2022-11-16 20:28:15
የሴትን ልጅ ልብ ለመማረክ እና ቀጣይነት ያለው
ግንኙነት ለመመስረት የሚረዱ 6 ነጥቦች
part_4{መጨረሻ}
6. Sex (ወሲብ)
በተጣማሪዎች መካከል ፍቅር ሰምሮ ኑሮ እንዲደረጅ፣
በሐሳብ እና ፍላጎት መጣጣም ተቀዳሚው መሆኑ
የማያጠያይቅ ሀቅ ነው፡፡ መከባበሩ፣ መፈቃቀሩና የሐሳብ
መጣጣሙ እንደተጠበቀ ሆኖ በወሲብ አለመጣጣም
ባለትዳሮች ከትዳራቸው ውጪ ሌላ ሰው መጎብኘታቸው
የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡
ብዙውን ጊዜ ተጣማሪዎች፣ የሐሳብ አለመጣጣምን
አቻችለውና ተቻችለው ኑሮን ሲገፉ ይስተዋላል፡፡ በአሁኑ
ዘመን እየተስተዋለ የመጣው እውነታ እንደሚያመለክተን
ግን በወሲብ አለመጣጣምን ማስታመም
ስለሚያቅታቸው ወይም ከሌላ ጋ ሲማግጡ ወይም
ከነጭራሹ ትዳርን ሲያፈርሱ ይታያሉ፡፡
በአብዛኛው በርካታ ወሲብ ነክ ፅሑፎችና ጥናቶች አንድን
ወንድ እንዴት ለወሲብ ማነሳሳት እንዳለብን እና እንዴት
እርካታ ላይ እንዲደርስ መርዳት እንዳለብን የሚገልፁ
ናቸው፡፡ ይህም የሚያሳየው የሴት ልጅ ስሜት ይሄ ነው
የሚባል አትኩሮት ከማህበረሰቡ ጭምር
እንዳልተቸገረው ነው፡፡
Nora Hayden (How to satisfy a women every
time) በተሰኘው መጽሐፏ ላይ እንደገለፀችው 80%
የሚሆኑት ሴቶች፣ እውነተኛ እርካታ ላይ እንደሚደርሱ
ሆኖም የትዳር አጋራቸውን ለማስደሰት ሲሉ ብቻ እርካታ
ላይ እንደደረሱ እንደሚያስመስሉ ይናገራሉ፡፡ ይህም
የሚሆነው ወንዶች በወሲብ ጊዜ የሴትን ልጅ ፍላጎት
እና የስሜት ምስጢር መረዳት ስለሚያቅታቸው እነሱ
በሚረኩበት መንገድ ይረካሉ ብለው በማሰብ ዘልማዳዊ
የሆነውን ግንኙነት ያደርጋሉ፡፡ ሆኖም ፈጣሪ ወሲብን
በትዳር መካከል እንድትደሰትበትና ትውልድን
እንድናስቀጥልበት የሰጠን ታላቅ ፀጋ በመሆኑ፣ የሴትም
ልጅ ስሜት መጠበቅ እና በባሏ መደሰት እንዳለባት
በመረዳት በግልፅ በመወያየትም ሆነ በዘርፉ የተፃፉ
ጽሑፎችን በማንበብ፣ ደስታውን የጋራ የማድረግ
የወንዶች ተቀዳሚ ኃላፊነት ነው፡፡
በመጨረሻ ማንሳት የምፈልገው ነጥብ፣ ብዙዎች
በትዳር ላይ በግንኙነት ዙሪያ በመርህ ደረጃ የሚነሱ
ጠቃሚ ምክሮችን ማንበብ ፋይዳ ቢ መሆኑን ሲናገሩ
ይታያል፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያነሱት
መከራከሪያ የፀሐፊዎቹ ወይም አነበብን የሚሉ ሰዎችን
ግለ ህይወት በናሙናነት በማንሳት፣ በትዳር ህይወታቸው
ስኬታማ አለመሆናቸውን ነው፡፡ እዚህ ጋ መረዳት ያለብን
ቁም ነገር፣ ችግሩ ያለው ከዕውቀቱ ወይም ከንባቡ
ሳይሆን ያወቅነውን እና የሰማነውን በልቦናችን አኑረን
መተግበር ስለሚሳነን መሆኑን ነው፡፡ በመሆኑም ተፈጥሮ
የለገሰችን ሰብዕና፣ በህይወት ተሞክሮ እና ዕውቀት
በማዳበር፣ ያካበትነውን ዕውቀት በመተግበር እና ለውጥ
በማምጣት ትዳራችን በግምት ሳይሆን፣ በጥበብ
የምንመራትን ልቦና ይስጠን፡፡
ሴት ልጅ ምን መስማት አትሻም!
ሴቶች ስለ ሌላ ሴት ወይም ስለ ቀድሞ ጓደኛህ
ስታደንቅ መስማት አትፈልግም፡፡ ከሌላ ሴት ጋር
እንድታወዳድራትም እንዲሁ፡፡ ስለ ሰውነት ቅርጽና ውበቷ
አድናቆት እንጂ ነቀፌታ ቅር ያሰኛታል፡፡ በድንገት
ተሳስተህ የሌላ ሴት ስም ማንሳትም አይኖርብህም፡፡
በሌላ መንገድ ያስጠረጥርሃልና፡፡ ከአሁን ቀደም በነበረህ
የሴት ልጅ ትውውቅ ውስጥ አላግባ ያደረካቸውን ነገሮች
ማውራትህ ከባድ ግምት ውስጥ ይጥልሃልና በተቻለ
መጠን ከኋላ ፈቅር ታሪክህ ውስጥ ጥሩ ጥሩውን እንጂ
የሚያስተችህን ለመርሳት ወይም ላለማንሳት ጥረት
አድርግ፡፡ በሌላዋ ላይ ይህን ያደረገ በእኔም ላይ ማድረጉ
አይቀርም የሚል እምነት ይኖራታልና፡፡ ሴቶች ስለ አንተ
ማወቅ የሚፈልጉትን ሲጠይቁህ እውነቱን መናገሩን ብቻ
ነው የሚያዋጣው፡፡ ብዙ ጊዜ ሴቶች ለማወቅ
በሚመስል መልኩ ይጠይቃሉ እንጂ የሚጠይቁትን ነገር
ቀድሞውኑ ያውቁታልና አትዋሽ!
በተቻለ መጠን ከአሁን ቀደም ከነበረህ የፍቅር ትስስር
እንዴት እንደተለያየህ ምክንያትህን አሳማኝነት ያለውና
ከአንተ በኩል ከፍተኛ ጥረት ማድረግህ ላይ ያነጣጠረ
ይሁን እንጂ ኃላፊነትህን ስላለመወጣትህ የሚያንፀባርቁ
ምክንያቶችን ወይም ደግሞ ቀድሞውኑ ለመለያየት
የማያበቁ ምክንያቶችህን ሴቶች መስማት አይፈልጉም!!
· · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @zii_zuo
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
336 views17:28