Get Mystery Box with random crypto!

የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenemanchester — የኔ ማንችስተር/Yene Manchester
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenemanchester — የኔ ማንችስተር/Yene Manchester
የሰርጥ አድራሻ: @yenemanchester
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 3.96K
የሰርጥ መግለጫ

© ይህ የ የኔ ማንችስተር ይፋዊ ቻናል ነው፡፡ ስለ እንግሊዙ ሃያል ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ የሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች ፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎችም ፕሮግራሞች ባማረ እና በሚስብ ሁኔታ የሚቀርብበት ቻናል ነዉ፡፡ ለቢዝነስ ጥያቄዎች በዚህ ያግኙን።
👇👇👇
@samson21

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2020-12-27 19:01:19
ሊድሶች እነማናቸው??
ዋናው ቡድን ዩናይትድ 6 ሊድስ 2
ማክ ቶሚኔይ
ብሩኖ
ሊንዴሎፍ
ጀምስ

ከ 18 አመት በታች ዩናይትድ 4 ሊድስ 0
ልማደኛው ማክኔይል
ሳቬጅ
ኢባል

ከ 16 አመት በታች ዩናይትድ 4 ሊድስ 1
ዌትሊ
ኪንግደን
ኦዬዴሌ

ከ 15 አመት በታች ዩናይትድ 4 ሊድስ 1
አጠቃላይ ውጤት? ማንችስተር ዩናይትድ 18 ሊድስ ዩናይትድ 4
ወንዶቹ ሊድስ ላይ ሴቶቻችንም ብሪስቶል ሲቲ ላይ 6 ጎሎችን ማግባታችን ገርሞኝ ሳያበቃ የሙሉ ቡድኑ ውጤት ቅርጫት ኳስ መስሎልኛል ለካ።
ጀግና ሴቶቻችን የሚጫወቱበት ሊግ የሉም እንጂ 10 በያይነታቸውን ጠጥተዋት ነበር
#Sami
893 viewsSa M Son, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-27 19:00:18
እዩልኝ የዚን ቅመም ደስታ
1.2K viewsSa M Son, 16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:33:48
የጨዋታ ሀይላይት
ማንችስተር ዩናይትድ 6 ሊድስ ዩናይትድ 2
1.5K viewsM, edited  15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:26:16
1 ወር ከ 20 ቀን በፊት በአርሰናል ከተሸነፍን በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ የጣልናቸው ነጥቦች ብዛት አርሰናሎች ካገኙት ጋር እኩል ነው ፤ የጣልነውም እነሱም ያገኙት ነጥብ 2 ነው። ነገሮች ሲገለበጡ እንዲሁ ነው ያንን ጨዋታ ግን እንዴት ሆነን እንደተሸነፍን አሁንም እንቆቅልሽ ሆኖብኛል! ቅዳሜ 7 ለ 0 በሜዳው ሲደበደብ ከዋለና የወራጅ ቀጠና ውድድር ውስጥ ካለ ቡድን ጋር ነጥብ መጣላችን ያስቆጫል!
#Sami
1.7K viewsM, 15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:18:52
ለ 12ኛ ሳምንት ስልካቹን ማሳመሪያ ፎቶ! Wallpaper ካረጋቹ በኋላ ስልካቹ እንዳይከብዳቹ ልጁ ከባድ ሚዛን ነው
#Sami
1.3K viewsM, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:18:31
እዚጋ የማክ ቶሚኔይን 2ኛ ጎል የአጨራረስ ብቃት እና ጥበቡ ማርሲያል የሰራውን ስራ ሳያደንቁ ማለፍ ይከብዳል!! የመጀመሪያው ምስል ላይ እንደምታዩት ሉክ ሾው ወደ ማርሲያል የእጅ ውርወራውን ወርውሮ ስኮት ደግሞ እንደነገርኳቹ ሊድሶች ጥለውት የሄዱትን ክፍተት ያስተውላል። ሁለተኛው ምስል ላይ ደግሞ ማርሲያል ኳሱን እንደተቀበለ ከጀርባው ካለው ተከላካይ ጋር በመጋፋት ኳሱ ከእግሩ እንዳትወጣ እያደረገና ስኮት ደግሞ ያስተዋለውን ሊድሶች የከፈቱትን ሰፊ ቦታ ለመጠቀም በሀይል ሲሮጥ ይታያል ፤ 3ኛው ምስል ላይ ማርሲያል እግሩ ላይ ተጋፍቶ ያቆየውን ኳስ ወደክፍት ቦታው መስመር ሰባሪ ፓስ በማድረግ ለስኮት እያቀበለው ይታያል ፤ 4ኛው እና የመጨረሻው ምስል ላይ ደግሞ ስኮት ያለፈለትን ኳስ በቀኝ የውስጥ እግሩ ወደግራ እግሩ ገፋ በማድረግ በግራ እግሩ በቆንጆ አጨራረስ ያገባዋል!
መጀመሪያም አካዳሚ ውስጥ አጥቂ ሆኖ ስለተጫወተ የስኮት እይታ እና አጨራረስ አልገረመኝም ፤ ጥበቡ ማርሲያል እና ስኮት ግን ምርጥ እንቅስቃሴ ነበር ያሳዩት እዚጋ ሼር እያረጋቹ
#Sami
1.1K viewsM, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:16:22
ያስጠጣል!!
ጨዋታው ሊጀመር ደቂቃዎች ሲቀሩት ሊድሶች ጥለውት የሚሄዱትን ክፍተቶች መጠቀም እንደሚገባን ፅፌላቹ ነበር ፤ የማክ ቶሚኔይ የመጀመሪያ ጎል ለዚ እይታ ምርጥ ማሳያ ነው ፤ የጎሉን ቪዲዮ ፈልጋቹ እዩትና የፃፍኩላቹን አስተውሉ። ጨዋታው ከተጀመረበት ደቂቃ አንስቶ የኦሌ ልጆች አልባዘኑም ነበር ፤ ኳሷ ልክ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ስትገባ ማክ ቶሚኔይ ባልተለመደ መልኩ ከመሀል አማካዮቻቸው ጀርባ የነበረውን ትልቅ እና በቂ ክፍተት በፍጥነት ነው የተጠቀመበት። የስኮት ማክ ቶሚኔይ ፣ ጀምስ እና ማርሲያል ለዚ አጨዋወት ሚና ከፍተኛ ነበር...ለዚህም ምንም አያውቅም ለምትሉት አሰልጣኝ ምስጋና ይድረስ ድክመትህን አውቆ እንዲ ሲወጋህ በደንብ ያስጠጣል!
የስኮትን ሁለተኛ ጎል ትንተና ከደቂቃዎች በኋላ ከፎቶ ጋር አያይዤ እለጥፍላችኋለው።
#Sami
698 viewsM, 15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:15:53
ማክ ቶሚኔይ ከጨዋታው በኋላ የሰጠውን አስተያየት ካያቹት ፈርጊ ፣ ሞሪንሆ አሁን ደግሞ ኦሌ ለምን ስኮትን እንደሚወዱ ይገባችኋል። የበሰለ ስራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ታታሪ ሰራተኛ ነው ፤ በቴክኒክ ከሌሎቹ አማካዮች ሊያንስ ይችላል ነገር ግን ከሱ የሚገኘው የጥቅም ብዛት ብቻውን ይጮሃል!
ከቃለ ምልልሱ በጥቂቱ ከሰማሁት የተወሰዱ"መልበሻ ክፍል ውስጥ ይሄንን ነበር ስናገር የነበረው ፤ በሜዳችን ስንጫወት ብዙ ጎሎችን አግብተን ቡድኖች እኛን መግጠም እንዲፈሩ ማድረግ አለብን ፤ ኦልድ ትራፎርድን የማይወጡበት ምሽግ ነው ማድረግ ያለብን። የደረጃ ሰንጠረዡን አናይም...ለሱ ጊዜ የለንም እኛ።"
በመጀመሪያዎቹ 3 ደቂቃዎች 2 ጎሎችን በማግባት በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
#Sami
619 viewsM, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-21 18:15:29
ማርከስ ራሽፎርድ የ ቢቢሲ የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት ላይ ለሁሉም ህፃናት ምግብ ይድረስ ብሎ ባስነሳው ስራ አማካይነት የልዩ ሽልማት አሸናፊ ሆኗል። የትንሽ ትልቅ! ይገባሃል
#Sami
569 viewsM, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ