Get Mystery Box with random crypto!

ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤ Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤
የሰርጥ አድራሻ: @wubyefkr_kalat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.49K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-03 14:20:03
#የድሀ_ፍቅር

እጅግ አጓጊ ምርጥና አስተማሪ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ።

በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የቴሌግራም ቻናል ላይ ዛሬ ምሸት ...
Join and share
@wubyefkr_kalat
314 viewsedited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 23:15:35 ​​አንቺ በህይወቴ ስላለሽ ብቻ ህይወት ታጓጓኛለች

የልቤ ዋና ክፍል አንቺ ነሽ እማ...




‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · ·• • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat
,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
454 views20:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 22:54:45 ​​ለምንድነው ዛሬም ማስብሽ እ ካወራን ቆይተናል....ከተያየንም ስንት ጊዜያችን ግን አሁንም ልቤ ውስጥ የሆነ ቦታ ይዘሻል ግን የት ይገባሻል

      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
439 views19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-01 10:45:00 ጣፋጭ የፍቅር ቃላት
አንቺን ለመሳም የመጨረሻው እስከሆንኩ ድረስ መጀመሪያ ማንም ቢስምሽ ግድ የለኝም።

ከልባቸው ሚያፈቅሩ ቶሎ አያረጁም።

ምን አልባት አንድ ቀን ምን ያክል አፈቅርህ እንደነበር ትረዳ ይሆናል ታዲያ አንተም ተፀፅተህ ልታፈቅረኝ ትሞክር ይሆናል ያኔ ግን አንተን እየጠበኩ ላይሆን ይችላል

ከልብሽ የሚወድሽ ሰው አይጎዳሽም።ም/ክ ከጎዳሽ ጉዳትሽ አይኖችሽ ውስጥ ይመለከታልና።ይህ ደሞ እሱንም ይጎዳዋል።

ላንቺ ሁሉንም ነገርሽ ለሆነ ለሱ ግን ምንም እንዳልሆንሽ ከተረዳሽው ጎን መቀመጥ በእርግጥ ያማል

ያገኘሀትን ሴት በቀላሉ እንዳገኘሀት ከማሰብ ይልቅ በፍቅር ልትይዛት ይገባል ም/ክ ድንጋይ ስትሰበስብ እንቁህን ልታጣ ትችላለህና።

ፍቅር ይብዛላቹ መልካም ቀን

· · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
51 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 19:40:00 #ተወዳጁ


የመጨረሻው ክፍል.....





ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን፤ግን እኔ ከ5 ደቂቃ በላይ አብሬያቸው ሆኜ ለመጠበቅ ፍቃደኛ አልሆንኩም።ሮቢ አጠገቤ መጥቶ ግን የኔ አለመሆኑን ማሠብ ሞት ስለሆነብኝ ወደ ቤቴ መሄድ ፈለኩኝ፤ጓደኛዬም እያመመኝ ስለነበር ተጨንቃ ወደ ቤት አብራኝ ሄደች።እቤት ካደረሰችኝ በኀላ ተመለሠች፤ልክ እሧ ስትወጣ ጠብቄ ባለቅስ ምመልሠው ይመስል ስንት ዘመድ የሚቀብረውን እንባዬን አፈሠስኩ።ሣላስበው የእናቴ ባል መጥቶ ከተኛሁበት አልጋ አጠገብ ከተቀመጠ በኀላ በጣም ደንግጦ ሮቢ ምን ሆነ ብሎ ጠየቀኝ፤እኔም ግራ እንየተጋባው ሮቢ የሆነ ነገር ሆኖ ነው ብለህ እነሸዴት አሠብክ አልኩት፤ያው ሠሞኑን ሀሳብሽም ጭንቀትሽም እሡ ስለነበር ነው አለኝ።ከመጀመሪያው ይበልጥ በጣም እያለቀስኩ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት፤ምንም ሊያምን አልቻለም ሮቢ አንቺ ላይ ይሄን አያደርግም አለኝ።እናቴ ጉዳይ ለማስፈፀም ሌላ ቦታ ነበረች፤በስልክ ነግሯት ነው መሠለኝ በነጋታው ት/ቤት መጣች።እሧ ስትመጣ የወደ ቤት ሠአት ደዉል ሊደወል የመጨረሻው ክፍለ ጊዜ ነበር፤ከክፍል ካስጠራችኝ በኀላ ት/ቤት ግቢ ውስጥ እንዴት እንደገባ ባላውቅም ሮቢ እኛ ወደቆምንበት ቦታ እየመጣ ነበር፤እየተንተባተብኩ ሮቢ አልኳት ለእናቴ ዞራ አየችውና ጎሽ እንደውም አናግረዋለው አለችኝ።እኔ ግን ልጅቷ የነገረችኝ ጆሮዬ ላይ ሲያቃጭልብኝ በፊት እንደዛ ለማቀፍ ምስገበገበውን ሮቢ ዛሬ ግን አጠገቡ መቆም አልሆንልሽ ቢለኝ አጠገባችን ሣይደርስ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ክፍል ተመለስኩ።ክፍል እንደገባው ወዲያው ስለተደወለ ለጓደኛዬ የሆነውን ነግሬያት ቦርሳችንን ይዘን ወደ ውጪ ወጣን፤ሮቢ እና እናቴ እያወሩ ነበር።ከግቢው ከወጣን በኀላ እናቴ ትንሽ ቆይታ መጥታ ሮቢን ድጋሜ ስለምታዋራው እዚው ከኤልሹ(ጓደኛዬ) ጋ አብረን እንድንሆን ነገረችን።ሮቢም ብዙም ሣይቆየሸ ወጥቶ ከእናቴ ጋ ቆመው ብዙ ሲያወሩ ከቆዩ በኀላ እናቴ ተመልሳ መጣች።ሮቢ ያላትንም እየነገረችኝ ወደ ቤት መሄድ ጀመርን።ሮቢ እኔ ላይ እንደዛ ያደረገበት ምክንያት በጣምምምም ሚገርም ነበር፤አስት ከኔ ጋ ያለውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ ስለነገረችው ነበር፤ይገርማል አይደል እንዴ በጣምምም እንጂ ምክንያቱም ለኛ አብረን እንዳንሆን መከልከል ብርቃችን አልነበረማ፤በጣም ብዙ ችግሮችን አልፈን ፍቅራችንን ማንም እንዳይንደው አጠንክረነው ነበራ፤የኔ እናት ከአንዴም ሶስቴ ስትከለክለን ለፍቅራችን ቦታ ሠጥቼ አብረን እንዳልተጋፈጥን እሡ ይሄ ከብዶት ከኔ ወደ ሌላ ሴት ፊቱን አዞረ።ሮቢ ሊያገኘኝም ሆነ ሊያዋራኝ ምንም አልሞከረም ነበር፤እንዲያውም ይባስ ብሎ ለኔ ስሜት ምንም ሳይጨነቅ ፍቅሬ ምኔ እያለ ከልጅቷ ጋ ሚነሡትን ፎቶ fb ላይ በጣም በብዛት መልቀቅ ጀመረ።ከዛ በኀላ የነበሩት በወራት የሚቆጠሩ ወራቶች ለኔ እጅግ በጣም አስቸጋሪ እና አሳሳቢ ነበሩ።በአባቴ በእናቴ እና በተለያዩ ሠዎች ምክር ወደ ራሴ መመለስ ጀመርኩ። ያ ሀገር ምድሩን ያሰቀናና ምሣሌ የነበረው ፍቅር ዛሬ ሰብሳቢ አጥቶ ተበትኗል፤ሮቢን ከማንም ይበልጥ ማመኔ በብዙ ነገሮች ጎዳኝ።አንተ ለፍቅራችን ምንም መሰዋትነት መክፈል አልቻልክም፤መቼም ቢሆን ግን አንተ ላይ ፈርጄብህ አላውቅም ያዋጣህ መስሎህ ንፁህ ፍቅሬን ረግጠህ ሄደሀል።
ህይወት ሠንሠለት ናት፤አንዱ አንዱን ሲፈልግ ሚፈለገው ደሞ ሌላ ይፈልገል።ህይወት የማትፈታ ቅኔ ናት፤እጅግ ብዙ ነገሮችን አሠባጥራ የያዘች።ህይወት ስሌት ናት፤አንዱን እየቀነስን ሌላውን ምንተካባት።ግን ከምንም በላይ ሀያል የሆነው ፍቅር ህይወት ነው ይሄን ሁሉ ነገር አንድ ላይ አቀናጅቶ የያዘ፤ሁሉም ሠው ልብ ውስጥ ያለ ግን አውቆ ለተጠቀመበት ብቻ ደስታን ምታጎናፅፍ።።።።።።።።


።።።።ተፈፀመ።።።።


· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr\kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
153 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 17:17:51 #ተወዳጁ
የተሰኘው ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ዛሬ ምሽት የመጨረሻው ክፍል ይለቀቃል።


╰── ──╯
••●◉Join us share◉●•• @wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
174 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 17:05:42 • • ጣፋጭ ቃላት • • •· ·

የኔ ፍቅር

ያኔ  አንቺን ያወኩባት ቀን ለኔ መኖር የጀመርኩበት ቀን ነበረች
ያኔ ያወኩሽ ቀን ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ያወኩ ያህል ነበር የተሠማኝ
ታውቂያለሽ አይደል አሁንም ቢሆን ሴት
ለኔ አንቺ ብቻ ነሽ ከአንቺ በላይ ብዙ እንዳሉ ባቅም ልቤ ግን አያምንም     

    ከወደዱት አጋሩ


╰── ──╯
••●◉Join us share◉●•• @wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
175 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 19:40:00 #ተወዳጁ

|ክፍል 15|


የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር አለችኝ። እንዴት ያስቃል ለካ የራሴን ጉድ ነበር ምክር ስሰጥበት የቆየሁት ሁሌ ክፍል በመጣች ቁጥር ቅድስት እኮ አብርሽ እንዲህ አርጓት እያለች የራሴን ታሪክ ትነግረኛለች፤አንቺ ብትሆኚ ምን ታደርጊ ነበር እያለች ስለምትጠይቀኝ እኔም ራሴን በቦታው አድርጌ እያሠብኩ እነግራት ነበር።የነገረችኝ ታሪክ<አብርሽ ቅድስትን ሳያዋራትም ሳያገኛትም እነሡ ት/ቤት ምትማረዋን ልጅ ግን ሁሌ ጠዋት ጠዋት ት/ቤት ድረስ ይሸኛታል፤እና የtg profilun የልጅቷን ፎቶ ነው እያቀያየረ ሚያረገው ቅድስት ግን ይሄን አታቅም ብነግራት ምን ታስቢያለሽ> ስትለኝ <ብትነግሪያት ጥሩ ነው ግን እኔ እሧን ብሆን የምልሽ ምናልባት የtg profile ማድረጉ የgame ትዕዛዝ ይሆናል፤ት/ቤት መሸኘቱም ቢሆን በአጋጣሚ እየተገናኙ ይሆናል።ግን ሮቢ እኔ ምማርበት ት/ቤት ድረስ እየመጣ ባያገኘኝ ስለ እውነት በጣም ነው ቅር የሚለኝ>አልኳት።እሧም እንደመናደድ እያለች<ይሄን ያህል ማመንም በኀላ ሚጎዳው ራስሽን ነው፤ትንሽ ተጠራጠሪ>ትለኝ ነበር።እኔም በሀሳቧ ስላልተስማማው የሁል ጊዜ ጭቅጭቃችን ነበር።እና የነገርኩሽ ታሪክ ያንቺ ነው ያለችኝ ይሄ ነበር፤እኔ እያለቀስኩ ከዚ በላይ እንዳትነግረኝ በአይኔ ከመለማመጥ ውጪ ምንም አላደረኩም።እሧ ቀጠለች<የገና ጊዜ ተዘጋጅቶ ሁሉም ተማሪ ሄዶ አንቺ ብቻ ያልሄድሽበት ፓርቲ ላይ እዛው አብሯት ሲጨፍር ከነበረችው ልጅ ጋ ሲሳሳም ነበር>አለችኝ።ከዚ በላይ መስማት አልቻልኩም፤በጣም አመመኝ። እረፍት ሠአት ደርሶ ስለነበር እንደ ምንም ጓደኞቼ አረጋግተውኝ ስላላመንኳቸው ስልኩን ነግሬያቸው tg ላይ search አድርገው profilun አሣዩኝ፤ከዚ በላይ ለሡ ምከራከርበት አቅም አጣው።profilu ላይ የሧ በዛ ያሉ ፎቶዎች እና ሁለቱ የተፃፃፉትን screenshot ተደረጎ ነበር፤ፅሁፉ የሚለዉ
<ፍቅሬ
ወዬ
አሸነፍኩሽ አይደል
ላንተ ስለሆነ ነዋ
እሺ አፈቅርሻለው
እኔም በጣም እወድሀለው አፈቅርሀለው>
ነበር።ፓርቲው ላይ የነበሩ ከግማሽ የማያንሱ የክፍላችን ተማሪዎችም ሲሳሳም እንዳዩት ነገሩኝ።ግን በጣም የሚገርመው እስካሁን የሇነ ስህተት እንዳለ እንጂ ሮቢ ይሄን ያደርጋል ብዬ መቀበል አልቻልኩም።አለማመኔ የገባቸውም ጓደኞቼ በምሳ ሠአት ላይ እውነቱን ሁሉ እሧ እንድትነግረኝ የልጅቷ ክፍል ይዘውኝ ሄዱ።ልጅቷን ጠርተናት ከመጣን በኀላ ጓደኛዬ ሁሉን ነገር እንድትነግረኝ ጠየቀቻት፤ልጅቷ መጀመሪያ ልትሸፋፍነው ብትሞክርም ጓደኛዬ አፋጣ ስለያዘቻት ሁሉንም ነገረችኝ ጓደኞቼ ከነገሩኝም ሌላ ብዙ ነገር ነገረችኝ አሁንም ካላመንሽ ደሞ እደውልለታለው ብላ ደወለችለት፤መቼም እኔ ከሣምንት የበለጠ ጊዜ ስደዉልለት ሣያነሳ ለሧ እንደማያነሳ እርግጠኛ ሆኜ ነበር፤ግን እሡ ምን በወጣው ብዙም ሣይጠራ አንስቶላት በኅላ ት/ቤት መጥቶ እንደሚያገኛት ተነጋግረው ስልኩ ተዘጋ።እኔም ጉዴን አውቄ እንባዬን እየዘራው ወደ ክፍል ሄድኩኝ፤ምንም ሣልናገር ሣልጋገር ወደ ቤት መሄጃ ሠአታችን ደረሠ።ልጅቷ መጥታ ለምን አሁን ሲመጣ ሁለታችን አብረን ሆነን አናፋጥጠውም አለችኝ፤ምንም አልመለስኩላትም ጓደኛዬ ግን በሀሳቧ ተስማምታ ውጪ ሆነን መጠበቅ ጀመርን።

ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
229 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:40:00 #ተወዳጁ


|ክፍል 14|


ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።በዛ ላይ እኔም ስልኬ ጠፍቷል እንደ በፊቱ አናወራም፤አሁን ገና ርቀታችን እየተሠማኝ መጣ።ሮቢን እንደ በፊቱ ባላገኘውና ባላወራውም ለሡ ያለኝ ፍቅር ቅንጣት እንኳን አልቀነሠም ነበር፤እንዲያውም ከነሠፍቆቱ ጋ ተደምሮ ፍቅሩ እጅግ በረታብኝ።ከ9 ወደ 10ኛ ክፍል ያለፍኩት ያው እንደተለመደው በደረጃ ቢሆንም የዘንድሮ ግን ያሳስባል፤ጥር ወር ውስጥ የ1st semester final exam ስለነበር ለማጥናት ብሞክርም አልቻልኩም፤ሀሣቤ ሁሉ ሮቢ ሆኗል።አሁንማ በስልክ እንኳን ካወራን 1 ሳምንት ከ3ቀን ሆኖናል።ጥር 14/2010አ.ም ማክሰኞ ቀን ከጊዜ በኀላ እንዳመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ክፍል ውስጥ ቆዝሜ ተቀምጬ አንድ ጓደኛዬ መጥታ አጠገቤ ተቀመጠችና<ኧረ ምንሼ ርብቂ ሮቢ ሚሠራው ስራ ምንም አይነፋም fb ላይ ሚለቃቸው ፎቶዎች እና ሚሠጣቸው comment አንቺን ሲያፈቅርሽ ከነበረው ሮቢ አይጠበቅም>አለችኝ።ለራሴ ግራ ገብቶኝ ብቻዬን እያወራው መሄድ ነው የቀረኝ እሧ እንደዛ ብላኝ አዞረችብኝ።ግን ለሮቢ ያለኝ እምነት እንዲህ በቀላሉ ሚበገር ስላልነበር<በሮቢ account ሌላ ሠው እየተጠቀመ ይሆናል አልኳት፤እሺ እራስሽ አይተሽ ፍረጂ ብላ ከእናቱ ጋ ሆኖ የለቀቀው ፎቶ ላይ የተሠጠውን comment አሳየችኝ።ልጅቷ እኛ ት/ቤት ናት ስለኛ ግንኙነትም በደንብ ነው ምታውቀው የሠጠችው comment የኔ ብቻ ነበር ሚለው የድንጋጤና የፌዝ ሣቅ እየሣኩኝ ወዲያው እሡ መልሶ የሠጣትን ለማየት ከፈትኩት።የሡ ብሶ ቁጭ ፍቅሬ እናቴ ህይወቴ ነበር ሚለው ስልኩን ለቅቄው እየተንቀጠቀጥኩ<አይ አይ ውሸት ነው እሡ አይደለም> እያልኩ ጮክ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ።በዚ ጊዜ አጠገቤ ተቀምጣ ዞራ ስታወራ የነበረችው የልብ ጓደኛዬ የነገረችኝ ልጅ ላይ እንዴት ከፈተና በፊት ትነግሪያታለሽ እያለች ጮኸችባት።ስለዚህ እውነት እያልኩ ለራሴ የተቀመጥኩበት ወንበር ላይ ተቀምጬ መንሠቅሠቅ ጀመርኩ።<በቃ ርብቂ ማወቅሽ ካልቀረ ሁሉንም እነግርሻለው>አለችኝ ጓደኛዬ እኔም እጇን ጥብቅ አድርጌ ይዣት እያለቀስኩ<ውሸት እንደሆነ ብቻ ንገሪኝ>አልኳት በሚለማመጥ ድምፅ በሠአቱ የነበረን free period አልቆ አስተማሪ እየገባ ስለነበር አሟት ነው ብላ ከክፍል ይዛኝ ወጣች።ግቢ ውስጥ ምሳ ለመብላት ምንጠቀምበት ቦታ ሄድንና ተቀመጥን።ምትነግረኝ ነገር ሮቢን እንደሚያሣጣኝ ስለማውቅ ንገሪኝ ብዬ መጠየቅ ፈራው።ለብዙ ደቂቃዎች ከኔ ለቅሶ ውጪ ሌላ ድምፅ ሳይሰማ ከቆየ በኀላ በረጅሙ ተንፍሣ መናገር ጀመረች።<ርብቂዬ ብዙ ጊዜ ሆኖታል፤ቢያንስ ወር ከምናምን ግን አንቺ ሮቢን ከምታፈቅሪው ይልቅ ሁሌ ምትነግሪን እንደምታምኚው ነው ስለዚህ ሁላችንም ልንነገርሽ አልደፈርንም>በመሀል አቋርጫት አሁንም ቢሆን አምነዋለው ምትሉትን አላምንም አልኳት።ባታምኚኝም ልነግርሽ ይገባል ብላ ንግግሯን ቀጠለች።<የጓደኛዬ ብዬ የነገርኩሽ ታሪክ ሁሉ ያንቺ ነበር> አለችኝ።

ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
148 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:59:05 #ተወዳጁ


|ክፍል 13|


ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።የቀረው ቦታ ላይ የፍቅር ጥቅሶች በመፃፍ፣የተለያዩ ስዕሎችን በመሣል እና ለየት ያሉ ፅሁፎችን በመፃፍ ደብተሩን በደምብ ካስዋብኩት በኀላ ከጀርባው የቀረው ቦታ ላይ ከተዋወቅን ጀምሮ ያሣለፍነውን የማይረሣ ጊዜ ፅፌ ካሠብኩት ቀን ቀድሜ ጨረስኩ።ምንም እንኳን ከነ ሮቢ ቤት ብንወጣም አንድ ቀን እንኳን ርቀታችን እንዲሠማኝ አያረግም ነበር፤በቻለው ሁሉ ባገኘው አጋጣሚ ያገኘኛል።በስልክ ምናወራበት ሠአትም በጣም ብዙ ስለሆነ ሁለታችንም አብረነሸ ያለን ያህል ነበር ሚሠማን ግን ከኔና ከሡ ችግር ፍቅር የያዘው ይመስል ሁሌ አብሮን ነው።ጥቅምት ወር መጨረሻ አከባቢ እኔ ስልኬን ት/ቤት ተሠረኩኝ፤ያው ስልኬ ለኔ ስልክ ብቻ አልነበረችም ሮቢ አጠገቤ እንዳለ እንዳስብ ምታረግ ትልቅ ሀይልም ነበራት።ነገር ግን እናቴ ሁሉንም ነገር ስለምታውቅ በሷ ስልክ መደዋወል ጀመርን፤መቼም ከምንም ይሻላል።ህዳር 4 የሮቢ ልደት ነበር፤ምንም እንኳን ስልክ ባይኖረኝም ከሁሉም ሠው ቀድሜ ሮቢዬን መልካም ልደት የምልበት እድል አላጣሁም ነበር።የልደቱ ቀን እኔ ከቤት መውጣት ስላልቻልኩ እሡ እቤት መጥቶ ተገናኝተን በዛውም ያዘጋጀሁለትን ስጦታ ሠጥቼው ብቻውን እንዲያየው ነገርኩት።ሮቢ ስጦታውን እንዳየው ደውሎልኝ ብዙ አወራን፤በጣም ደስ ብሎት ነበር እኔም የሡ ደስታ ተጋብቶብኝ ደስተኞች ሆንን።ሰከንድ ሰከንድን፤ደቂቃ ደቂቃን፤ሠአት ሠአትን፤ቀናት ቀናትን እየተኩ ህዳር 15 ቀን ፍቅር ከጀመርን 9ወር ከ10 ቀን በኀላ ቀለበት አደረገልኝ።በጣም የተለየ ስሜት ነበር የተሠማኝ እንዴት ብዬ ላስረዳቹ በቃ ያላያችሁ ስታዩት ያያችሁ ደሞ የተሠማችሁን አስታውሣቹ ትንሽ ከገባቹም ተረዱኝ።ቀኑን ሙሉ ማታም ቁጭ ብዬ ቀለበቴን ሣየው አደርኩኝ።ሮቢ promise ካረገልኝ በኀላ ፀባዩ ቀስ በቀስ መለወጥ ጀመረ።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
123 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ