ 2 አሲስት እና የኤቨርተኑ ጨዋታ ላይ ደግሞ 1 ጎል እና 1 አሲስት አድርጓል...ይሄንን መስማት የሚፈልግ ሰው ቁጥር ግን ይሄን ግባ የማይባል ነው። እናንተ የሚስታቸውን ጎሎች እያነሳቹ አጥቂ አይደለም የሚል ዲስኩራቹን የምትቀጥሉ ከሆነ እኔም ይበልጥ በመነሳሳት መንፈስ ስለሱ ጥበብ ማውራቴን አልቆጥብም!
#ጥበቡ_ማርሲያል
2.1K viewsSa M Son, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:03:47
ሶልሻየር ስለ ፖግባ "ዋንጫዎችን ባነሳን ቁጥር ተጫዋቾቻችንም ለኛ መጫወት ይፈልጋሉ ፤ ፖግባ እዚ ከመጣ ቆይቷል እና ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማግኘት ይፈልጋል ፤ ልምምድ ላይ እና ኳስ ስንጫወት ቆንጆ የሆነ ስነምግባር ነው ያለው።"
1.1K viewsSa M Son, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:03:16
971 viewsSa M Son, 16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:01:58
ካይሴዶ loading...

ማንችስተር ዩናይትዶች ከኢኳዶር ሰፈር ሞይስስ ካይሴዶ የተባለ ከሳጥን ሳጥን የሚጫወት ፣ እንደ የመሀል አማካይም እንደ ተከላካይ አማካይም ሆኖ መጫወት የሚችል የ 19 አመት አማካይ ለማስፈረም ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት ንግግር አድርገዋል ፤ ተጫዋቹ በዩናይትድ የ 5 አመት ውል ለመፈረም ችግር የለበትም...(የፖግባ አድናቂ ነው) ፣ የተጫዋቹ ውል ማፍረሻ 5 ሚሊየን ፓውንድ ሲሆን ዩናይትዶች ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅርቡ ውሳኔ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
858 viewsSa M Son, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ