Get Mystery Box with random crypto!

Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamhara — Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ® V
የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamhara — Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®
የሰርጥ አድራሻ: @voaamhara
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.27K
የሰርጥ መግለጫ

Voice of Amhara Ethiopian በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካዊ ማህበራዊ ዘርፎችን የሚያነሳ የቴሌግራም ቻናል። ፈጣና ተአማኒ ነት ያላትቸውን መረጃዎች በፍጥነት ያግኙ!!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-10 11:23:04 ሰበር መረጃ!

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ከስልጣኗ ተነስታለች!
111 views#......, 08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 15:56:38
ደብረ ማርቆስ!

ደብረ ማርቆስ ዛሬም አድማው ተጠናክሮ ቀጥሏል። አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ሆነ የንግድ ሱቆችና ድርጅቶች ተዘግተው አድማውን ተቀላቅለዋል።
127 views#......, 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 15:52:55 መውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ ይሰጣል።(ትምህርት ሚኒስቴር)

መውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በመጪው ሰኔ  ወር  በአንድ ጊዜ እንደሚሰጥ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና ( ዶ/ር ) ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ  ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ከ6 ወራት  በኋላ እንደሚሰጥም ዶ/ር ኤባ  አስረድተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው ፈተናውን ለ200, 000 የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥና፣ ይህም የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ በመሆኑ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱም ሆኑ ተፈታኝ  ተማሪዎች ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አቶ ሰይድ አሳስበዋል።

በመውጫ ፈተና ብቃትና የፈተና ኮርሶች ልየታና የተገቢነት ማረጋገጥ ዙሪያ በተዘጋጀው አውደጥናት ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውም ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። (ዘገባውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ነው)

በመጨረሻም፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለተፈታኝ  ተማሪዎቹ እና ለሁሉም አካዳሚክ ስታፍ ፈተናው በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ አውቀው፣ተማሪዎችን በማብቃቱ ስራ ላይ ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ ሲል ያሳስባል።

ህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
https://t.me/VOAamhara
https://t.me/VOAamhara
https://t.me/VOAamhara
#shere
286 views#......, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 15:51:08 አማዞን ላይ ታገኙታላችሁ!



ዩኒቨርሲቲያችን ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ጊዚያት ሲያስጠና የቆየውን “ወረራና መዋቅራዊ ዘር ማጥፋት በወልቃይት-ጠገዴና ጠለምት” የሚል  የምርምር ውጤት መጽሐፍ በቅርቡ አሳትሞ ማስመረቁና ለአገር ውስጥ ለገበያ ማቅረቡ ይታወሳል።

በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተደራሽ ይሆን ዘንድ "አማዞን" ላይ እንደሚለቀቅ ቃል በገባነው መሠረት ዛሬ "አማዞን" ላይ ለሽያጭ ቀርቧል፡፡
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈንጠሪያ በመጫን እንዲገዙ ስናቀርብልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የመተርጎምና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የማቅረብ ሥራው በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቅርቡም  አማዞን ላይ በተመሣሣይ ለገበያ ይቀርባል።

(ዶክተር አስራት አፀደወይን)


https://www.amazon.com/dp/B0BP6WQC9N/ref=mp_s_a_1_1?crid=PK2RU6D0H7OV&keywords=Annexation+and+Structural+Genocide&qid=1670349981&sprefix=annexation+and+structural+genocide%2Caps%2C403&sr=8-1
108 views#......, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 11:14:15 መቀሌ

የመከላከያ ሠራዊት  መቐሌ ሊገባ ነው

በደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መሰረት  ህወሓት ሁሉንም ከባድ እና የቡድን መሣሪያዎቹን ለመከላከያ ሠራዊት እንዲያስረክብና የፌደራል መንግሥትም መቀሌን እንዲረከብ የሚያስችል ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል፡፡

ከትግራይ ክልል የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት በተለያዩ ግንባሮች  የሚገኙ ከባድ እና የቡድን መሣሪያዎቹን ለመከላከያ ሠራዊት ለማስረከብ በመቀሌ አቅራቢያ በሚገኝ  ሥፍራ እየሰበሰበ ይገኛል፡፡ ታጣቂዎቹንም ከሁሉም ግንባር በማምጣት የተሓድሶ ሥልጠና ወደሚሰጥባቸው  ካምፖችም አስገብቷል፡፡ ይህን ተከትሎም በስምምነቱ መሰረት የመከላከያ ሠራዊት በጥቂት ቀናት  መቐሌን እንዲረከብ መግባባት ላይ ተደርሶና አቅጣጫ ተቀምጦ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ መንግሥት በተከታታይ እየወሰደ የሚገኘው እርምጃ ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት ቁርጠኛ መሆኑን እንደሚያሳይ፤ ህወሓትም የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ያከናወናቸው እንቅስቃሴዎች ተስፋ ማጫራቸው የተለያዩ ምላሾች እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያውያንን እርስበእርስ በማጋጨት ትርፍ ለማግኘት ተጠንስሶ የነበረው ሴራ እየከሸፈ መምጣቱን መላው ዜጋ እንደ ትልቅ ብሥራት ሲቀበለው፤ በጠላት ሰፈር ግን ያልተገመተ መርዶ ሆኖ እዬዬው እንዲበረክት አድርጓል፡፡  ይሁንና ሁሉንም ጎራ ያስማማው አንድ ጉዳይ ይህንን ሂደት ወደ ኋላ የሚቀለብስ ኃይል አለመኖሩ ነው፡፡

በመላው ኢትዮጵያውያን በተለይ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ የተጣለበት የሰላም ስምምነት በመሰረታዊ አገልግሎቶች እጥረት ሲፈተን የነበረውን ኅብረተሰብ መከራ ስለሚያቀል፤ ከትምህርት ገበታ ተገልለው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን ተስፋ ስለሚያለመልም፤ በልጆቻቸው የተነሳ የሚሳቀቁትን እናቶችንም እንባ ስለሚያስቆም ሁሉም ለተግባራዊነቱ የድርሻውን ያበርክት፤ ሰላም ይስፈን::
107 views#......, 08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 11:13:15 ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ!

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከልኮ በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከኹለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግ በተነሳው ግጭት፣ ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ኹለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

የኦሮሚ ክል ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳውን ሲቃወሙ ነበር፡፡ ከመቃወምም አልፈው ወደፊት ችግር ሊፈጥር ይችላል በማለት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማውን በት/ት ቤቶች መሰቀሉን ይቀጥላል ከማለት ውጪ ያሉት ነገር የለም፡፡

    ( አዲስ ማለዳ )
110 views#......, 08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 16:05:50
የአማራ ተቋማትን የመምቻ ሰበብ!

ከዚህ ቀደም በምንም አይነት የአማራ እንቅስቃሴ ውስጥ የሌሉ ግለሰቦች ስም እየተጠራ፣ አንድ ድራማዊ ዶክመንተሪ ተሰርቶ ነበር። ከዛ በኋላ አማራን በጎጥ የሚከፋፍሉና ሌሎች የሀሰት ሰነዶች ወጥተዋል። ዛሬ ደግሞ የአማራን ሰላማዊ እንቅስቃሴ፣ ሲቪክ ተቋማትና ምሁራን ለመምታት ሌላ የሀሰት ሰነድ ተሰርቶ "አፈትልኮ የወጣ" እየተባለ እየተሰራጨ ነው። ሰነዱን የአማራን ተቋማት ለመምታት የሚያመቻች የሀሰት ሰነድ ስለመሆኑ በመሃል የሰነቀራቸው በርካታ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል።


በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች አማራ ላይ የተጀመሩት እንቅስቃሴዎች የዚህ እቅድ ጅምር ሆነው መሰል ሰነዶች በቀጣይ የአማራን ተቋማት ለመድፈቅ የሚሰሩ ስለመሆናቸው በወፍ በረር ይዘቶቹን  ማንበብ በቂ ነው።
129 views#......, 13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 16:03:37 ኦነግ "ሸኔ" የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጋር አብሮ እየሰራ እንደሚገኝ አምኗል።


"የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከአራት ኪሎ ትዕዛዝ መጠበቅ ትቶ በፋኖ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ። እኛም  በፋኖ ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው።  እንደሚባለው ተቀናጅተው ነው የሚባል ነገር የለም። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የአምባገነን ስልጣን መጠበቅ ትቶ ከህዝብ ጎን ሆኖ በምስራቅ ወለጋ  ሁሮ ጉድሩ መልካም ስራ ላይ ነው። ስለዚህ እነሱም ስራ ላይ ናቸው። እኛም ስራ ላይ ነን።"

የኦነግ "ሸኔ" ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ።


ማስገንዘቢያ፥ ፋኖ የሚሉት የአማራን ንፁሃንና የኦሮሚያ ክልል ያሰለጠናቸውን የአማራ ሚሊሻዎች ነው።

ተፈናቅሎ ጫካ ያለው አማራም የሚናገረው ከኦነግ ቃል አቀባይ ጋር ተመሳሳይ ነው። አጥቂው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው።
104 views#......, 13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 16:02:24
በኦነግ ሸኔ ታግቶ የነበረው ወንድማችን ተገደለ!

ኦሮሚያ ክልል ኩዮ ገብረ ጉራቻ ስሚንቶ ለመጫን ሄዶ፤ ከወር በፊት መንግስታዊ ድጋፍ ባለው ኦነግ ሸኔ ታግቶ  የነበረው ተጎድ ደነቀው በግፍ መገደሉ ታውቋል።

ሹፌር ተጎድ በጨኝ አውራጅነት እና በረዳትነት እየሠራ ጥሮ ግሮ እቁብ ገብቶ እና ተበድሮ ነበር፤ መኪናውን የገዛው። መኪናውን ከገዛው ዓመት አልሞላውም። አርመኔው ቡድን መኪናውን አቃጥለው፣ እሱንም አግተው አንድ ሚሊዮን ብር ክፍል ብለው፣ መጨረሻ ላይ በጭካኔ ገድለውታል። የተጎድን ግድያ ተከትሎ ደብረ ማርቆስ ላይ አሽከርካሪዎች እና ማኅበረሰቡ ሰልፍ ወጥቷል።
96 views#......, 13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ