Get Mystery Box with random crypto!

እዚጋ የማክ ቶሚኔይን 2ኛ ጎል የአጨራረስ ብቃት እና ጥበቡ ማርሲያል የሰራውን ስራ ሳያደንቁ ማለፍ | የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

እዚጋ የማክ ቶሚኔይን 2ኛ ጎል የአጨራረስ ብቃት እና ጥበቡ ማርሲያል የሰራውን ስራ ሳያደንቁ ማለፍ ይከብዳል!! የመጀመሪያው ምስል ላይ እንደምታዩት ሉክ ሾው ወደ ማርሲያል የእጅ ውርወራውን ወርውሮ ስኮት ደግሞ እንደነገርኳቹ ሊድሶች ጥለውት የሄዱትን ክፍተት ያስተውላል። ሁለተኛው ምስል ላይ ደግሞ ማርሲያል ኳሱን እንደተቀበለ ከጀርባው ካለው ተከላካይ ጋር በመጋፋት ኳሱ ከእግሩ እንዳትወጣ እያደረገና ስኮት ደግሞ ያስተዋለውን ሊድሶች የከፈቱትን ሰፊ ቦታ ለመጠቀም በሀይል ሲሮጥ ይታያል ፤ 3ኛው ምስል ላይ ማርሲያል እግሩ ላይ ተጋፍቶ ያቆየውን ኳስ ወደክፍት ቦታው መስመር ሰባሪ ፓስ በማድረግ ለስኮት እያቀበለው ይታያል ፤ 4ኛው እና የመጨረሻው ምስል ላይ ደግሞ ስኮት ያለፈለትን ኳስ በቀኝ የውስጥ እግሩ ወደግራ እግሩ ገፋ በማድረግ በግራ እግሩ በቆንጆ አጨራረስ ያገባዋል!
መጀመሪያም አካዳሚ ውስጥ አጥቂ ሆኖ ስለተጫወተ የስኮት እይታ እና አጨራረስ አልገረመኝም ፤ ጥበቡ ማርሲያል እና ስኮት ግን ምርጥ እንቅስቃሴ ነበር ያሳዩት እዚጋ ሼር እያረጋቹ
#Sami