Get Mystery Box with random crypto!

ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤ Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤
የሰርጥ አድራሻ: @wubyefkr_kalat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.49K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-01-24 21:10:58 |የድሀ ፍቅር|


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ

|ክፍል 13|


ሜላቴ ደወለችልኝ በጣም እያለቀሰች ነበር። በጣም ስለደነገጥሁ ምን እንደተፈጠረ ጠየቅኃት እሷም አባቷ የመኪና አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል ተጠርታ እየሄደች እንደሆነ ነገረችኝ። በቃ አይዞሽ ሁሉም ለበጎ ነው አባትሽ ምንም አይሆኑም ተረጋጊ አልኳት እሽ በቃ ሆስፒታል ደርሻለው በኃላ እናወራለን ብላኝ ስልኩን ዘጋችው። ደነገጥኩ! አምላኬ ምን ይፈጠር ይሆን አባቷ ምንም እንዲሆኑ አልፈልግም ሜላቴ ትጎዳብኛለች። በቃ ጌታዬ አደራህን ብዬ ወደ ዶርሜ ገባሁ።
ዶርሜ ውስጥ ቁጭ ብዬ ስልኬን መጠባበቅ ጀመርኩ እስካሁን አልደወለችም ግራ ገባኝ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ማንም ጋ መደወል አልቻልኩ እናቴ ጋ ለመደወል አስቤ እሷን ማስጨነቅ ስለመሰለኝ ተውኩት። ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ማጥናት ባልችልም ከደብተሬ ጋ ግን ተፋጠጥን።
ሜላቴ አልደወለችም በጣም ሲብስብኝ ምን ተፈጠረ የኔ ፍቅር ብዬ ሜሴጅ ላኩላት። ደህና ነው ትንሽ ቆይቼ እደውልልሀለው እሽ አለችኝ ትንሽ ተረጋጋሁ... ወደ ጥናቴ ተመለስኩ ሰአቱ እየመሸ ስለነበር ከዶርም አልወጣሁም። ወዲያው እናቴ ደወለችልኝ ሰላም አለችኝ ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቅኃት ምንም አልተፈጠረም ሜላት ደውላ ደውዬ እንድነግርህ ነግራኝ ነው አባቷ ደህና ናቸው ምንም አልሆኑም ዛሬ ሆስፒታል ስለሚያድሩ እሷም እዛው ነው የምታድረው ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው ብላሀለች አለችኝ እሽ አልኳት ...የአባቷ ደህና መሆን አስደስተኝ።
ጠዋት ተነስቼ ወደ ክላስ ከመግባቴ በፊት ለሜላት ሜሴጅ ፃፍኩላት" አባትሽ ተሻላቸው አንቺስ እንዴት ነሽ የኔ ፍቅር?" አላየችውም መልስም አልተላከልኝም ወደ ክላስ ገባሁ ,ከትምህርት መልስ ላይብረሪ ገብቼ አጥንቼ ስወጣ ሜላት ደወለችልኝ ይቅርታ የኔ ውድ ለመደወል ስላልተመቸኝ ነው .ምናልባት ሳወራ ስምተው ስልኬን ፈትሽው ቁጥርህን እንዳይወስዱ በማሰብ ነው ይቅርታ አለችኝ እር ችግር የለውም ,አባትሽ ግን እንዴት ናቸው አልኳት ተሽሎቷል ወደ ቤት ልንወስደው ነው እኔም ወደ ቤት እመለሳለው እስከሚሻለው ድረስ አለችኝ።
የሜላት ወደ ቤት መመለስ ቢያስደስተኝም ,ላግባት ያለው ልጅ መምጫው ስለደረስ ግን አሳስቦኛል ,ብቻ ምንም ማለት ስላልፈለግሁ እሽ በቃ ሂጂ አባትሽኝ እግዚአብሄር ጨርሶ ይማራቸው ብያት ስልኩ ተዘጋ ፈተና ለመፈተን ሳምንት ስለቀረን በጣም በጥናት ተወጥሪያለው ወደ ጥናቴ ተመልሼ ሳጠና አመሸሁ ,
ሜላት አንድ ታላቅ እህት አለቻት አላገባችም ማግባት አትፈልግም የመጀመርያ ፍቅረኛዋ በመኪና አደጋ ስለሞተባት ብዙ ተሰቃይታለች ሌላ ወንድ አልፈልግም እሱም ቀርቷል እንኳን ሌላው የሚል አመለካከት አላት . ሜላት እቤቷ ተመልሳለች አባቷም ደህና ናቸው ከቤት ልጁን አባረረ ላለመባል እንጂ ተመልሳ ወደ ቤት እንድትገባ አይፈልጉም ነበር.,
ሜላት ስልክ ደውለችልኝ እቤት እንደሆነችና ማታ ነገ እንግዳ እቤት ይመጣል ስለተባልኩ ብር ያስፈልገኛል ላክልኝ አለችኝ እሽ ብዬ የራሷን ብር አውጥቼ የምትፈልገውን ያክል ላክሁላት.እንግዳው ማን እንደሆነ አላውቅም ግን ሲያወሩ የሰማሁት የአባቴ የስራ ባልደረቦች እንደሆኑ ነው አለችኝ ችግር የለውም ብቻ እራስሽን ጠብቂ አልኳትና ስልኬን ዘግቼ ወደ ጥናት ተመለስኩኝ.,
እኔ ከተመረቅሁ በኃላ ቶሎ ስራ ይዜ ሜላቴን ማስደሰት እናቴን ማስደስት ነው የምፈልገው .,ለዛም ነው የምችለውን ያክል ጠንክሬ የምማረዉ.ሜላቴ ቀኑን ሙሉ አልደወለችም እንግዳ አለ ስላለች ልረብሻት ስላልፈለግሁ ዝም ብዬ አመሽሁ .ሜላቴ ደወለችልኝ .የሚገርም ነገር ልንገርህ አለችኝ በደስታ እየተፍለቀለቀች ምን ተገኝቶ ነው ንገሪኝ እስኪ የኔ ፍቅር አልኳት ሜላቴ ፍፁም ደስተኛ ነበረች......

ይቀጥላል....
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌
748 viewsedited  18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 22:30:24
ደሜ ውስጥ ፍቅርሽ አለ.......

Join us
https://t.me/joinchat/S8FWZpKrYoiM6yX2

@zii_zuo
758 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 22:30:24
........ያንቺን ስም ብቻ....

Join us
https://t.me/joinchat/S8FWZpKrYoiM6yX2
703 views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-23 21:24:53 ​​<የድሀ ፍቅር>

እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ

ክፍል 12

ፈተና ስለደረስብኝ ለማጥናት ላይብረሪ ቆይቼ ስመጣ በጣም ብዙ miss call አገኝው እናቴም ሜላትም ደውለው ነበር በጣም ደነገጥኩ ደግሜ ስደውል ስልካቸውን አያነሱም ግራ ገባኝ .በሜላት ስልክ ትንሽ ታገስኝ እሰውላለው የሚል ሜሴጅ ደረሰኝ... ትንሽ ተረጋጋሁ...
ከትንሽ ቆይታ በኃላ ሜላት ደወለች .በፍጥነት አነሳሁት ምንድነው ምን ተፈጠረ ሜላቴ አልኳት ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አለችኝ እና ለምን ይሄን ያክል ጊዜ ደጋግማችሁ ደወላችሁ አልኳት የኔ ውድ እንዳትደነግጥ በጥሞና አዳምጠኝ ,አለችኝ እሽ አልኳት ግን ምንድነው አልኳት ልቤ ፍራት ፍራት እያለው .ካልተረጋጋህ ልነግርህ አልችልም አለችኝ እሽ !እሽ ! ንገሪኝ አልኳት ለመረጋጋት እየሞከርኩ..
እየውልህ የኔ ፍቅር ዛሬ ትንሽ ችግር የፈጥሯል አንተ ትምህርት ልትጨርስ አንድ ወር ነው የቀረህ አይደል እኛ ደግሞ ይቺን አንድ ወር በዘዴ ማለፍ ይኖርብናል አለችኝ ምንድነው ግራ ገባኝ እኮ ንገሪኝ አልኳት,.ውስጤ ግን ይበልጥ ፍርሀት ውስጥ ገብቷል.ምን መሰለህ የኔ ውድ ማታ እንደነገርኩህ አባቴ ሌላ ቦታ ለስራ ሊሄድ ነበር, ነገር ግን ጠዋት ትንሽ ችግር ተፈጥሮ እኔ ከቤት ወጥቻለው አለችኝ .,ደነገጥኩ ለምን እንዴት ብዬ ጥያቄየን አፋጠንኩት.ተረጋጋ አባቴ ውሳኔየን ሲጠይቀኝ የማላውቀውን የማልወደውን ሰው ማግባት እንደማልችልና እንደማልፈልግ ስነግረው ከቤት አባረረኝ አሁን እናንተ ቤት ነኝ አለችኝ ..
ብደነግጥም ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌው,.ወይኔ በጌታ እሽ በቃ እሱው ጋ ሁኚ ግን ተጠንቀቁ አልኳት ችግር የለውም እኔ ግን የደወልኩት ዋነኛው ምክንያት ይሄ አይደለም አባቴ ምናልባት የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰህና ያለህበትን ካወቀ ችግር እንዳያደርስብ እንድትጠነቀቅ ልነግርህ ነው ምክንያቱም በጣም ሲዝት ነበር አለችኝ.አይ ችግር የለም እዚህ ምንም አይፈጠርም አታስቢ አልኳት .
አባቷ እኔን ምንም ማድርግ አይችሉም የፈራሁት ለወንድሜና ለእናቴ ነው ምንም እንዲሆኑብኝ አልፈልግም .ሜላቴንም ማጣት አልፈልግም .,እሷ ሀብታም እኔ ድሀ ሆነኜ ያለን ፍቅር እሷም እንደኔ ድሀ ስትሆን ይዘልቅ ይሆን ?አላውቅም ብቻ ግን አሁን ላይ አፈቅራታለው ሁሉም ምንም አይሁኑብኝ .,የሚገርመው እኔ ሳላውቅ ሜላቴ ብር በእኔ አካወንት ማስገባቷን ስትነግረኝ ደነገጥኩ ብዙ ብር ነው ስፈልግ ስፈልግ ትልክልኛለህ ይቀመጥ ለጊዜው ትንሽ ብር እጄ ላይ አለ አለችኝ እሽ አልኳት.,
ሜላት እኛ ቤት መኖር ከጀመረች ሳምንት ሆኗቷል እኔም ፈተና ስለደረሰብኝ በጥናት ተወጥሪያለው በቃ ብቻ ስለ ወደፊቱም አስባለው .አንዳንዴ የነገን አምላክ ያውቃል ብዬ እተወዋለው ሜላት እኔ ጋ መምጣት ፈልጋ ነበር እኔ ግን የፈተና ሰአት ስለደረስ አትምጪ አልኳት ምክንያቱም እሷን ትቼ ማጥናት አልችልም ግዴታ አብሪያት መዝናናት ይኖርብኛል .እሷም ስለተረዳችኝ ምንም አላለችኝም እሽ ብላ ቀረች.,
ሜላት ስራ አቁማለች ምንም አትሰራም እኛ ድሮ ከምንኖርበት ቤት ለቀው ሌላ ቦታ ተከራይተው ነው የሚኖሩም ምክንያቱም ወንድሟ ቤታችንን ያውቀው ስለነበር እንዳያገኛት በማሰብ ነበር .የሜላት እናት ለሜላት እባቷ ሳያውቅ ብርም አንዳንድ ነገር ያደርጉላታል እባቷ ግን ደውለው አያውቁም .የት እንደምትኖርም ለማጣራት አልፈለጉም ብር ስትጨርስ ተመልሳ ትመጣለች ብለው አስበዋል.እሷ ግን ወደ ቤት አልተመለሰችም ነበር..,
ማታ ሳጠና አምሽቼ ጠዋት ተነስቼ ሻወር ወስጄ ወደ ላይብረሪ ሄድኩኝ ትንሽ አጠናሁና ተመልሼ ወደ ዶርም ገባሁ .ሜላቴ ደወለች በጣም እያለቀሰች ነው እባቷ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ሆስፖታል ገብተዋል ተብሎ ተነግሯት ወደ ሆስፖታል እየሄደች መሆኑን ነገረችኝ ደነገጥኩ ምንም አባቷ ሊለያዬን ቢፈልጉም ምንም እንዲሆኑ ግን አልፈልግም ነበር በቃ አይዞሽ ተረጋግተሽ ሂጂ አልኳት .በቃ ደረስኩ ብላኝ ስልኩ ተዘጋ እኔም ቆሜ ቀረሁ ......

ይቀጥላል....
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr\_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌
4.4K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 20:50:56 ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| pinned «​​የድሀ ፍቅር እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ ክፍል 11 የመጨረሻ አመት ተመራቂ ስለሆንኩ በጣም ተወጥሬ እያጠናሁ ነው አንደኛው ሲሚስተር አልቆ ሁለተኛው ሲሚስተር ላይ ነን አጋጣሚ ላይብረሪ ከምሄድ ማንም ዶርም ውስጥ ስለሌለ እዚሁ ላጥና ብዬ እያጠናሁ ነበር .ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች.ስልኩን…»
17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-21 18:30:00 ​​የድሀ ፍቅር


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ

ክፍል 11


የመጨረሻ አመት ተመራቂ ስለሆንኩ በጣም ተወጥሬ እያጠናሁ ነው አንደኛው ሲሚስተር አልቆ ሁለተኛው ሲሚስተር ላይ ነን አጋጣሚ ላይብረሪ ከምሄድ ማንም ዶርም ውስጥ ስለሌለ እዚሁ ላጥና ብዬ እያጠናሁ ነበር .ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች.ስልኩን አነሳሁት የኔ ፍቅር እንዴት ነሽልኝ አልኳት ድምፃ ደስ አይልም ነበር.አለውልህ እንዴት ነህልኝ ውዴ አለችኝ.
ሜላቴ የሆነ ነገር ካልሆነች በስተቀር እንደዚህ ፍዝዝ ብላ አታወራኝም.ደግሞ ምን ተፈጠረ ወይ አምላኬ አልኩ በልቤ.ምነው የኔ ፍቅር ምን ሆንሽብኝ ድምፀሽ ትክክል አይደለም አልኳት.ውዴ ግራ ገብቶኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች ምንድነው ምን ተፈጠረ ንገሪኝ አልኳት .አባቴ መልስሽ ከዛሬ እንዳያልፍ ወይ እሽ ወይም እንቢ ብለሽ አታስጠብቂኝ መልሱን ማታ እንድትነግርትኝ ብሎኛል አለችኝ እያለቀሰች .ደነገጥኩ በጣም ምን ትበላቸው.,
የኔ ፍቅር ተረጋጊ መፍትሄ አናጣም አልኳት ""እሽ በይ እንዳትለኝ ብቻ ""አለችኝ በጩኸት አላደርገውም የኔ ፍቅር አልኳት .አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት .እሷም አፈቅርሀለው.እሽ መቼም አልለይህም ሁሌም አብሬህ ነኝ .ለማንኛውም በቃ በኃላ አወራሀለው ብላኝ ስልኩ ተዘጋ ተረበሽኩ ግን ምን ላድርግ ምንም .ማጥናት እንኳን አልቻልኩም ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ከሜላቴ ጋር ሆኜ ያሳለፍኳቸው እያንዳንዶ ጊዜና ሰአት ድቅን ብለው በትዝታ ወሰዱኝ.,
ሜላት ስልኩን ዘግታ ባንክ ሄዳ ያላትን ብር እንዲሁም ሌላ ብር ጨምራ ወደ እኔ አካወንት ውስጥ ታስገባዋለች እኔ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም.ሜላት ይሄንን ያደረገችው .አባቷ ጨክነው ከቤት ብትባረር እንኳን ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ይሆናል ብላ አስባ ነበረ .ወደ ቤቷ ከመሄዷ በፊት ደወለችልኝ አባቷን በፍፁም ማሳመን ስለማትችል በቃ አልፈልገውም ማግባት አልፈልግም ብላ መልስ ለመስጠት እንደተዘጋጀችና ወደ ቤት መግባቷን ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ.,
እኔም ፀሎቴን ቀጠልኩ ምንም እንዳይፈጠር አምላኬ ሆይ አደራህን አልኩት,በቃ ግራ ስለገባኝ ለእናቴ ደወልኩላት , ሰላም ካልኳት በኃላ ድምፄ ስለተቀየረባት ምን ሆንክ ብላ ጠየቀችኝ መቼም የእናት አንጀት ሆኖባት ምነው ልጄ እራበህ ጠማህ ምንድነው ድምፅእህ አለችኝ .እኔም ሁሉንም ነገር ነገርኳት ጨንቆኛል አልኳት አይዞህ አምላክ ያውቃል ልጄ አለችኝ እሽ .,እማ ምን አደርጋለው በፀጋ መቀበል ነው ብዬ አሰብኩ ,ልጄ አላማህን እንዳትረሳ ይቺ ልጅ ያንተ ከሆነች የትም አትሄድም እሽ በትምህርትህ በርትተህ እኔንም እሷንም ማስደሰት ይኖርብሀል አለችኝ ,እናቴ እውነቷን ነው እሽ እማ በቃ ሰላም እደሩ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት ,
እናቴ ያለችኝን ነገር እያሰብኩ ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ግን ጥናት ማጥናት አልቻልኩም.ወዲያው ሜላት ደወለች ምን !ምን!ተፈጠረ አልኳት በፍጥነት.ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አባቴ ድንገት ስራ ተብሎ ነገ ከከተማ ስለሚወጣ በጊዜ ተኝቷል ከሳምንት በኃላ ፈጣሪ ያውቃል አለችኝ .ተመስገን ጌታዬ አልኩ ደስ አለኝ .ትንሽ ተሳስቀን ደህና እደሪ ደህና እደር ተባብለን ስልኩ ተዘጋ.ከዚህ በኃላ ማጥናት አለብኝ ብዬ ማጥናት ጀመርኩኝ.,
በማግስቱ ጠዋት ስልኬት ትቼ ወደ ትምህርት ገብቼ ስለነበር ስልኬ ሲደወል ማወቅ አልችልም .በደንብ በጥሩ መንፈስ ተማርኩኝ .ላይብረሪም ገብቼ ሳጠና ቆየሁ .ከዛ ሜላቴ ትዝ ስትለኝ ልደውልላት ብዬ ወደ ዶርማችን ሄድኩ ስልኬን ሳነሳው ያየሁት missed call ከሁለት መቶ በላይ ነበር እናቴና ሜላት ነበሩ ደነገጥኩ.,ስልኬን አንስቼ በመጀመርያ እናቴ ጋ ደወልኩ ግን አታነሳም ለሜላትም ስደውል ስልኳ አይሰራም., ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ግራ ገባኝ .በዛው ደቂቃ ትንሽ ቆይ መልሼ እደውላለው የሚል ሜሴጅ በሜላት ስልክ ተላከልኝ.......

ይቀጥላል....
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr\_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
878 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 20:42:58 ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| pinned «​​የድሀ ፍቅር እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ ክፍል 10 እኔና ሜላቴ አብረን እየተነጋገርን ማልቀስ እንደሌለባት እየመከርኳት እያለ ድንገት የሜላት ስልክ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኩን እንዳነሳችው ሰላም እንኳን ሳይሏት የት ነሽ አልዋት .ሜላትም እረጋ ብላ አባቢ እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ መጣሁ አለች በትህትና…»
17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:20:13 ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| pinned «​​የድሀ ፍቅር {ክፍል 9} እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ ሜላቴ እቤት መጥታ ተጠምጥማ ሰላም አለችን ከድሮዋ ተለውጣብኛለች ፈገግታዋ የለም እንዲያውም እንባዋ ቅርር ብሏል ,ሜላቴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሻል አልኳት ,ከመቀመጫዋ ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ግራ ገባኝ ,ሜላቴ ለመጀመርያ…»
18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-18 21:19:49 ​​የድሀ ፍቅር {ክፍል 9}


እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በጣፋጭ የፍቅር ቃላት የ ቴሌግራም ቻነል ተዘጋጅቶ የቀረበ



ሜላቴ እቤት መጥታ ተጠምጥማ ሰላም አለችን ከድሮዋ ተለውጣብኛለች ፈገግታዋ የለም እንዲያውም እንባዋ ቅርር ብሏል ,ሜላቴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሻል አልኳት ,ከመቀመጫዋ ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ግራ ገባኝ ,ሜላቴ ለመጀመርያ ጊዜ ከአይኗ እንባ ሲወርድ አየሁ በሳቅና በደስታዋ ነው እኔ የማውቃት,.
በጣም ግራ ገባች ምን ሆነሽ ነው ይሄን ያክል ናፍቄሻለው እንዴ አልኳት እየቀለድኩ ,ማልቀሷን አላቆመችም ምን ሆንሽብኝ ብዬ እንባዋን ጠራረግሁላት እስኪ ንገሪኝ ምንድነው የተፈጠረው?አስከፋሁሽ?ያስከፋሽ ሰው አለ ምን ሆንሽ የኔ ፍቅር አልኳት እንባዋን ለማስቆም እየሞከርኩ,.
ሜላቴም እንባዋን ለማስቆም እየታገለች በሚያሳዝን ድምፅ እወድሀለው! አፈቅርሀለው! ካንተ ተለይቼ መኖር አልችልም አለችኝ ,እንዴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሽ ነው ምን ተፈጠረ አልኳት ,ሜላቴም ከልብ አዝና እንደዚህ ብላ የተፈጠረውን ነገረችኝ.,
በጣም እያዘነች አባቷ ሊድሯት እንደሆነ ነገረችኝ, ከአባቷ ጋር አብሮ የሚሰራ አንድ ሀብታም ልጁ ከአሜሪካ ተመልሶ ሀገሩ ተመልሶ መኖር ስለሚፈልግ እኔን እንዲድርለት ሲጠይቅ አባቴ እሽ አላቸው ግራ ገብቶኛል አይሆንም ካልሽ ልጄ አይደለሽም አላውቅሽም አታውቂኝም ብሎ አስፈራርቶኛል አለችኝ እንባዋ እየወረደ,.
የምላት ስለጠፋብኝ ዝም አልኩ እኔ እሷን የኔ ማድርግ የምችለው በፍቅር ብቻ ነው .በሌላ ነገር በምንም የኔ ማድርግ እንደማልችል አውቃለው... በተለይ አባቷን በምንም ነገር ማሳመን እንደማልችል ሲገባኝ ተሰፋ የመቁረጥ ስሜት ተሰማኝ ግን እሷን ይበልጥ ማሳዘን ስላልፈለግሁ አይዞሽ በቃ አታልቅሺ አልኳት ስሜቴን እየደበቅሁ,.
እኔም አንድ አመት ነው የቀረኝ ለመመረቅ ስለዚህ አብረን እንሆናለን እስከዛ ግን ጠንካራ መሆን ይኖርብናል አልኳት እሽ ግን ያገባሻል የተባልኩት ልጅ አመት ያክል የሚቆይ አይመስለኝም አለችኝ .አይዞሽ ተሰፋ አለን ግን አባትሽን እሽ እንዳትያቸው ቆይ እያልሽ ትንሽ እንዲቆይ አድርጊ,ሜላቴ የኔ ፍቅር አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት,.አቀፈችኝ አፈቅርሀለው እኔም ላጣህ አልፈልግም አለችኝ.,
ሜላት ድንገት ስልኳ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኳን አነሳችው የት ነሽ የሚል ጥያቄ አቀርብላት ሰላምም ሳይሏት አለው እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ አለቻቸው የት እንዳለሽ አውቃለው እዛ የድሀ ልጅ ጋ ነሽ አይደል ሲሉ እኔና ሜላት አይን ለአይን ተያየን,........

ይቀጥላል.....


‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ · · • • • ጣፋጭ ታሪክ • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr\_kalat // ,, @wubkalat
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷
249 views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 22:49:20
#profile_pic

.....ህይወቴ ነሽ....

http://t.me/joinchat/AAAAAEun43lpI7QeydrF-Q

@wubyefkr_kalat
@wubyefkr_kalat
255 views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ