2022-01-28 23:23:38
ሐሊማ
ክፍል 11
፡
፡
፡
ሀሊማ ድንገት ወደ ፈጡማ ስትዞር የፋጡማ አይን
ፈጦዋል ሀሊማ ደንግጣ ባባ አክስቴን ተመልከታት ብላ ጮኃችበት
ከድር በጣም ደንግጦ ፋጡማ .....እህት ፋጡማ እያለ ጮኃ
ፋጡማ ግን እስከመጨረሻ አሸልባለች ከድር አይኗን ገርበብ
አደረገላት ሀሊማ ባባ ምን እያደረክ ነው ልጄ አይዞሽ እኔ ከጎንሽ
አለሁ ምን እያልከኝ ነው አክስትሽን ድጋሚ አናገኛትም ሞታለች
አላት ሀሊማ የሰማችውን መቋቋም አቅቷት እራሷን ስታ ወደቀች
ከድር የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው ባንድ በኩል የፋጡማ ሬሳ
አለ በሌላ በኩል ልጁ እራሷን ስታ ወድቃለች ሰሚራ ጋር ደውሎ
እንድትረዳው ጠየቃት ግን እንደ እድል ሆኖ ሰሚራ የፋጡማን ቤት
አታውቀውም በምልክት እንድትመጣ ነገራት ሰሚራም ታክሲ
ተኮናትራ ከከድር ጋር እየተደዋወለች በምልክት ደረሰች ከድር ከ
እቤት ወጥቶ ተቀበሏት አንድ ላይ ወደ ቤቱ ገቡ ሀሊማ ልትነቃ
ስላልቻለች ከድር አቅፎ ወደ ሀኪም ቤት ይዟት ሄደ፡፡
ሰሚራ ከፋጡማ ጋር ብቻዋን ነች በጣም ፈርታታለች ልትቀርባት
አልቻለችም ፋጡማ የቀረ ዘመድ የላትም ሰሚራ ለጥቂት ግዜ
ተረጋግታ አስባ አንድ ሀሳብ መጣላት የፋጡማ ጎረቤቶች ጋር
ሄዶ መናገር ወዲያው ከ ቤቱ ወጥታ ለተወሰነ ሰው ተናገረች
የሰፈሩ ሰው ተባብሮ ድንኳን ተደኮነ ሬሳውንም እንዲከፈን
ተደርገ ሁሉም ነገር ቦታ ቦታ እየያዘ ነው በዚህ መሀል ግን
ሰሚራ እንደዛ በብጣሽ ጨርቅ ጠቅልላ የጣለችው ሬሳ ትዝ
አላት ስራዋ ለእራሷ ቀፈፋት አሁን ቢቀፋትም ባይቀፋትም ከ
አለፈ ወዲያ ምን ያደርጋል ......
ሀሊማ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ነቃች ከድር ትንሽ ሰላም ተሰማው
ወዲያውኑ ዶክተሩን ጠራው ዶክተሩም የተወሰነ ነገር ቼክ
ካደረገ በኃላ ከድርን 1 ውጪ ላናግርህ ብሎ አብረው ከክፍሉ
ወጡ በሩን ጠጋ አድርጎላት መነጋገር ጀመሩ ያን ያህል አደጋ
ላይ ሊጥላት የሚችል ነገር የለም አንዳንድ ሰው ከመጠን ያለፈ
ደስታ እና ሀዘን ሲያጋጥመው መቋቋም ያቅተውና እንደዚህ
አይነት ችግር ሊፈጠር ይችላል ብሎ ዶክተሩ ለ ከድር ይነግረዋል
የተወሰነ ሰአት እረፍት ታድርግና ትወጣለች ብሎ ዶክተሩ ከድርን
ተሰናብቶ ይሄዳል ከድር የሀሊማን ጉዳይ ከሰማ በኃላ ወደ
ሰሚራ ጋር ይደውላል ሰሚራ ከሰፈር ሰዎች ጋር አንዳንድ
ነገሮችነ ነው 6፡00 ይላል ሰአቱ የዝሁር ሰላት ሰአት እየደረሰ
ነው ከድር ከሀኪም ቤቱ አሁን ካሎጣ ሰአቱ ይሄዳል ሀሊማንም
ጥሎ መሄድ አይችልም ከድር ወዲያውኑ ወደ ዶክተሩ ቢሮ ሄዶ
ለዶክተሩ ሁኔታውን አሰረዳው ዶክተሩም ሀሊማን ይዟት እንዲሄድ
ፈቀደለት ከድር ዶክተሩን አመስግኖ ያለበትን ሂሳብ ከፍሎ
ሀሊማን ይዞ ወደ ፋጡማ ቤት መሄድ ጀመሩ የሰሚራን ጩኃት
እያሰበ ነው እስከ አሁን ብቻዋን እንደሆነች ነው የሚያውቀው
ወደ ፋጡማ ቤት የሚወስደው ቅያስ ጋር ሲደርስ ሀሊማ
በድጋሚ እራሷን እንዳትስት ፈራ ሰአቱ 6፡25 ይላል ወደ እቤት
ላድርሷት ቢል እንኳ ሰአቱ አይበቃውም አማራጭ ስለሌለው
ሀሊማን ወደ ፋጡማ ቤትይዟት መሄዱን ቀጠለ ቤት ሲደርሱ
ድንኳን ተደኩኖ ያያል ማን እንዲህ እንዳደረገ ለማወቅ በፍጥነት
ወደ ውስጥ ገባ ጭራሽ ያልጠበቀው ነገር ነበር ሀሊማ አካሏ
ነው እንጂ የለችም ማለት ይቻላል ወደ ወስጥ ሲገባ
የሚያለቅስ ሰው ምግብ የሚሰራ ሰው ብቻ ግቢው በሰው
ተሞልቶ ከድር በጣም በተገረመ ሁኔታ ያያል የሰውን ሁኔታ ሲያይ
እሱም ሚስቱ ትዝ አለችው አንገቱን ደፍቶ ወደ ውስጥ ገባ
ሰሚራን በአይኑ መፈለግ ጀመረ ሰሚራ አይታው ስለነበር ወደ
ከድር መጣች ከድር ሰሚራን እንዳገኛት በቅድሚያ የጠየቃት
ስለ ፋጡማ ሬሳ ነበር ሁሉንም ነገር ነገረችው እና ሬሳውም
መስጅድ ወስጥ እንዳለ ነገረችው ሀሊማን ወደ መስጅድ ይዟት
ሄዶ እንድትሰናበታት አደረገ ከዝሁር ሰላት በኃላ ተሰግዶባት
ተቀበረች...........
ሰው ትንሽ ቀዝቀዝ ብሏል ከድር ሀለቱን ለጆቹን ይዞ መጣ
ሁሉም አንድ ላይ ናቸው ሀሊማን ከፋጡማ ሞት ይልቅ የእናቷ
አሟሟት ነው ይበልጥ የጎዳት በስርአቱ እንኳን
አልተለቀሰላትም.....
በዛ ላይ አንድ አለችኝ የምትላት ፋጡማን መጣቷ ጓደኛዋ እናቷ
አክስቷ በቃ ሀሉ ነገሯ ነበረች ሀሊማ አሁን ከምንም ጊዜውም
በላይ ብቸኝነት ተሰማት.....
፡
፡
፡
ዛሬ ፋጡማ ከሞተች ሶስተኛ ቀኗ ነው እንደመጀመሪያው ቀን
የሰፈሩ ሰው በጋራ ሆነው ድንኳኑን አፈረሱት ሀሊማ ሀዘኑን
ለመርሳት እየሞከረችነው ጠንካራ ለመሆን እየጣረች ነው የ
አክስቷን አላማ ለማሳካት ወስናለች ከ ሳምንት በኃላ እነ ከድር
ወደ እቤታቸው ተመለሱ ሀሊማ ሀዘኑ አለቀቃትም ለ እህትና
ለወንድሟ ብላ ጠንካራ መሆን አለባት እሱን እያሰበች ጠንካራ
ለመሆን እየሞከረች ነው ክረምት አልፎ በጋ እየመጣ ነው
ሀሊማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገብታለች እህትና
ወንድሞቿም ትምህርት ጀምረዋል ሀሊማ በመጀመሪያ
ሴሜስተር የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያው ነጥብ የእሷ ነበር
አባቷ በሀሊማ ውጤት በጣም ተደሰተ የሀሊማ ወንድም እና
እህትም ሀያትና መሀመድ 1ኛ እና 2ኛ ወጡ ይህ ውጤት
የሀሊማ የልፍት ውጤት ነው ሁለቱም ሀሊማን እንደ እናትም
እንደ እህትም ነው የሚያዮዋት እሷም ቢሆን የእናትነቱም
የእህትነቱን ሀላፊነት በሚገባ ትወጣዋለች ሀሊማ ለሰሚራ
ከምንም ግዜ በላይ ጥሩ እየሆነችላት ነው እናቷ የምታደርጋቸው
ነገሮችን ሀሊማም እያደረገች ነው፡፡ ሰሚራ በስራዋ እንድትፀፀት
እያደረገቻት , በይበልጥ ደግሞ ህሊነዋ እንዲወቅሳት
እያደረገቻት ነው ለከድርንም ቢሆን አንድ አይነት ነገር
እያደረችው ነው ሰሚራ በከድር ልጆች የቀናች ይመስላል ከድር
ከስራ እስኪመለስ ጠብቃ እራት በልተው ጨርሰው ሁሉም ተኙ
ከድር እና ሰሚራ ብቻ ሲቀሩ ከድር ከድር አለችው ለዘብ ባለ
ድምፅ አቤት አንድ ጥያቄ ለጠይቅህ ነበር ምንድ ነው ጠይቂኛ
እኔ ለ አንተ ምንህ ነኝ?
ዝም አላት ብትጠብቅ መልስ የለም እሺ አትመልስለኝ ግን ልጅ
መውለድ እፈልጋለሁ ቢያንስ ይሄን መልስልኝ......
,,,,, ,,,,,
••●◉Join us share◉●••
3.5K views20:23