Get Mystery Box with random crypto!

ዋናውን?! አሁንም አስረግጬ እናገረዋለሁ ማርሲያል በሊጉ ካሉ በቴክኒክ ጥበብ የሚደርስበት ማንም | የኔ ማንችስተር/Yene Manchester

ዋናውን?!
አሁንም አስረግጬ እናገረዋለሁ ማርሲያል በሊጉ ካሉ በቴክኒክ ጥበብ የሚደርስበት ማንም ተጫዋች የለም። አሁን ካልተገለጠልህ ግን ጠብቅ ትንሽ አንድ ላይ እናያለን...አሽሊ ያንግ ይለወጣል ብዬ ስንት አመት እንደጠበኩት እኔ ነኝ የማቀው...አሽሊን ያን ያህል ጠብቄ ለአንቶኒ ጊዜ መስጠት አያቅተኝም።

እመኑም አትመኑም አንድ ሀቅ አለ...ቀስ በቀስ ሙሉ የጨዋታ ሙዱ እየመጣለት ነው። ተጭኖ መጫወት ፣ ኳስ አያያዝ(ተጋጣሚ ክልል ውስጥ ወሳኝ ብቃት!) እንደ እሱ ኳስን የሚይዝ ተጫዋች ቡድናችን ውስጥ የለንም፣ የፓስ ስኬቱ ፣ እንቅስቃሴው እና የጨዋታ አረዳዱ ባለፉት ሲነቀፍባቸው በነበሩ ሳምንታት ውስጥ ከማርሲያል ያየሁት ለውጥ ነበር። ዋናውን በተደጋጋሚ የጎል ማግባት ሚና በቅርቡ እንጠብቃለን። ሼፊልድ ላይ 1 ጎል 1 አሲስት ፣ ሊድስ ላይ 2 አሲስት እና የኤቨርተኑ ጨዋታ ላይ ደግሞ 1 ጎል እና 1 አሲስት አድርጓል...ይሄንን መስማት የሚፈልግ ሰው ቁጥር ግን ይሄን ግባ የማይባል ነው። እናንተ የሚስታቸውን ጎሎች እያነሳቹ አጥቂ አይደለም የሚል ዲስኩራቹን የምትቀጥሉ ከሆነ እኔም ይበልጥ በመነሳሳት መንፈስ ስለሱ ጥበብ ማውራቴን አልቆጥብም!
#ጥበቡ_ማርሲያል