Get Mystery Box with random crypto!

ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤ Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤
የሰርጥ አድራሻ: @wubyefkr_kalat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.49K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-11-29 19:40:00 #ተወዳጁ


|ክፍል 12|


የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው፤የኔና የሮቢ እናት ተጣሉ።ሮቢ ነገሩ ስላስጨነቀው ሁሉቱን ለማስታረቅ የአስትን እናት ሊያመጣት ወደ አሠላ ሄደ።ሮቢ ስልኩ ተበላሽቶበት ስለነበር እሡ በሌላ ሠዉ ስልክ ሲደዉልልኝ ብቻ ነበር ማገኘው፤እናቴም ቤቱን ለመልቀቅ አስባ ለጊዜው እዛው ሠፈር አገኘች።ለሮቢ እንኳን ነግሬው እንዲያስቆማት ማድረግ አልቻልኩም ነበር ምክንያቱም ሮቢ አልደወለልኝም፤ሮቢ አርፍዶ ነበር ቤቱን ለቀን አዲሡ ቤት እቃውን አስገብተን ስንጨርስ ደወለልኝ።ሮቢ በጣም ባይናፍቀኝ ኖሮ ቀዛ ሠአት ባላወራው ደስ ይለኝ ነበር፤አነሳሁና አዋራሁት በጣም ቅዝቅዝ ብዬበት ስለነበር ምን እንደሆንኩ ሲጠይቀኝ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ሮቢ ምንም አላለኝም ሣወራም አይመልስልኝም በጣም ጨነቀኝ ስሙን ደጋግሜ ብጠራውም መልስ የለም ከብዙ ዝምታዎች በኀላ ያለ ምንም መልስ ስልኩ ተዘጋ።ሮቢ በጣም ሲከፋው ምንም አይናገርም ዝምታን ነው ሚመርጠው፤ምንም አያጠያይቅም አሁን ሮቢ በጣም ከፍቶታል።እኔም ሀዘኔን ዋጥ አድርጌ እሡን እንዳላፅናናው እንኳን እንደ ሌላው ጊዜ አብረን አይደለንም ሌላው ቢቀር እንኳን ስልኩ አይሠራም።ሮቢ በነጋታው ከተረጋጋ በኀላ ደወለልኝ እዛ ምንም እንደማይሠራ እና ቶሎ እንደሚመጣ እቤትም መጥቶ እንደምንገናኝ ነገረኝ።ሮቢ በነገረኝ ቀን እቤት መጣ።ሮቢዬን ከ3 ቀን ናፍቆት በኀላ አገኘሁት፤ሁሉንም ሠላም ብሏቸው እኔ ጋ ሲደርስ ተያየን እና ተቃቀፍን።እስኪሄድ ድረስ አቅፎኝ ቁጭ አልን፤ማም እያየችን ትገረማለች ምንም ብንፈተን ፍቅራችን ይበረታል እንጂ ቀዝቅዞ አያውቅም ነበር።ከሮቢ ጋ በዚህ መንገድ እሡ እቤት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከነ ሮቢ ቤት ነሀሴ 21/2010አ.ም ነበር የወጣነው፤ማም የተሻለ ቤት ስታገኝ ነሀሴ 28/2010አ.ም ጭራሽ ሠፈሩን ለቀን ወደ ሌላ ሠፈር ገባን።የገባን ቀን ለሮቢ በምልክት እየነገርኩት መጣ።ሮቢ አዲስ የተከራየንበት ቤት ሁሌ ይመጣል፤ቢያንስ አሁንም ሮቢዬን አገኘዋለው ለኔ ይሄ በቂ ነበር።እንግዲህ በዚህ ሁኔታ 2011 መጣው መጣው ተቀበሉኝ ማለት ጀመረ።መስከረም 1/2011አ.ም ሮቢዬ ወደ ከሠአት እቤት መጥቶ አብረን በአሉን ደስ ብሎን አሣለፍን።ለ10ኛ ክፍል ሁለታችንም መዘጋጀት ጀመርን፤ት/ትም ተጀምሮ እንደ በፊታችን ት/ቤት መገናኘት ጀመርን ቅዳሜ ቅዳሜ ደግሞ ሮቢ እቤት እየመጣ አብረን እንውል ነበር።የሮቢ ልደት ህዳር ወር ላይ ስለነበር እኔ ልሠጠው ያሠብኩት ስጦታ ደሞ ጊዜ ስለሚፈልግ ስልኬ ያሉትን ፎቶዋችንን ቶሎ በማሳጠብ ጀመርኩኝ።ሁሉንም ፎቶዎች በቅርፅ ከቆራረጥኳቸው በኀላ ያዘጋጀሁት ማስታወሻ ደብተር ላይ ለጠፍኳቸው።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
416 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 19:40:00 #ተወዳጁ


|ክፍል 11|


ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት፤ መጥቶ አቀፈኝ።ይኸዉልሽ ርብቂ ሚም ፈቅዳለች አለኝ እየሣቀ እስካሁን እንዳዘነ ያስመሠለው surprise ሊያረገኝ ፈልጎ እንደሆነ ነገረኝ።ደስታዬ አሳብዶኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩበት።ሁሉንም ነገር ያወሩትን አንድ በአንድ ነገረኝ፤ማምን ጠርቷት ውጪ እንደወጡ እሡ ምንም ሣያወራ<ሮቢ ይኸውልህ ለምን እንደፈለከኝ አውቃለው ያንተና የርብቃ ፍቅር ብዙ ተፈትኗል ግን የእናንተ ፍቅር እንኳን ሊቀንስ ይበልጥ ጨመረ፤የሁለታችሁንም ፀባይ እያስተዋልኩ ነበር እናንተን መለየት ፈፅሞ ማይታሠብ ነው እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም መለየት አይችልም>ብላው ፍቅራችንን እነሸደመረቀችልን እና እሡንም ብዙ እንደመከረችው ነገረኝ።
የዛሬው ደስታዬ ልክ አጣ፤ወደ ማታ አከባቢ የተጠራው ሠው ሁሉ ተሸኝቶ እኛ ተሠብስበን መጨዋወት ጀመርን።ሌሎቹ ምርቃቱን ሲያከብሩ እኔና ሮቢ ደግሞ የፍቅራችንን የነፃነት ቀን እያከበርን በጣም ተደስተን አሣለፍን።ከዛ በኀላ ያሉት ቀናቶች ሁሉ በጣም ደስተኛ እየሆንን የፍልሠታ ፆም ደረሠ።ፍልሠታን አብረን ማስቀደስ ጀመርን፤የ6 ወራችን ማግስት ጊዜ አልሄድንም ነበር ሳናስበው በጣም ለየት ባለ መንገድ አከበርነው፤ቤቱን ቀለም እየቀባን ደስ የሚል ቀን ነበር አንዴ ፊታችንን አንዴ ፀጉራችንን እየተቀባን ቤቱን ቀብተን ጨረስን።ነሀሴ 14/2010አ.ም እኔና ሮቢ መንገድ ላይ ቆመን እያወራን ሶስት ወንዶች ከፊታችን መጡ፤ልክ አጠገባችን ሲደርሱ ቆሙና አንዱ ልጅ እኔን ጎተተኝ ሮቢ እኔን ሊያስለቅቀኝ ሲሌ የቀሩት ሁለት ልጆች ከሗላ ይዘውት ቸመዞሪያ እንኳን ጊዜ ሣይሠጡት በጩቤ ወጉት፤ሮቢ አይኔ እያየ ከፊቴ ሲወድቅ ነበር ከዚ እውነት ከሚመስል አስፈሪና አስቀያሚ ቅዠት የነቃሁት፤ልክ እንደተነሳው የእውነት የሆነ ይመስል የሆነውን እያስታወስኩ አለቀስኩ።ከእናቴ ጋ ስለነበር የተኛሁት ሳለቅስ ተነስታ ምን እንደሆንኩ ስትጠይቀኝ ነገርኳት፤እሧም ሁኔታዬ አስገርሟት እየሣቀች ጠግቦ በልቶ ስለተኛ ነው አለችኝ፤እኔም የሠጠችኝ ምክንያት ፈገግ ቢያስብለኝም ሮቢን እስካገኘው እና ምንም እንዳልሆነ እስካረጋግጥ አላመንኩም።አይነጋ የለ ያ የጭንቅ ለሊት ነግቶ ሮቢን አገኘሁት፤ያየሁትን ህልም ስነግረው ሆዱን እስኪያመው በኔ እንደዛ መሆን እየሣቀ እሡም እናተሰ እንዳለችኝ ጠግቦ በልቶ ስለተኛ እንደሆነ ነገረኝ።እኔም እያሾፍኩ ሁለተኛ ጠግበህ እንዳትበላ አልኩት፤ሁለታችንም ተሣሣቅን።
ቀናቶችም እየበረሩ መቼም ህይወት ብዙ ስሜቶች ሚፈራረቁባት ናት፤ደስታ ሲኖር ሀዘን ይኖራል።የኔና የሮቢ ፍቅር በድጋሚ ሊፈተን ነው።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
134 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 19:40:00 #ተወዳጁ


|ክፍል 10|


የምርቃቱን ዋዜማ ደስ ብሎን አሣልፈን ማታ ላይም ስራ ሲሰራ ስለነበር አብረን ብዙ አመሸን።ነገ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቀው ስለምንሄድ ተኛን።ቀኑ በጣም ደስ ይል ነበር አይነጋ የለ ነግቶ እኔና ሮቢ የማም ባልን ልናስመርቅ ሄድን።የማም ባል ወንድሙና እናቱም አብረውን ነበሩ።አብረን ብዙ ፎቶ ተነስተን እቤት ወደተዘጋጀው ዝግጅት ስንሄድ ድምቅ ብሏል ሁሉም ነገር ቦታ ቦታውን ይዞ ደስ ይላል።የተጠሩ ሠዎች መምጣት ሲጀምሩና ሁሉም busy ሲሆኑ ሮቢ ጠርቶኝ እነሡ ቤት ሄድኩ።እንዲህ ብቻችንን ከተገናኘን ስንት ጊዜ ሆኖን ነበር ሄጄ ጥምጥም ብዬ አቀፍኩት እሡም አቀፈኝና ይሄን ያሣለፍነው ጊዜ እንደማይደገምና በራሡ መንገድ እንደሚያስተካክለው ቃል ገባልኝ።በምን አድርጎ እንደሚያስተካክለው ግራ ቢገባኝም ሁሌም ሮቢ ላይ ትልቅ እምነት አለኝ።በተለይ የአባቴ ምትክ ነሽ ካለኝ በኀላ በምንም means እንደማይተወኝ እርግጠኛ ነበርኩ።እኔም አባቴን ካሉኝ ነገሮች ሁሉ አብልጬ ነው ምወደው ከአባቴ በኀላ በዚ መጠን የወደድኩት የመጀመሪያው ወንድ ሮቢ ነው።ማም ከፈለገችኝ እንዳታጣኝ ብዬ ቶሎ ወጣው፤እኔ እንደወጣው ሮቢም ትንሽ ቆይቶ መጣና ማም ጋ ሄዶ በጆሮዋ የሆነ ነገር ሲላት እሧም አንገቷን ወደ ላይና ወደ ታች ነቀኘቀችለት።
ከዛ ተከታትለው ከግቢ ውጪ ወጡ፤የዛን ጊዜ የተሠማኝ ፍርሀት እና ድንጋጤ መቼም አጋጥሞኝ አያውቅም ነበር።ቆይተው የገቡት ቢያንስ ከ10 ደቂቃ በኀላ ቢሆንም ለኔ ግን ከሮቢ ጋ በነፃነት ሣንገናኝ ያሣለፍነዉን 10 ቀን ያህል ነበር የረዘመብኝ፤ሮቢ ከማም ጋ አውርቶ ሲጨርስ በምልክት ወደ ቤት ጠራኝ።ሲጀምር ባይጠራኝም እኔም ልሄድ ነበር ወዲያው ሄድኩ፤ልክ ሣየው የከፋው ይመስላል ቃል ማውጣት አልቻልኩም በቃ መጥፎ ዜና ምሰማበት አቅም አልነበረኝም።ዝም ብዬ አየሁት እስካሁን እንዳቀረቀረ ነው ሁለታችንም ዝም ዝም ብቻ እንደምንም አፌን አላቅቄ ሮቢ አልኩት መጥቶ አቀፈኝ።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
131 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 19:40:00 #ተወዳጁ

|ክፍል 9|



አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።ሀምሌ 5/2010አ.ም ከሮቢዬ ጋ 5 ወር ሞላን፤የአመቱ አቡኤ ስለነበር እኔ ሮቢ አስት እና ፍቅር ልናነግስ ቤተ ክርስቲያን ሄድን።ሮቢን የመጀመሪያ ልጃችን ስም ማን ቢሆን ደስ ይልሀል ስለው በጣም ነው የገረመኝ እኔም ያሠብኩትን ስም ነበር የነገረኝ "ቅዱስ" የሁለታችንም ምርጫ ነበር ደስ ሲል!ቀኑ የሠኔ ፆም መፍቻ ስለነበር ወደ ቤት ሄደን አስት ወጥ መሠራራት ጀመረች።እነ ማም ከስራ ሲመጡ ሁላችንም አንድ ላይ በላን።ሀምሌ 11/2010አ.ም(ርብቃ ምክንያቱን መጥቀስ አልፈለገችም) በድጋሚ እናቴ ከሮቢ ጋ እንድንለያይ ጥብቅ የሆነ ትዕዛዝ ሠጠችኝ።እናቴ ውሳኔዋ የሚሻር አይመስልም ነበር።የሚያፈቅሩትን ሠው ለማጣት ማሠብ በጣም ከባድ ነው።ለመጀመሪያ ጊዜ የእናቴን ትዕዛዝ ተላለፍኩ፤ከሡ መለየት እንደማልችል ቃል በቃል ነገርኳት።እሧም በሠአቱ በጣም ተናዳ ስለነበር ያለችኝን ካላደረኩ ቤቱን እንደምትለቅ ነገረችኝ።ግን ማነው እስቲ እኔ በዛ ሠአት የተሠማኝ ስሜት የገባው ለማንም የማይገባ ስሜት ነበር።<መቼም ወጥተን አይኑን ከማላየው ያልሽኝን አደርጋለው ግን እሡን ከኔ ልታርቂው ምትችይው በአካል ነው ከልቤ ሊወጣ አይችልም>አልኳት።እናቴ ንዴቷ ጠፍቶ በንግግሬ እየተገረመች አንቺ እኮ ገና ልጅ ነሽ ብዙ ህይወት ይጠብቅሻል አለችኝ።የኔ ማዘን ቢያሣዝናትም በሠአቱ በሮቢ ተናዳበት ስለነበር ውሣኔዋን ሊያስቀይራት አልቻለም።ቀናቶች እየተቆጠሩ በመጡ ቁጥር እኔና ሮቢ በነፃነት የመገናኘት ፍላጎታችንና ሀዘናችን እየበረታ መጣ።እንደ በፊቱ አንድ ላይ መዋል የለ አብረን ምግብ መብላት የለ በቃ ለደቂቃ ያህል ግቢ ውስጥ እንገናኝና ሌላዉን በtg ነበር ምናወራው ለማያውቀው ቀላል ሊመስል ይችላል ግን እጅግ በጣም ከባድ ነበር ቢሆንም ከዛ ግቢ ወጥተን አይኑን ካለማየት እንዲህ ይሻል ነበር።እናቴ ከከለከለችኝ በኀላ ያመጣሁት የባህሪይ ለውጥ ቢያሣስባትም መሸነፍ ስለማትወድ በውሣኔዋ እንደፀናች ነው።እናቴ ግንኙነታችን እንዲቀጥል ባትፈቅድም ሮቢ ላይ ግን ምንም አልተለወጠችበትም ነበር።ሀምሌ 21/2010አ.ም የማም ባል ምርቃት ስለነበር ዛሬ ሽር ጉዱ ተጧጡፏል፤በዚ አጋጣሚ እኔና ሮቢም የቤቱን decor ስንሠራ ያለ ማንም ከልካይ አብረን ዋልን።ወደ ማታ ላይ ማም እና አስት ፕሮግራሙ እንዴት እንደሚያደርጉ እያሠቡ እኔና ሮቢን የተከራዩትን ድንኳን እንድናመጣ ሂዱ ተባልን፤አቤት ደስታ እንኳን ለቀናት የናፈቅነውን ነፃነት አግኝተን አይደለም ምክንያት እየፈለግን አብረን ስንሆን እንኳን ደስታ ልዩ ነው።ድንኳኑን ለማምጣት ስንሄድ ቦታውን ስለማናውቀው የማም ባል አብሮን ነበር የመጣው፤የምርቃቱን ዋዜማ እጅግ ደስ ብሎን አሣልፈን.............


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr\kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
270 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 19:40:00 #ተወዳጁ_

|ክፍል 8|


መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን ነበር።እናቴ ከሮቢ ጋ ያለኝን ግንኙነት እንዳቆም አንዴ እየተቆጣች አንዴ ደሞ እያለቀሠች ነገረችኝ።መጀመሪያ ላይ የቀልዷን ቢመስለኝም እያለቀሠች ስትለምነኝ እና ስትቆጣኝ ነው የእውነቷን መሆኑ የገባኝ።ከሡ ተለይቼ እንደማልኖር እምባዬን እንደ ዝናብ እያወረድኩ ብነግራትም ልመናዋን ወደ ትዕዛዝ ለወጠችው።ከሡ ጋ እንድለያይ የፈለገችው ብዙ ጊዜ ከሠዎች ጋ ስለሚደባደብና ስለሚጣላ እሡን እንጎዳለን ብለው እኔን የሆነ ነገር እንዳያረጉኝ በመፍራት ቢሆንም ከሡ ተለያዪ ከምባል ሞት ሺ ጊዜ ይሻለኝ ነበር።ስለዚህ ግንኙነታችንን በድብቅ ለማድረግ አሠብኩ።በጣም ከባድ ነበር ለሮቢ 3ቀን ብደብቀውም ጭንቀቴ በግልፅ ያስታውቅ ስለነበረ በጣም እንድነግረው ሲያስጨንቀኝ ነገርኩት።በኔ ጥፋት ምክንያት እንዲህ ስላሰቃየሁሽ ይቅርታ ርብቂ ሁሉንም አስተካክለዋለው ብሎኝ ደግመኛ እንደማይጣላ ቃል ገብቶልኝ ሚምንም ይቅርታ እንደሚጠይቃት ነገረኝ።የስንት ቀን ጭንቀቴን እሡ በአንድ አ.ነገር አጠፋልኝ በጣም ደስ አለኝ።የአክስቴ ልጅም ጭንቀቴ በጣም ስላስጨነቃት እናቴን ደዉላ አናገረቻት።እናቴ ባይዋጥላትም ደስተኛ እንድሆን ፈቀደች።በጣም ነበር ደስተኛ የሆንኩት ያፈቀሩትን ሠው በነፃነት ማግኘትን የመሠለ ምን አለ።መጋቢት 30/2010አ.ም እሁድ ቀን የፋሲካ በአል ነበር።ሮቢዬ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር መጥቶ ተገናኘን።በጣም ናፍቆኝ ነበር ትንሽ ብቻ አብረን ከቆየን በኀላ የገዛሁለትን ሠአት እንደተጠቀለለ ሠጥቼው ቶሎ ወደ ቤት መሄድ ስለነበረበት ሄደ።እኔና ሮቢ በፍቅራችን እንኳን ሌሎች እኛ ራሡ እንቀና ነበር ከሮቢዬ ጋ 3ወር ሞልቶናል ኧረ እንደውም ለልደቴ የሆነ መናፈሻ ሄደን የአንገት ሀብል አደረገልኝ።ከዛ ወደ እናቴ ቤት ስለነበር ምሄደው አብረን ወደ ቤት እየተመለስን cupcake ገዝተን እየበላንና ክሬሙን እየቀባኝ ነበር የሄድነው።እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።

እቤት ልንደርስ ስንል አብረን እንደነበርን እንዳያውቁ እኔ መጀመሪያ ገባሁና እሡ ትንሽ ቆይቶ መጣ።ልደቴን ደስ ብሎኝ አሣለፍኩ።ሮቢ ለእናቱ የፍቅር ግንኙነት እንደጀመርን እንደነገራት ነግሮኝ ነበር ቢሆንም አስት አሁንም እንደ በፊቷ ነች ምንምአልተለወጠችም ። ግንቦት 12/2010አ.ም ሁላችንም ተሠብስበን ቤተ ክርስቲያን ሄድን ንግስ ነበር።ከዛ ሮቢ እዛው ቁጭ ብለን<አንቺ የአባቴ ምትክ ነሽ አባቴን ባጣሁት በአመቱ አንቺን ሠጠኝ>አለኝ።ሮቢ ለአባቱ ያለውን ፍቅር ጠንቅቄ ስለማውቅ ደስታዬ ወደር አጣ።ወደፊት ተጋብተን ለሚኖረን ህይወት ማረጋገጫ ፊርማ የሠጠኝ ስለመሠለኝ ምን አይነት ህይወት እንደሚኖረን እያሠብኩ በደስታ ክንፍ አውጥቼ ልበር ምንም አልቀረኝም ነበር።ሮቢ የአባቱን ያህል እንደሚወደኝ ሣስብ መቼም እንደማይተወኝ ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እርግጠኛ ሆንኩኝ።ቀናት ቀናቶችን እየተኩ final exam ከወሠድን በኀላ ከአክስቴ ልጅ ጋ ትንሽ ተጋጭተን እናቴ ጋ መኖር ጀመርኩ።(ርብቃ ምክንያቱን በሙሉ ልትነግረኝ ባትፈልግም በሮቢ ምክንያት እንደሆነ አጫውታኛለች)አሁን ክረምት ነው ስለዚህ ት/ት የለም በዛ ላይ ከሮቢ ጋ አንድ ግቢ ነው ምንኖረው።ጠዋት ነግቶ የመኝታ ሠአት እስኪደርስ እኔና እሡ አንድ ላይ ነን።ቀናቹብኝ አይደል ከሚያፈቅሩት ሠው ጋ አንድ ላይ እየኖሩ አብሮ መዋል አቤት ለዚህ ደስታ ሚሆን ቃል የለኝም።ጠዋት ከነጋ እኔ የለሁት አሸነ ሮቢ ቤት ነኝ፤ይሄ ልምድ እንኳን እኔና ሮቢ አስቱም ለምዳዋለች።አንዳንዴ ባልሄድ እንኳን አስት ፍቅርን እየላከቻት ትጠራኝ ነበር።
ሀምሌ 5/2010 አ.ም የእኔና የሮቢ ልዩ ቀን ነበር ....


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
143 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 19:40:00 #ተወዳጁ

| ክፍል 7 |


ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።<ሁላችሁም እንዳከበራችሁን እግዚአብሔር ያክብራችሁ፤ይሄንን ዝግጅት እንዲህ የተሟላ እንዲሆን በሀሣብም ሆነ በስራ ስለረዳችሁን በጣም አመሠግናለሁ በተለይ ሚም ለሊቱን ሙሉ ሳትተኚ ሁሉንም ስራ ሸፍነሽ ስትሠሪ ነበር በእኔና በእናቴ ስም ምስጋናዬን አቀርባለው። አባቴም ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑርልኝ።>ብሎ ተቀመጠ።ማስተዋል በተሞላበት ንግግሩ ኮራሁበት።እናቴ ቡና አፍዪ ብላኝ ቡና እያፈላው ብዙ ስነወራ ካመሸን በኀላ ሁሉም ወደ ቤት መሄድና የቀሩት መተኛት ሲጀምሩ እኔና ሮቢ ቁጭ ብለን እያወራን እጄን የሡ እጅ ላይአድርጎ ጣቴን መለካት ጀመረ፤ሮቢ ምን እየሠራህ ነው ስለው ደሞ ሠፊ ቀለበት ገዝቼልሽ የሠው መሣቂያ እንዳልሆን ነዋ አለኝ።ሁለታችንም እየተሣሣቅን እናቴ ድንገት መጥታ እናንተ ከተገናኛቹ በቃ ወሬ አያልቅባችሁም አይደል ነገ እኮ ት/ት አለ ነይ በይ ተኚ አለችኝ እየሣቀች አንተም ደክሞሀል ሮቢ ከትላንት ጀምሮ አልተኛህም በል ተኛ አለችው።አቅፌው ቻው አልኩትና ወደ ቤት ሄድኩኝ።መጋቢት ሰባት ማታ ላይ የኔ ቤተሠቦች አስት የሮቢ ጓደኞች ሌሎች ተከራዮችና እኔና ሮቢ ግቢ ውስጥ ቁጭ ብለን እራት እየበላን እየተጨዋወትን ነበር።ሁሉም እራት በልቶ ጨርሶ የየራሡን ወሬ ማውራት ሲጀምር እኔና ሮቢም ከጓደኞቹ ጋ ማውራት ጀመርን።ሁሉም ቀስ በቀስ ወደ ቤት ሲገባ የሮቢ ሁለቱ ጓደኞቹ ደሞ በ pc film ማየት ጀመሩ እኔና ሮቢ ፊልሙ ስላልተመቸን የራሣችንን ወሬ ማውራት ጀመርን።ከሮቢ ጋ ቁጭ ብለን የባጥ የቆጡን ስነሠወራ ለካ ሠአቱ ሄዶ ነበር፤ከሡ ጋ ስሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ ልክ እንደ ሁል ጊዜው እጄን ይዞኝ እያወራን ጓደኞቹ ተነስተው በቃ እንሂድ ሲሉ አስትም ወጣችና አው መሸባቹ ሂዱ እናንተም ግቡና ተኙ መቼም እናንተን መለያየት ችግር ነው አለችን።ቅር እያለንም ቢሆን ተነስተን ገባን።ፍቅር ለኔም ሆነ ለሮቢ የመጀመሪያችን ነው። ለኔ በጣም ለብዙ ነገር መጀመሪያዬ ሮቢ ነው።ብዙ ነገሮችን በሡ አይቻለው፤ተምሬያለው።ደስ የሚል እና ሁሌም ቢያስቡት የሚያስቀና የማይሠለች የፍቅር ጊዜ አብረን አሣልፈናል።ቅዳሜ ቀን እኔ ግቢ ውስጥ ለማፍላት እቃ አቀራርቤ ቡናውን እየቆላው አጠገቤ መጥቶ ቁጭ አለና earphone አድርጎልኝ ላንቺ ነው ውዴ ስሚው አለኝ።የናቲ ማን የመጀመሪያዬ ሚለው ዘፈን ነበር።ዘፈኑ ገና መውጣቱ ነው ተነሣሁና ጉንጩን ስሜው ቁጭ አልኩኝ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር።እንዴ ቆይ ሌላም አለ ድጋሜ ትስሚኛለሽ ብሎኝ አሁንም የናቲ ማን track 01 <ተነፋፍቆ ለተገናኘ ሠው
ለጨዋታ ቀን ሌቱም አይበቃው>ሚለውን ዘፈን ከፈተልኝ።ሀሣባችንን በደንብ ሚገልፅ ግጥም ስለነበረው በጣም ነው የወደድኩት ቅዳሜን በጣም ደስ ብሎን አሣለፍን።ማታ ላይ እናቴ የኔና የሮቢ ቅርበት በጣም በዝቶባት ስላጠራጠራት ያለንን ግንኙነት እንድነግራት ጠየቀችኝ።እኔም ምንም ሣልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት፤ሁሉንም ስለነገርኳት ደስ ብሏት ሮቢንም ስለምታውቀው ምንም አላለችኝም።ሁሉም ነገር ሲመቻች እንዴት ደስ ይላል ከሮቢ ጋ ያለን ፍቅር በጣም እየጨመረ መጣ በቃ ሁሉም እስኪቀናብን ነበር ምንፋቀረው፨ሮቢ ከጋበዘኝ ዘፈኖች ውስጥ የናቲ ማን(የመጀመሪያዬ እና ተነፋፍቆ)፤የያሬድ(ዘለላዬ)፤የታሜ(ሀኪሜ ነሽ)፤የሳንቾ(አታሣዩኝ) ሁሌ ስሰማቸው እስካሁን እሡን ነው የሚያስታውሱኝ ግን ከምንም በላይ የብስራት ሱራፌል(ቃል በቃል)ብሎ ያዜመውን ሙዚቃ ስሰማው ሮቢ አብሮኝ ያለ አጠገቤ የተቀመጠ ነው ሚመስለኝ ሁሌ ከሮቢ ጋ አብረን ስንሆን ስለምንሠማው ነበር።አንድ ቀን እንኳን ሣንኮራረፍ ሁለተኛ ወራችን እየቀረበ መጣ።መጋቢት 21/2010አ.ም ነበር ሠማይ የተደፋብኝ እስኪመስለኝ የጨለመብኝ በጣም ከባድ ቀን........


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
260 views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 20:30:02 #ተወዳጁ

| ክፍል 6 |


በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።ት/ት ሲከፈት እሡም እኛ ት/ቤት ለወደ ቤት ሠአት እየመጣ መገናኘት ጀመርን።ከሠኞ እስከ ሀሙስ እሡ ት/ቤት እየመጣ እንገናኛለን አርብ ደሞ እኔ እናቴ ጋ ከት/ቤት ስወጣ ስለምሄድ ቅዳሜ እና እሁድ አብረን እየዋልን ሠኞ ደሞ አብረን ወደ ት/ቤት እንሄዳለን።የፍቅር ምሣሌዎች እስክንባል ፍቅራችን ገዘፈ።አንዳንዴ ወደ ውጪ ወጣ ስንል ከአባቴ ጋ ምኖርበት ሠፈር እየመጣም እንገናኝ ነበር።ፍቅራችን እንኳን ለሚያቀን መንገድ ላይ ላየን እንኳን የሚያስቀና ነበር።እንዲህ እየተባለ አንድ ወራችን ደረሠ ግን አልተገናኘንም ነበር ምክንያቱም በማግስቱ በጣም የሚወደው አባቱ ሙት አመት ነበር።ስለዚህ ት/ቤት አልሄደም።እኔም ቀኑ ረቡዕ ስለነበር እናቴ ጋ አልሄድኩም አርብ ቀንን ምመርጠው ሁለቷን የእረፍት ቀኔን እሧ ጋ ለማሣለፍ እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለም።ረቡዕ ወደ ቤት ስገባ አስት ደወለችልኝና ነገ እንዳትቀሪ ብላ በአደራ እና በማስጠንቀቂያ ነገረችኝ።እኔም እንቢ ማለት ስለከበደኝና ለሮቢ እንደማስፈልገው ስለማውቅ እሺ አልኳት።የሧን ስልክ እንደዘጋሁት ወዲያው እናቴ ደወለችና እሧም እንዳትቀሪ ነይ አለችኝ።ለአባቴ ሀሙስ እንደምሄድና ሠኞ እንደምመጣ ነገርኩት።መጋቢት 6/2010አ.ም ሀሙስ ቀን ከት/ቤት ስወጣ እነ ሮቢ ቤት መሄድ ጀመርኩኝ።ድንገት ሄጄ ደስ ላሠኘው ፈልጌ ለሮቢ እንደምመጣ አልነገርኩትም ነበር።ልክ የውጪው በር ጋ ስደርስ ሮቢ እየወጣ ነበር ልክ ሲያየኝ በጣም ደስ አለው።አልመጣም ብዬው ስለነበር ሲያየኝ አላመነም መጥቶ አቀፈኝና ሠላም አለኝ።አብረን ወደ ውስጥ ገባን ግቢ ውስጥ ብዙ ሠው ነበር ሠላም አልኳቸውና አስት እና እናቴን ስሜያቸው ወደ ውስጥ ገባው።ልብሴን ቀያይሬ የሠው ብዛት እስኪቀንስ ትንሽ ጋደም አልኩኝ።ማታ ላይ አስት ጠራችኝና እነሡ ቤት ሄድኩኝ።እናቴ ነበረች ሌሎች ማላውቃቸው ሠዎች ነበሩ።ሮቢ ከሁሉም ጋ አስተዋወቀኝ ዘመዶቹ ነበሩ።ከዛ እራት እየበላን ድንገት ሮቢ ተነስቶ መናገር ጀመረ።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
120 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 22:38:16 #ተወዳጁ


| ክፋል 5 |


እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛው ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።ደግሞ ሌላ text ላከልኝ<እሺ ቅድም ላስረዳህ ስትዪ አልነበር አሁን እሠማሻለዉ ስለ ልጁ በደንብ ንገሪኝ>አለኝ።balance እንደጨረስኩኝ አውቆ ነው እንዴ አልኩኝ ለራሴ ከ5 ደቂቃ በኀላ<አየሽ ልታስረጂኝ አትችይም ምንም ማለት አትችይም>አለኝ።ጠዋት ደርሶ ምን ብዬ እንደማስረዳው ሣስብ ለሊቱ ሲጋመስ ነበር እንቅልፍ የወሠደኝ።አይደርስ የለ ያቺ ጠዋት ደረሣ ተገናኘን።እንደ ሌላዉ ቀን እንኳን አቅፎ ሠላም ሊለኝ ይቅርና ለአይኑ ራሡ ያስጠላሁት መሠለኝ ዛሬም አብሬያቸዉ ሣልበላ ስትጨርስ ጥራኝ ብዬው ወጣው።ብዙም ሣይቆይ ፍቅር መጥታ ውጪ እየጠበቀሽ ነው አለችኝ።እኔም ወድያው ወጣውና መሄድ ጀመርን።ማታ እንቅልፍ አሣጥቶኝ ያደረውን ስብሰለሰልበት የነበረውን ልነግረው <ይኸውልህ ሮቢ ልጁ እኮ...>አላስጨረሠኝም።<እኔ እኮ አያገባኝም ለኔ መናገር አይጠበቅብሽም>ሲለኝ ሊፈስ የደረሠውን እንባዬን ዋጥ አድርጌው በዝምታ መጓዝ ጀመርን።ለሁለታችንም እኩል በሚሆነወሸ መንገድ ስንሄድ ይበልጥ ዝምታ ነፈሠ እያንዳንዷ ምንራመዳት እርምጃ የ10 ሠዎችን ያህል ጩኸት ገዘፈብኝ።ጩሂ ጩሂ ሁላ አለኝ።ምንም ትንፍሽ ሣንል መለያያችን ጋ ስንደርስ ተቃቀፍንና ሁለታችንም ጀርባችንን ተሠጣጥተን በየ መንገዳችን ሄድን።ክፍል ውስጥ ያለመደብኝን ጥግ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ።እረፍት ሠአት ላይ ጓደኞቼ በግድ ይዘውኝ ወጡ።ግን ድንገተኛ ረብሻ በአከባቢው ላይ ስለተነሣ ሁሉም ወላጅ እየመጣ ልጆቹን መውሠድ ጀመረ።ሁሉም ጓደኞቼ ከሄዱ በኀላ አባቴ በድንጋጤ እየበረረ መጣ።ልክ ሣየው ሄጄ ተጠመጠምኩበት።በጣም ፈርቼ ነበር።አባቴም አቅፎኝ ድንጋጤው ሲለቀው ወደ ቤታችን ሄድን።አይገርምም ሮቢ ነበር ለእናቴ ደውሎ ብጥብጥ እንደተነሣ ነግሯት ለአባቴ ደውላ የነገረችው።ሮቢ ለኔ እንደዚ ማሠቡ አስደስቶኝ ወደ ቤት እንደገባው በሠላም ገባህ የሚል text ላኩለት።እሡም ወድያው በሠላም እንደገባ ነግሮኝ የኔን ደህንነት ጠየቀኝ።እናም በዚ ተነስቶ እኔ በጣም እንደምወደው ነገርኩት እሡም ለኔ ተመሣሣይ ስሜት እንዳለው ነግሮኝ የፍቅራችንን የመጀመሪያ ቀን ሀ ብለን ጀመርን።በተነሣው ረብሻ ምክንያት ለ3ቀን ት/ት ተዘግቶ ነበር።በቃ ቀኑንም ለሊቱንም ነበር ምናወራው።

ገና ትምሀርት ከመከፈቱ .......

ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkrkalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
94 views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 20:35:39 _ #ተወዳጁ _


| ክፍል 4 |



የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ ስልኬን ወሠደብኝ።እኔም የሡን ስልክ ወስጄ ፎቶ እያየው ድንገት የኔ ስልክ ላየሸ text ገባ።ማነው ስለው በአንዴ ፊቱ ተቀያይሮ ስልኬን ወርውሮልኝ ወደ ውጪ ወጣ።እኔ በጣም ደንግጬ ስልኬን ሣየው እኛ ት/ቤት የሚማር የጓደኛዬ ፍቅረኛ ነበር text የላከልኝ<እምወድሽ>ነበር ሚለው።እሡ ሁሉንም ሠዉ እንዲ እያለ ነው ሚጠራው የሡ text ምንም አልገረመኝም።ይልቅስ የገረመኝና ጥያቄ የሆነብኝ የሮቢ እንዲህ መሆን ነው ለምን እንዲህ ተናደደ።እንደውም ስልኬን ወርውሮብኝ ጥሎኝ ስለወጣ ተናድጄ እኔም ወደ ቤቴ ሄድኩኝ።ማታ ላይ ፍቅር መጥታ አስት እየጠራችሽ ነው ብላኝ እነሡ ቤት ሄድኩኝ።ከዛ እቤት ስገባ ሮቢ ሶፋ ላይ ተኝቶ በearphone ሙዚቃ እያዳመጠ ስልኩን እየነካካ ነበር ድምፁን በጣም ከፍ ስላደረገው ሚሠማው ዘፈን ይሠማ ነበር<ያለ ተቀናቃኝ ያለ ፉክክር
ቦታ አለሽ በልቤ በፍቅሬ መንደር>
የሚለው ነበር።እቤት ገብቼ እሡ ከተኛበት ሶፋ አጠገብ ከተቀመጥኩ ብዙ ቆየው ግን እሡ እስካሁን አላዋራኝም ከአስት ጋ ብቻ ነበር ሣወራ የነበረው።አስት ተነስታ ወደ kitchen ስትገባ<ምን ሆነህ ነው ሮቢ>ብዬ text አረኩለት።አይቶት ዝም ሲለኝ በጣም ከፍቶኝ እንደ ሌላው ጊዜ አብሬያቸው እራት ሣልበላ ደና ደሩ ብዬ ወጣው።ልክ እቤት ስገባ text ገባልኝ፤ሮቢ ነበር<የውሸት ነበር ለካ>ይላል።<ምኑ>ብዬ ወዲያው መለስኩለት።<በቃ ተይው>አለኝ።እኔም ነገሩን ከሡ መስማት ፈልጌ እንጂ መጀመሪያም ገብቶኝ ስለነበር ልጁ ምኔም እንዳልሀቀነ እንዲያውም የጓደኛዬ ፍቅረኛ እንደሆነ ላስረዳው ሞከርኩኝ።እሡ ግን ወይ ፍንክች እኔ እኮ የምር ወድጄሽ ነበር አንቺም እንደዛ ይመስለኝ ነበር ሲለኝ አልተሣሣትክም እኮ ታድያ ብዬ ስልክለት balance ጨርሼ ነበር።


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkrkalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
154 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-18 19:03:25 #ተወዳጁ

|ክፍል 3|

..... እኔም ወደ ቤት ተመልሼ አያቴንና ትንሿን እህቴን ስሜያቸው ወጣው።ከሮቢ ጋ እየሄድን ሁሌም እንደምናወራ እና እንደምንደዋወል እየተነጋገርን ለኔ ት/ቤት በሚቀርበኝ መንገድ ከሸኘኝ በኀላ ተቃቅፈን ቻው ተባባልን።ለኔ ት/ቤት በሚቀርበው መንገድ ስለሄድን ቶሎ ነበር የደረስኩት።ቀኑን ሙሉ እሡን እያሠብኩ ምሣ ሠአት ደርሶ ከጓደኞቼ ጋ ከበላን በኀላ ከጓደኛዬ ጋ ላይብረሪ ገባን ግን ምንም ማጥናት አልቻልኩም።እሧም ጨንቋት ምን እንደሆንኩኝ ስትጠይቀኝ እኔም ፈገግታ ሣይለየኝ ሁለት ቀኑን እንዴት እንዳሣለፍኩኝ ነገርኳት።በጣም በግርምት እያየችኝ<አንቺ ለወንድ ከመች ጀምሮ ነው እንዲ ምትሆኚው ገና በትውውቅ ት/ትሽን እየነካብሽ ነው ስለዚህ ተጠንቀቂ ርብቂ>አለችኝ ፍርሀት በሞላው ድምፅ!ላይብረሪ ገብተን ምንም ሣናጠና ተደውሎ ወጣን።ቀሪውን ሁለት ክፍለ ጊዜ ምንም ሣልሠማ የወደ ቤት ሠአት ደውል ተደወለ።ቶሎ ከአባቴ ጋ ምኖርበት ቤት ሄጄ ቦርሣዬን ብቻ አውልቄ fb ላይ ተጣድኩኝ የአባቴ እናት መጥታ መክሰስ ብዪ እንጂ ብላ እስክትቆጣኝ ስልኬ ላይ ተደፍቼ ነበር።ከዛ ዩኒፎርሜን አወላልቄ እና ተጣጥቤ መክሰስ ከበላው በኀላ ለቀጣዩ ቀን የሚሆነኝን ፕሮግራም ካዘጋጀው በኀላ ትንሽ አጥንቼ መልሼ የፈረደበት ስልኬ ላይ ተደፋው።ከሮቢ ጋ ካወራን በኀላ አባቴ ሲመጣ ሁላችንም እራት በልተን ተኛን።ከሮቢ ጋ በዚ መልኩ በጣም እየተግባባን መጣን።ቀናቶች በቀናቶች እየተተኩ የገና በአል ደረሠ።ሮቢ ትንሽ አሞት ስላልጠየኩት ቅጣት ነበረብኝ።እና የገና ስጦታ ሠጠሁት እሡም ሠጠኝ።ይሄ እንግዲ ፍቅር ከመጀመራችን በፊት የተሠጣጠነው የመጀመሪያ ስጦታ ነው።
የካቲት 4/2010አ.ም እሁድ ቀን እኔ እነ ሮቢ ቤት ቁጭ ብዬ.........


ይቀጥላል........

· · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkrkalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
170 views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ