Get Mystery Box with random crypto!

ያስጠጣል!! ጨዋታው ሊጀመር ደቂቃዎች ሲቀሩት ሊድሶች ጥለውት የሚሄዱትን ክፍተቶች መጠቀም እንደሚ | የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

ያስጠጣል!!
ጨዋታው ሊጀመር ደቂቃዎች ሲቀሩት ሊድሶች ጥለውት የሚሄዱትን ክፍተቶች መጠቀም እንደሚገባን ፅፌላቹ ነበር ፤ የማክ ቶሚኔይ የመጀመሪያ ጎል ለዚ እይታ ምርጥ ማሳያ ነው ፤ የጎሉን ቪዲዮ ፈልጋቹ እዩትና የፃፍኩላቹን አስተውሉ። ጨዋታው ከተጀመረበት ደቂቃ አንስቶ የኦሌ ልጆች አልባዘኑም ነበር ፤ ኳሷ ልክ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ስትገባ ማክ ቶሚኔይ ባልተለመደ መልኩ ከመሀል አማካዮቻቸው ጀርባ የነበረውን ትልቅ እና በቂ ክፍተት በፍጥነት ነው የተጠቀመበት። የስኮት ማክ ቶሚኔይ ፣ ጀምስ እና ማርሲያል ለዚ አጨዋወት ሚና ከፍተኛ ነበር...ለዚህም ምንም አያውቅም ለምትሉት አሰልጣኝ ምስጋና ይድረስ ድክመትህን አውቆ እንዲ ሲወጋህ በደንብ ያስጠጣል!
የስኮትን ሁለተኛ ጎል ትንተና ከደቂቃዎች በኋላ ከፎቶ ጋር አያይዤ እለጥፍላችኋለው።
#Sami