Get Mystery Box with random crypto!

............ የበረራው ሰዓት ደረሷል ፣ መንገደኞች ለፈተሻ ተሰልፋዋል አንዲት ሴት በአየ | ZZ |ጣፋጭ የፍቅር ቃላት| ❤

............

የበረራው ሰዓት ደረሷል ፣ መንገደኞች ለፈተሻ ተሰልፋዋል አንዲት ሴት በአየር መንገድ ማረፊያ (Airport)ውስጥ ካለ ሱቅ አንድ ሱቅ የተጠበስ ድንች ( ቺፕስ መግዛት ፈለጋለች እየበላች ልትገፋው አስባለች አንድ አሽ ጋ ቺፕስ ገዛችና በቦርሳዋ ውስጥ ጨመረች ፍተሻዋን አጠናቃ አውሮፕላን ውስጥ ገባች ፣ ከጎኗ የተቀመጠው ሰው ሰላምታ ሰጣት ቀዝቀዝ ባለ ሰላም ምላሽ ሰጠችው ከስው ጋር ማውራት አልፈለችም ። መፅሐፍት ማንበብ ጀመረች ።

ዐይኗን መጽሐፍት ላይ ተክላ እጇን ከጎና ወደ ተቀመጠው ቺፕስ ትልክና ኮርሸም ታደርጋለች ሰውዬውም መጽሔት በማንበብ ላይ ነው እርሱም እጅን ይዘረጋና ከቺፕሱ ያነሳል ሴትትዮዋ ድፍረቱ አስገርሟታል ፍቃድ እንኳን አልጠየቃትም ። ድጋሚ እጇን ልካ ከድንቹ ጥብሱ ላይ አነሳች ሰውየውም አስከተለ ኮርሽም አደረገ ሴትዮዋ ውስጧ በትዝብት ታመሰ ምን ዓይነት ደፋር ሰው ነው ! ስትል አጉመተመች ሰውዬው አልሰማትም ።

በዚህ መልኩ ሁለቱም ተራ በተራ እጃቸውን እየላኩ ቺፕሱን ማንሳት ቀጥለዋል የሰውዬው ድፍረት ይበልጥ አበሳጭቷታል ። ልትነገረው ሁሉ ቃጥቷት እንደምንም ራሷን ተቆጣጠረች ። ይቅርታ ማንሳት እችላለሁ? ቢለኝ እኮ አልከለክለውም ምን አይነት ሰው ነወ ? ስትል ከሯሷ ጋር አወጋች ። ቺፕሱ እያለቀ ነው የቀረችዋ አንዲት የተጠበሰች ድንች ነች ስውዬው ድንቿን አነሳና ለሁለት ከፈላት ግማሷን ለሴትዩዋ ሰጡ ። ይህ ሲያደርግ ይበልጥ አናደዳት ዐይንአውጣ አለች በልቧ ።

በራሪው መዳረሻ በመቃረቡ መንገደኞች የጥንቃቄ ቀበቷዋቸውን እንዲያጠባብቁ ከበረራ ክፍል መልዕክት ተላለፈ ። ከደቂቃዎች በዋል አውሮፕላን አረፈ መንገድኛው ሊወርድ ሲል አመሰግናለሁ አለማለቱ ደግሞ ሴትዮዋን እጅጉን ከንክኗታል ፊቱ ላይ ምንም ዓይነት የተለየ ስሜት አይታይበትም የእጅ ሻንጣውን ትክሻው ላይ አንጠጥሎ እጁን የሱሪ ኪሱ ውስጥ ከትቶ ተረጋግቶ ከአውሮፕላን ወረደ ሴትዮዋም ወረደች ሴትዮዋም በትዝብት ዐይን ክፍኛ እየገረፋችው ተከትላው ወረደች ።

ከአየር ማረፊያ በመነሳት ቀደም ሲል ወደ ያዘችው ሆቴል በታክሲ እያመራች ነው ። ዐይን አውጣው ሰውዬም በሌላ ታክሲ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሄዷል የሴትየዋ ሞባይል አቃጨለ ቦርሳዋን ከፈተችና ስልኳን ለማንሳት እጇን ወደ ቦርሳዋ ላከች እጇ አንድ ነገር ጨበጠ ማመን አቃታት በሀፍረት ላብ ተጠመቀች አየር ማረፊያው ውስጥ የገዛችው ቺፕስ ቦርሳዋ ውስጥ ነበር ።

በረራ ላይ እያለች የበላቸው ቺፕስ የሰውዬው መሆኑን ስታውቅ ተሽማቀቀች ። ዐይን
አውጣው እራሷ እንደሆነች ተሰማት አግኝታው ይቅርታ ብትጠይቀው ተመኘች ። እርሷ የተሰማት ስሜት ያልተሰማው በመሆኑ የላቀ ስብዕና ያለው የተከበረ ሰው መሆኑን ልትነግረው ወደዳች ዳሩ ግን ሰውዬው ከአካባቢው ርቋል ።

ሰንቶቻችን እርግጠኛ ባልሆነ መረጃ በሰዎች ላይ መጥፎ ስሜት አዳብን ይሆን ስንቶቻችንስ ሰዎች ለኛ የሚያደርጉትን መልካም ነገር እንደ ክፉ ቆጥረን ጠልተናቸው ። ንቀናቸው ወይም ታዝበናቸው ይሆን ስንቶቻችን የእኛብ ድፋነት ሳናስተውል ሌሎችን በዐይን አውጣነት ከሰናቸው ይሆን ? ........

· · • • • ጣፋጭ ቃላት • • • · ·

••●◉Join us share◉●••
@wubyefkr_kalat // ,, @zii_zuo


#መልካም_ምሽት