Get Mystery Box with random crypto!

ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤ Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ wubyefkr_kalat — ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤
የሰርጥ አድራሻ: @wubyefkr_kalat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.49K

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2021-11-02 20:37:54 ZZ ጣፋጭ የፍቅር ቃላት pinned «​​. ሀሊማ ክፍል ሶስት : : ፡ የተወሰነ መንገድ ከሄደች በኃላ ግን ውስጧን የሆነ ነገር ከነከናት እና ልጅቷ ምን ሆና ይሁን ብላ አሰበች ለምን ሄጄ አልጠይቃትም ብላ አሰበች ትንሽ ቆም ብላ አሰበችና ወደ መጣችበት መንገድ ተመለሰች ነገር ግን ሀሊማ ከነበረችበት ቦታ ለቃ ሄዳለች ፋጡማ በጣም ተናደደች ለምን መጀመሪያ ሄጄ አላናገርኳትም ብላ እራሷን ወቀሰች እዛው አካባቢ…»
17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 20:23:06 ​​. ሀሊማ


ክፍል ሶስት
:
:

የተወሰነ መንገድ ከሄደች በኃላ ግን ውስጧን የሆነ ነገር ከነከናት
እና ልጅቷ ምን ሆና ይሁን ብላ አሰበች ለምን ሄጄ አልጠይቃትም
ብላ አሰበች ትንሽ ቆም ብላ አሰበችና ወደ መጣችበት መንገድ
ተመለሰች ነገር ግን ሀሊማ ከነበረችበት ቦታ ለቃ ሄዳለች ፋጡማ
በጣም ተናደደች ለምን መጀመሪያ ሄጄ አላናገርኳትም ብላ እራሷን
ወቀሰች እዛው አካባቢ ዞር ዞር እያለች መፈለግ ጀመረች ወደ
አንዱ አቅጣጫ ስትመለከት ሀሊማ በተዳከመ አቅሟ እየተጎተተች
እየሄች ተመለከተቻት በጣም ቢራራቁም ማየት ችላለች .....
በፍጥነት እየተራመደች እርቀታቸውን እያጠበበች ሄደች በጣም
ስትቀርባት ሚጣ.....ሚጡ .... ኧረ ሚ....ጡ.... እያለች
ተጣራች ሀሊማ ግን ጭራሽ አልሰማቻትም አሁንም እየሄደች ነው
ፈጡማ ከመጀመሪያው በላይ በጣም እየፈጠነች የሞት ሞቷን
አጠገቧ ደረሰች እንኪ ሚጡ ብላ እጇን ይዛ ወደ እራሷ ስታዞራት
ጭራሽ ያላሰበችውን ነገር ነበር ያየችው ሀ..ሊ..ማ አለቻት
ምንም መልስ አልሰጠቻትም እራሷን ለማረጋጋት እየሞከች እዚህ
ብቻሽን ምን ታደርጊለሽ ?? አለቻት የሀሊማ ያለወትሮዋ ዝም
ማለቷ እየገረማት አላወቅሽኝም እንዴ ፋጡማ አክስትሽ እኮ ነኝ
ምንም አይነት መልስ የለም በሁኔታው ግራ እንደተጋባች ፋጡማ
ቤቷ እዛው እቅራቢያ ስለነበር ይዛት ወደ ቤቷ ሄደች ሰውነቷ
ጠውልጎዋል ከንፈሯም ከሚባለው በላይ ደርቆዋል ፋጡማም
ፊቷን እጇን እና እግሯን አጠበቻት ሀሊማ ከቅድሙ ትንሽ እንደ
መንቃት እያለች ነው ወደ ውስጥ ይዛት ገብታ የሚበላ አቅርባላት
እያበለቻት ሳለች ስልኳን አንስታ ወደ አባቷ ጋር ለመደወል ቤት
ልደውልላቸው አይደል አለቻት አንገቷን በመነቅነቅ እንዳትደውል
በምልክት ነገረቻት እሺ ቤት አልደውልም ግን ምን እንደሆንሽ
ንገሪኝ አለቻት ምን ብላ ትንገራት ዝም አለቻት እሺ በቃ ልደውል
ነው ስትላት ሀሊማ በድንገት እንባዋ እንደ ጉድ መውረድ ጀመረ
መናገር ትፈልጋለች ግን አፏ ተሳስሮባታል ፈጡማ በሁኔታዋ ትንሽ
ተረበሸች እሺ በቃ ተይው አትነገሪኝ ብላ ከተቀመጠችበተ ተነስታ
ሀሊማ አጠገብ ሄዳ እቅፍ አባበለቻት በጣም እርቧት ስለነበር
የበላችው ምግብ አደካከማት ገና አቅፋት ጸጉሯን ማሻሸት
እንደጀመረች እንቅልፍ ይዟት ሄደ ፈጡማም ሀሊማ እንደተኛች
ስታይ አስተካክላ አስተኝታት የሀሊማ አባት ጋር ለመደወል ስልኳን
ይዛ ወጣች:......

yketlall ,,,,, ,,,,,

· · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @zii_zuo
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
2.9K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 20:05:27 ​​. ሀሊማ


ክፍል ሁለት


፡......አባቴ መናገር ጀመረ ግን እኔ እንደጠበቁት ሳያሆን የበለጠ
እንደገደላት የሚያረጋግጥ ነገር ነበር የተናገረው.....ሰሙ ልክ ነሽ አለ ግን..... ሲል እንዳትጨርሰው......ምንም ግን የሚባል ነገር የለም ባይሆን ሬሳዋን ምን
እንደምናደርገው እናስብ አለችው....እሺ ልጆቼስ አላት ለእነሱ እኔ አለሁ ደግሞ ተነጋገርንበት
አይደል አለችው..........አባቴ በጣም በጨነቀው ድምፅ እሺ ለ ሀሊማስ እናቴስ
ካለችኝ ምን ልላት ነው........የሆነ ምክንያት እንነግራታለን ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ክፍለ
ሀገር እንደ ሄደች ወይም ሌላ ምክንያት እንነግራታለን አለችው.....ሌላ አማራጭ ስለሌለው እሺ አላት ይህንን ሀሊማ ስትሰማ
ምድር የተደፋባት የህል ነበር የተሰማት በሩን ከፍታ ወደ ወስጥ
ገብታ የእናቷን ሬሳ ለመንካት ድጋሚ የማላገኛት ከሆነ ልሳማት
ብላ አስባ በሩን ጠጋ ለማድረግ ስትሞክር ሰሚራ እጅ ላይ
ያለውን ብረት ተመለከተችው እናቷን ብረቱ መትታት
እንደገደለቻት ስትናገር ሰምታለች የእናቷ እጣ ለ እሷም
እንዳይደርሳት ፈራች ልትከፍተው የነበረውን በር መልሳ ተወችው
የእናቷን ሬሳ ለመደበቅ ሲዋከቡ አየቻቸው ሞት ማለት ምን
እንደሆነ በማታውቅበተ እድሜ ላይ ሆና በንጹህ አእምሮዋ የ
እናቷን አሰቃቂ ሞት የ አባቷ ጭካኔ አየች አባቷ ይህ ሁሉ ሲሆን
ሀሊማ እንደማታውቅ ነው ያሰበው ከመኝታ ቤቱ ለመውጣት
ሲሞክሩ ሀሊማ በሞተ አቅሟ እተንቀጠቀጠች ቤቱ ለቃ ወጣች
በጣም ስለደነገጠች ሰውነቷ ደርቆዋል ወዴት እንደምትሄድ
አታውቅም እንዲሁ እግሯ ወደ መራት አቅጣጫ መሄድ ጀመረች
ረጅም መንገድ ከሄደች በሃላ ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግራ
ገብቷት አንድ ጥግ ላይ ተቀምጣለች............
.....እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሀሊማ በተቀመጠችበት መንገድ
የሀሊማ
የእናቷ የቅርብ ዘመድ የሆነችው ፋጡማ በዚያ መንገድ ስታልፍ
ሀሊማን በ አትኩሮት ተመለከተቻት ሀሊማ ግን ቀድማ ፉጡማን
አይታታለች ግን ማን እንደሆነች ማገናዘብ አልቻለችም
ፉጡማም ግራ በተጋባ ሁኔታ አየቻት ፊቷ አዲስ አልሆነባትም
በደንብ ለማየት ሞከረች ግን የሀሊማ ሂጃብ ስለተዝረከረከ
ከፊል ፊቷን ሸፍኗታል ማን ትሆን እያለች ማሰብ ጀመረች እንደዚ
ትንሽ ልጅ የት ነው የማውቀው ብላ ትንሽ እንደማሰብ ካለች
በኃላ የ አክስቷ ልጅ የሆነችው ዘይነባ የሷ ልጅ ሀሊማ ትሁን ብላ
አሰበች ሀሊማ ብትሆን አይታኝ ዝም አትለኝም እንኳን እንዲ
አይታኝ በ ስልክ እራሱ እንዴት እንደምትሆን እያለች ብቻዋን
እያወራች ደግሞ እዚህ ድረስ ምን ልትሰራ መጣች በዛ ላይ
ብቻዋን አይ እሷ አይደለችም ብላ አልፋት ሄደች.......


ይቀጥላል ...

. · · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @zii_zuo
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
3.4K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-09 19:13:57 ​​​​​​​​​​​​​​​​.
ሀ ሊ ማ
:¨·...............:¨·.

#ክፍል 1



"ህይወት አንዳንዴ እኛ እንደ ምንፈልገው ሳይሆን እሷ እንደ መረጠችው ነው የምንኖረው"
.
ዛሬም እንደ ወትሮዋ ከእኩዮቿ ጋር ለመጫወት ከ ቤት ወጥታ ወደ ጓደኞቿ ጋር ሄደች፡፡ ሀሊማ በጣም ተጫዋች ደስተኛ እና ሁሉም ሰው የሚወዳት አይነት ልጅ ናት የተወሰነ ሰአት
ከተጫወተች ወዲህ እረሀብ ቢጤ ተሰማት ያው የልጅ ነገር እረሀቡን ለማስታገስ ያህል ብቻ ነው እነደነገሩ ምግቡን ቀመስ ቀመስ የሚያደርጉት፡፡ ከዛ ወደ ጨዋታቸው ይመለሳሉ ፡፡ ሰአቱ ከ ጠዋቱ 5፡30 ይላል ሀሊማ ጓደኞቿን ተሰናብታ ወደ ቤቷ ሄደች ፡፡ ነገር ግን እቤቷ ስትደርስ ያልጠበቀችውን ነገር ያጋጥማታል ያ ክስተት ህይወቷ አንዲከብድ ያ ያሰለፈችው ጨዋታ እንዳይደገም የደረገውን ደስታዋ ሁሉ ጠፍቶ ቀሪ ጊዜዋን በ ሀዘን እንድታሳልፍ
ያደረገ ክስተት ነው ሀሊማ በራፍ ላይ ስተደርስ ያልጠበቀችው ነገር ያጋጥማታል ያለ ወትሮ የግቢቸው በር ተከፍቶ ታገኘዋለች ትንሽ ግራ ገባት ምን አልባት ኡሚ እደከፈተችው ረስታው ይሆናል ብላ አሰበች በሩን ድምፅ ሳታሰማ ቀስ አድርጋ ዘጋችው ፡፡ሌላ ግዜ
እንደምታደርገው እናቷን ጋር ሰትደርስ በቀስታ ኮቴ ሳተሰማ ትሄድና ታስደነግጣት ነበር ዛሬም እንደ ወትሮዋ እናቷን ለማስደንገጥ እናቷን ሁሌ ወደ ምታገኝበት ቦታ ኩሽና ሄደች ግን
እንደጠበቀችው አልሆነም እናቷን ኩሽናው ውስጥ ልታገኛት አልቻለችም ምን አልባት ሳሎን ትሆናለች ብላ ወደ ሳሎን ቤት በተመሳሳይ መልኩ እየተራመደች ሄደች ግን እዛም ቢሆን
ተመሳሳይ ነገር ነው ያጋጠማት ሀሊማ እናቷ ያለወትሮዋ ሁሌ ከምታገኛት ቦታ በማጣቷ ትንሽ ግራ ተጋብታ ቁጭ ብላ መጠበቅ ጀመረች ኡሚ ...ኡሚ... ብላ ልትጠራት አስባ ግን ድንገት አንድ
ሀሳብ መጣላተ መኝታ ቤት ለምን አላያትም የሚል አሁንም እዛም ቢሆን ካገኘቻት ከሃላዋ ሆና ለማስደንገጥ እንዲያመቻት ቀስ አያለች ወደ መኝታ ቤቱ አመራች ነገር ግን የሆን ድምጽ ሰማች የ
እናቷ ድምጽ አይደለም ማን ይሆናል ያለው እያለች እየፈራች ወደ ክፍሉ ተጠጋች በሩ አልጠበቀም ነበርና ቀስ ብላ ጠጋ አደረገችው የ አባቷ ድመጽ ሰማች በዚህ ሰአት እቤት ምን ይሰራል ብላ አሰበች ጠዋት ቁርስ ከበሉ በኃላ ስራ እንደሄደ አስታወሰች ታዲያ እንዴት መጣ ብላ እያሰበች በሩን ከመጀመሪያው ትንሽ ጠጋ አድርጋ አንገቷን ወደ ውስጥ አስገባች ግን ምንም ያልጠበቀችው ነገር ነበረ የተመለከተችው ሁለት አንድ አመት ያልሆናቸው ታናናሽ መንታ እህትና ወንድሟ አልጋው ላይ እን ተኙ ናቸው፡፡ የሀሊማ እናት ግን
:
:
አልጋው ግርጌ ጋር በጀርባዋ ተንጋላ ወድቃለች ከ አንገቷ አካባቢ ደም እየፈሰሰ ነው፡፡ አባቷ ደንግጦ ባለበት ደርቆ ቆሞዋል ከአልጋው ጎን ሰሚራ የሆነ ብረት የሚመስል ነገር ይዛ ቆማለች
ሰሚራ ማለት ጓረቤታችን እና የ እናቴ የቅርብ ጓደኛ ነች እኔ ሳልወለድ ጀምረው ጓደኛ ናቸው አሁን እኔ ሰባት አመቴ ነው እነሱ ከዛም በፊት ጀምሮ ጓደኛ ናቸው ነገር ግን ዛሬ ያየሁትን ነገር ማመን አልቻልኩም ብረቱን ለምንድነው የያዘችው ምን ልታደርግበት ነው ብዬ አሰብኩ...... አባቴ ራሱን ከመሳት በማይተናነስ መልኩ ነበር ደንግጦ
የቆመው፡፡ አባቴ ትንሽ ወደ እራሱ እንደመመለስ ሲል ወደ እናቴ ተጠግቶ ለማንሳት ሲሞክር በድንገት ሰሚራ ፊቷን አጨማዳ
.
"ምን ለማድረግ እየሞከርክ ነው" ብላ ጮኧችበት .......ወደ ሀኪም ቤት ልወስዳት ነው አላት እየተርበተበተ
በምላሹም ሰሚራ ......."ከዛስ ባክህ ምን ሆና ነው ሲሉህ ምን ልትላቸው ነወ እኔ እና የባለቤቴ ጓደኛ በጣም ስለተዋደድን እሷን ደግሞ መፍታት ስለማልችል እኔ እና ሰሚራ ተመካክረን
ልንገድላት አስበን ሰሚራ በብረት ጭንቅላቷን መታት ነው ብለህ
ልትነግራቸው ነው " ብላ አፈጠጠችበት ይሄን ስሰማ በዛ በጨቅላ አቅሜ መሸከም ከምችለው በላይ ነበር ሰሚራ ብረቱን ለምን እንደያዘችው ያኔ ነበር የገባኝ መቋቋም አቃተኝ የሰማሁትን
ማመን አልቻልኩም አንድ ሰው ከሞተ ድጋሚ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችል ነበር እናቴ የነገረችኝ ታድያ እናቴንም ድጋሚ ላገኛት አልችልም ማለት ነው .......ስለ ሞት እንኳ በቅጡ
አላውቅም ነበር አይሆንም አባቴ እንዲህ አያደርግም አባቴ እናቴን በጣም ነወ የሚወዳት እያለኩ ከ እራሴ ጋር አወራለሁ፡፡ አባቴም መናገር ጀመረ ይበልጥ ተጠግቼ ማዳመጥ ጀመርኩ እሱ ይሄን እንደማያደርግ እንዲያረጋግጥልኝ በማሰብ ግን.....


ይቀጥላል ...

. · · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·
╰── ──╯
••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @zii_zuo
✶⊶⊷ ⊶⊷ ❍ ⊶⊷⊶ ⊷✶
3.4K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-01 18:53:10
አሪፍ አዝናኝና አስተማሪ የፍቅር ታሪክ ነው ...

@wubyefkr_kalat
@zii_zuo
3.4K viewsedited  15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ