Get Mystery Box with random crypto!

ማክ ቶሚኔይ ከጨዋታው በኋላ የሰጠውን አስተያየት ካያቹት ፈርጊ ፣ ሞሪንሆ አሁን ደግሞ ኦሌ ለምን | የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

ማክ ቶሚኔይ ከጨዋታው በኋላ የሰጠውን አስተያየት ካያቹት ፈርጊ ፣ ሞሪንሆ አሁን ደግሞ ኦሌ ለምን ስኮትን እንደሚወዱ ይገባችኋል። የበሰለ ስራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ታታሪ ሰራተኛ ነው ፤ በቴክኒክ ከሌሎቹ አማካዮች ሊያንስ ይችላል ነገር ግን ከሱ የሚገኘው የጥቅም ብዛት ብቻውን ይጮሃል!
ከቃለ ምልልሱ በጥቂቱ ከሰማሁት የተወሰዱ"መልበሻ ክፍል ውስጥ ይሄንን ነበር ስናገር የነበረው ፤ በሜዳችን ስንጫወት ብዙ ጎሎችን አግብተን ቡድኖች እኛን መግጠም እንዲፈሩ ማድረግ አለብን ፤ ኦልድ ትራፎርድን የማይወጡበት ምሽግ ነው ማድረግ ያለብን። የደረጃ ሰንጠረዡን አናይም...ለሱ ጊዜ የለንም እኛ።"
በመጀመሪያዎቹ 3 ደቂቃዎች 2 ጎሎችን በማግባት በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
#Sami