Get Mystery Box with random crypto!

Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®

የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamhara — Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ® V
የቴሌግራም ቻናል አርማ voaamhara — Voice of Amhara የአማራ ድምጽ ®
የሰርጥ አድራሻ: @voaamhara
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.27K
የሰርጥ መግለጫ

Voice of Amhara Ethiopian በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካዊ ማህበራዊ ዘርፎችን የሚያነሳ የቴሌግራም ቻናል። ፈጣና ተአማኒ ነት ያላትቸውን መረጃዎች በፍጥነት ያግኙ!!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-14 14:21:08
የአብይ አህመድ የመደመር መፅሀፍ የአፋን ኦሮሞ ትርጉም ገፅ 375 ላይ እንዲህ ይላል:-

"በሬውን ዘርፈህ እረድበት፣
ሚስቱን ቀምተህ ውሰድበት፣
ቀየውን አቃጥለህ አውድም፣ ወደ አመድ ቀላቅለው፣
ሲቸገር የሚያደርገው ሲያጣ እራሱ ጉልበትህ ላይ ይወድቃል.."
https://t.me/VOAamhara
https://t.me/VOAamhara
19 views#......, edited  11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 14:18:00 ሰበር ዜና!

መምህርት መስከረም አበራ በድጋሜ ታሰረች!

የፖለቲካ ተንታኝ እና መምህር መስከረም አበራ የፌዴራል የጸጥታ አካላት ልብስ በለበሱ ግለሰቦች መወሰዷን ባለቤቷ አቶ ፍፁም ገብረሚካኤል ለአማራ ድምጽ ገለጹ።

ዛሬ ከቀኑ 11 ሰአት ገደማ 22 አካባቢ ከባለቤቷ ጋር ተቀምጣ በነበረችበት ወቅት የደህንነት አካላት ነን ያሉ ግለሰቦች እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ልብስ የለበሱ አካላት ለጥያቄ እንፈልግሻለን በሚለው ወደ ፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደወሰዷት ባለቤቷ ተናግሯል።

ባለፈው ግንቦት ወር በርካታ ጋዜጠኞች እና የማኅበረሰብ አንቂዎች በመንግስት የጸጥታ አካላት በታሰሩበት ወቅት መስከረምም ታስራ እንደነበር የሚታወስ ነው። መምህርት መስከረም "ንቃት" በሚል የዩቲዩብ ቻናሏ የፖለቲካ ሀሳቦቿን በማጋራት ትታወቃለች።

    
22 views#......, 11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 14:16:35 ኢዜማ

ኢዜማ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር እንዲዘመርና ባንዲራው እንዲውለበለብ የሚደረገው "ሕገወጥ ተግባር" እንዲቆም ትናንት ባወጣው መግለጫ በድጋሚ ጠይቋል።

ኢዜማ ድርጊቱ በቶሎ ካልተገታ ወደ ሕግ ወስጄ መፍትሄ እንዲያገኝ አደርጋለሁ ብሏል። "ሕገወጡ" ድርጊት እንዲቆም የሚጠይቁ ደብዳቤዎችን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ማስገባቱን የጠቀሰው ኢዜማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ግን ደብዳቤውን ሁለት ጊዜ አልቀበልም ማለቱን ገልጧል።

ፓርቲው ትምህርት ቢሮው በዚህ ድርጊቱ፣ "ለሕግ እንደማይገዛና በማናለብኝነት እንደሚንቀሳቀስ" አስመስክሯል በማለት ከሷል
21 views#......, 11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 14:11:28 አደራችሁን! አቅልላችሁ እንዳታዩት!

ከስር የሶስቱ ክልሎች መዝሙር ላይ የተቀነጨቡ ስንኞች ተቀምጠዋል። እያወራን ያለነው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በግለሰብ ስለተለቀቀ ጉዳይ አይደለም። አንድ ሰሞን መነጋገሪያ ስለሆነ ነጠላ ዜማ አይደለም። ትውልድ 30 አመት በላይ አይኑን ጨፍኖ በስሜት እየዘመረው ስለመጣበት ጉዳይ ነው ልዩነቱን ታገኙታላችሁ።

1)የኦሮሚያ ክልል መዝሙር

የመቶ አመት እድፍ ፥ በደማችን አጠብንልሽ
በብዙ እልፍ እልቂት ፥ ባንዲራሽን ከፍ አደረግን
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ፥ ስልጣንን መልሰን አገኘን
...........
ኃይላችንን አሰባስበን ፥ ተነስተናል ተማመኚብን
ኦሮሚያ አብቢ ፥ ለምልሚና ኑሪ!

2)  የትግራይ  ክልል መዝሙር
.....
በጭራሽ አንሸነፍም!
......
በፀሀይ ሀሩር እና በቁር
ነፍሳችን ውሀ ይጥማት
አለት ይሁን ትራሳችን
ዋሻ ይሁን ቤታችን
ሌትም ቀንም ጉዞ ይድከመንም ይራበንም
.............
በጅቦች እንከበብ መሬት ይክበበን
የጠላቶቻችን ጥርስ ስጋችን ውስጥ ይቀርቀር!
ስጋችን ላሞራ ደማችን እንደ ጎርፍ ይፍሰስ፤
አጥንታችን ይድቀቅ ዱቄት ሆኖ ይበተን
............
የጦር መሳሪያ መርዝ ፋሽስታዊ ንዳድ
ሚሊየን ጠላቶቻችን ፊታችን ላይ ይጉረፉ
መስዋዕትነት መቁሰል እና ኪሳራም እንከፍላለን፤
የከፋ መከራም ቢመጣ ወደን እንከፍላለን

3) የአማራ ክልል መዝሙር
የአማራነት ክብር ደማቅ አርማ ይዘን ፥
ከሌሎች ህዝቦች ጋር እኩል ተከባብረን
በፍቅር በአንድነት አብረን እንዘልቃለን ።

በነገራችን ላይ አማራ ክልል ብዙ አካባቢዎች ይህ የአማራ ክልል መዝሙር እንደ ከፋፋይ ተቆጥሮ ተማሪዎች የኢትዮጵያ መዝሙርን እንዲዘምሩ ይደረግ ነበር። አንዳንድ ክልሎች ደግሞ እንደ አሁኑ ማህበራዊ ሚዲያ ሳይኖር ህዝብን በመዝሙር መስደብን ስልት አድርገውታል። ሊረዝምባቸው ሆኖ ተቸግረው ይሆናል እንጅ ግለሰብ ጠቅሰው ቢሰድቡም ደስ የሚላቸው አይጠፉም።
21 views#......, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 08:15:02 በማዕከላዊ ጎንደር  ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ  የእህቱን ልጅ አግቶ 150 ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ በምዕራብ  አርማጭሆ ወረዳ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ።

የወረዳው ፖለስ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢንስፔክተር አበበ ደጀን እንደተናገሩት  የታጋች ስም ህፃን አሜሪካው እያዩ  እንደ ሚባል ጠቁመው የ3 ዓመት ህፃን መሆኑን ተናግረው የአጋች ስም ገበያው በሌ ታረቀኝ  ሲሆን ነዋሪነቱ በምስራቅ  ደምቢያ ወረዳ የአይንባ  ንዑስ ወረዳ ነዋሪ እንደሆነ ጠቅሰው የእህቱን ልጅ በማገት 150 ሽ ብር ለመጠየቅ  መሆኑን ኢንስፔክተሩ  አስረድተዋል ።

ሰለሆነም አጋቹ በቁጥጥር ስር የዋለው በቀን 01/04/2015  ዓ/ም  ከምሸቱ 1:00  መሆኑን ከፖሊስ ያገኘነው  መረጃ  ያመለክታል ።

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
89 views#......, 05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:31:47
የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ስጦታ ተበረከተ!

የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ!

የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በራያ ቆቦ ወረዳ 042 ቀበሌ ልዩ ስሟ ጎለሻ በምትባል ቦታ በደማቅ ሁኔታ ታስቦ ውሏል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ፋኖ አንድነት ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰፈር መለሰ የተገኙ ሲሆን የመንግሥት ስልጣንን ሽፋን በማድረግ ፋኖን የማሳነስ እና የማንኳስ ስራ ላይ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው የገለፁ ሲሆን ፋኖ አገርን ከውርደት የታደገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑንም ተናግረዋል ።

የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ ኃላፊና እና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና አዛዥ ዋርካው ሻለቃ ምሬ ወዳጆ በበኩላቸው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከመከላከያ ጋር በመሠለፍ ብዙ ጓዶች ቢሰውም ታሪክ የማይረሳው ጀብዶ መሥራታቸውን ተናግረዋል።

ስለሆነም ያለመስዋዕትነት አሸናፊነት እና ክብር ስለማይገኝ የአገርን ህልውና  ለመጠበቅ ሁሉም ፋኖ መሆን አለበት ብለዋል።በዕለቱ በክብር ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ፋኖዎች እውቅናና የትግል ታሪካቸው ተነግሯል።

የሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ስጦታም ተበርክቷል።
118 views#......, 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 11:28:46 የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ስጦታ ተበረከተ!

የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ!

የአማራ ፋኖ አንድነት የምስራቅ አማራ ፋኖ ዝክረ ሰማዕታት እና የተሃድሶ ፕሮግራም በራያ ቆቦ ወረዳ 042 ቀበሌ ልዩ ስሟ ጎለሻ በምትባል ቦታ በደማቅ ሁኔታ ታስቦ ውሏል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ፋኖ አንድነት ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰፈር መለሰ የተገኙ ሲሆን የመንግሥት ስልጣንን ሽፋን በማድረግ ፋኖን የማሳነስ እና የማንኳስ ስራ ላይ መጠመዳቸው እንዳሳዘናቸው የገለፁ ሲሆን ፋኖ አገርን ከውርደት የታደገ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑንም ተናግረዋል ።

የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ ኃላፊና እና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና አዛዥ ዋርካው ሻለቃ ምሬ ወዳጆ በበኩላቸው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከመከላከያ ጋር በመሠለፍ ብዙ ጓዶች ቢሰውም ታሪክ የማይረሳው ጀብዶ መሥራታቸውን ተናግረዋል።

ስለሆነም ያለመስዋዕትነት አሸናፊነት እና ክብር ስለማይገኝ የአገርን ህልውና  ለመጠበቅ ሁሉም ፋኖ መሆን አለበት ብለዋል።በዕለቱ በክብር ሰማዕትነትን ለተቀበሉ ፋኖዎች እውቅናና የትግል ታሪካቸው ተነግሯል።

የሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምስል ያለበት ስጦታም ተበርክቷል።
112 views#......, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 16:43:31 አሳዛኝ ዜና!

ከዲጋ፣ አርጆ ጉደቱ በበርካታ መኪና ተጭኖ ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር በመስፋፋት እና በመውረር የሚታወቀው ኦነጋዊ ጥምር ኃይል በከማሽ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ላይ ጦርነት በመክፈት ሰላማዊ አማራዎችን እየገደለ እና እያፈናቀለ መሆኑን በየጫካ የሚሳደዱ ነዋሪዎች ገለጹ።

ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ከአርጆ ጉደቱ በበርካታ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ዛሬ ታህሳስ 1/2015 ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ኦነጋዊ ኃይል እየተስፋፋ እና እየወረረ መሆኑ ተገልጧል።

በከማሽ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ላይ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ ጦርነት ከፍቷል።

የተደራጀ እና የተቀናጀ ጥቃቱን የከፈተውም በበለው ጅጋንፎይ/በሚዥጋ ወረዳ መንደር 42/ተንካራ በሚባል አማራዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው።

እየገደለ እና እያፈናቀለ መሆኑን በየጫካ የሚሳደዱ ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን አሁንም ከአርጆ ጉደቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የአሸባሪው ሸኔ አባላት ወደ መንደር 42 እየገቡ ነው።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በከባድ መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ንጹሃንን እያጠቁ፣ ወረራውን አጠናክረው እየቀጠሉ መሆኑን የአሚማ ምንጮች ገልጸዋል።

በአስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው።

ይህ ወረራ መሆኑን የሚገልጹት ነዋሪዎች መንደር 42ን ብቻ ሳይሆን ወረዳውን ጭምር ለመቆጣጠር አልሞ የመጣ የሚመስል ከፍተኛ ኃይል ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በተንካራ/መንደር 42/ አማራዎች መውጫ አጥተው እየተሰቃዩ የከረሙበት አካባቢ ነው።

የሚዥጋ ወረዳም ሆነ የከማሼ ዞን ንጹሃንን ለመታደግ እየሰሩ አለመሆኑ ምክር እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል ምንጮች።

    
126 views#......, 13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 11:28:08 በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!
*
በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት ዓመታት ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ለመትከል ፣ እኩልነትን ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ሕዝብ የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ለማድረግ በርካታ መስዋዕትነት የተከፈለ እና በብዙ ውጣውረዶች ውስጥ ያለፍን ቢሆንም ፣ ትግላችን እና ጉዟችን ከድጡ ወደማጡ እየሆነ ፣ ሀገራዊ ፈተናዎቻችን እየበረቱ እና አዳዲስ ችግሮች እየተፈጠሩ በአሁኑ ወቅት ሀገራዊ ኅልውናችንን እና አንድነታችንን ላይ አደጋ የጋረጡ ፈተናዎች ከፊት ለፊታችን ተደቅነው ይገኛሉ፡፡ ባለፉት አምስት አስር ዓመታት ውስጥ በሀገራችን ኢትዮጵያ ከተፈጠሩ ፖለቲካዊ የኃይል አሰላለፎች ውስጥ ዋነኛ ኃይል ሆኖ የወጣው “የነጻ-አውጭዎች” የኃይል አሰላለፍ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት በመፈረጅ እድልና አጋጣሚ በፈቀደለት ጊዜና ሁኔታ ውስጥ ሁሉ በሕዝባችን ላይ ተነግሮ የማያልቅ መከራ እና እልቂት ሲያደርስ ቆይቷል፡፡

ሀገር ለማፍረስ ተማምለው ጫካ የወረዱ እና በለስ ቀንቷቸው አራት ኪሎ እግር የጣላቸው “ነጻ-አውጭ” ድርጅቶች ያለሕዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫኑት ሀገር-አፍራሽ ሕገ-መንግስታዊ ሥርአት እና አፓርታይዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ስራ ላይ ከዋለበት ካለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፖለቲካዊ ቀውሱ እና ምስቅልቅሉ ወደ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል እንዲወርድ እና በየእለቱ የወገኖቻችን ሕይወት የሚቀጠፍበት ፣ ከቀያቸው የሚፈናቀሉበት እና በማያቋርጥ የእልቂት እና የቀውስ አዙሪት ውስጥ ተዳርገን እንገኛለን፡፡ የቀውስ አዙሪቱ ተባብሶ ቀጥሎ ቀድሞ እያሰለሰ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጸም የኖረው የዘር-ማጥፋት ወንጀል አሁን የዕለት ተዕለት ክስተት እና የተለመደ የአዘቦት ተግባር ወደመሆን ተሸጋግሯል፡፡ በዚህ የቀውስ አዙሪት ውስጥ ዋነኛው ገፈት ቀማሽ የአማራ ሕዝብ ቢሆንም የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የቀውስ አዙሪቱ ተጠቂ እና የግፍ ጽዋው ተቋዳሽ መሆናቸው አልቀረም፡፡

በሥራ ላይ ያለው ሀገር-አፍራሽ ሕገ-መንግስት እና አፓርታዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ዋነኛ አርክቴክት እና አናጺ የሆነው አሸባሪው ትሕነግ በጦር ግንባር ተሸንፎ ትጥቅ ለመፍታት መፈረሙን ተከትሎ ፣ የሽብር ቡድኑ ይፋዊ አጋር የሆነው ኦነግ-ሸኔ እና በህቡዕ እና በይፋ ለቡድኑ ሥልታዊ እና ቀጥተኛ ድጋፍ ሲሰጡ የቆዩት የኦሮሚያ ክልልን የሚዘውሩ አንዳንድ ባለስልጣናት ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የወደቁ ሲሆን ፣ በአዲስ አበባ እና በፌዴራል መንግስቱ ውስጥ ያለውን መዋቅራቸውን በማንቀሳቀስ በኦሮሚያ ክልል ፣ በአጎራባች ክልሎች እና በአዲስ አበባ ከተማ ቀውስ ለመፍጠር እና ሀገር ለማተራመስ የመጨረሻውን አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም ወደለየለት የሽብር ስራ ገብተዋል፡፡ በውጤቱም በበርካታ የወለጋ ዞኖች በአማራ ተዋላጆች ላይ እያሰለሱ ሲፈጽሙት የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀል የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ያደረጉ ሲሆን ፣ በፌዴራል መንግስት መዋቅሮች ውስጥ በየደረጃው በተቀመጡ አስፈጻሚወቻቸው በኩል በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልል መዝሙር ዘምሩ እና የኦሮሚያን ባንዲራን አውለብልቡ የሚል የማተራመሻ ስልት ይዘው በመግባት፣ በህጻናትና በመምህራኖች ላይ ነውረኛ ጫና በመፍጠር አዲስ አበባ ከተማን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ ያለ የሌለ አቅማቸውን አሟጠው እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡

በጫካ ያለውም ሆነ የመንግስት መዋቅርን የተቆጣጠረው ኦነግ-ሸኔ ወደ ለየለት የሽብር ተግባር ውስጥ ገብተው ንጹሃንን ዕለት በዕለት የሚጨፈጭፉት እና አዲስ አበባ ከተማ ድረስ ዘልቀው አዲስ የቀውስ ማዕከል ለመፍጠር እየተጣጣሩ ያሉት ፣ ተሸንፎ እጅ የሰጠውን የጥፋት አጋራቸውን እና አሸባሪውን ትሕነግ ከገባበት ቅርቃር ለማውጣት እና እነሱም የማይቀርላቸውን የሽንፈት ጽዋ ላለመጎንጨት የመጨረሻውን መንፈራገጥ እያደረጉ ለመሆኑ (The last kick of a dying horse) ማሳያ ከመሆን የሚያልፍ አይደለም፡፡ ከሁሉም በላይ አሸባሪው ኦነግ-ሸኔ እና የኦሮሚያ ክልልን የሚዘውሩት አንዳንድ ባለስልጣናት በአማራ ተወላጆች ላይ እየፈጸሙት ያሉት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፣ በኦሮሚያ ክልል እየፈጠሩት ያለው ፖለቲካዊ ምስቅልቅል እና አዲስ አበባን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ እየሄዱበት ያለው እርቀት የሚያረጋግጠው የስብስቡን ጥንካሬ ሳይሆን ፣ በሥራ ላይ ያለው አፓርታዳዊ የአስተዳደር መዋቅር ለሽብርተኝነት እና ሽብርተኞች መደበቂያነት የተመቸ መዋቅር መሆኑን ፣ ሥርአቱ የመጠቀሚያ ጊዜው ያለቀ እና ሊጠገን በማይችል ስብራት ላይ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡

ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ሕዝብ ላይ የኅልውና አደጋ የደቀኑትን የፖለቲካ ኃይሎች ነጥሎ ሲታገል የቆየ ሲሆን ፣ ይህን የትግል መስመር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ፓርቲያችን አብን የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን የኅልውና አደጋ ለመቀልበስ በሚችልበት የተሟላ አቋም ላይ እንደሚገኝ ይተማመናል! ሕዝባችን ሊሸነፉ አይችሉም የተባሉ ጠላቶቻችንን በአስደናቂ ተጋድሎ እያሸነፈ እና እጅ እያሰጠ በድል ግስጋሴ ላይ እንደሚገኝ ጠላትም ወዳጅም የሚውቀው ሃቅ ነው፡፡ ባልታጠቁ እና ራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ ህጻናት ፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ሲቪል ወገኖቻችን ላይ በየእለቱ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ እና እልቂት ሀዘን አጥንታችን ድረስ ዘልቆ ቢገባም ፣ እንደ ሕዝብ እየተፈጸመብን ያለው የማያባራ ጥቃት አንገታችንን አያስደፋንም! ለጠላቶቻችን እጅ አያሰጠንም! ኦነግ-ሸኔ እና በመንግስት የሲቪልና የጸጥታ መዋቅር ተሰግስገው በሕዝባችን ላይ ያለእረፍት ጭፍጨፋ እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙ ያሉት እና አዲስ አበባ ከተማን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ እየተውተረተሩ ያሉት ሽብርተኞች ምኞት እንደማይሳካ እና ሽንፈታቸው የማይቀር ለመሆኑ ፓርቲያችን በጽኑ ያምናል፡፡ 

ፓርቲችን አብን ለመላው የአማራ ሕዝብ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አንድነቱን እንዲያጠናክር ጥሪውን እያስተላለፈ ፣ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በግፍ እየተጠቃ ካለው የአማራ ሕዝብ ጎን እንድትሰለፉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ድል ለአማራ ሕዝብ! ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ! 

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)
አዲስ አበባ ፣ ሸዋ፣ ኢትዮጵያ
ሕዳር 30 ቀን 2015
137 views#......, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 11:24:23 #ሰበር ዜና#

ከ25 በላይ አርሶ አደሮች በኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተሰማ!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ አዝመራ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከ25 በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች በኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

በሳሲጋ ወረዳ ልዩ ስሙ ሃያ አራት ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ህዳር 27/2015 ዓ/ም በከፈቱት ጥቃት አዝመራ ስብሰባ ላይ የነበሩ ከ25 በላይ የአማራ ተወላጆችን መገደላቸውን ነው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ያረጋገጡት።

የፀጥታ ኃይሎቹ ህዳር 24/2015 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በሃያ አራት ቀበሌ ማሳ ለማሳ እየዞሩ ፋኖ ያለበትን ለምን አልጠቆማችሁንም በሚል አዝመራ ሲሰበስቡ የነበሩ አርሶ አደሮችን ከሰበሰቧቸው ቦኋላ በስለት እንደገደሏቸው ነው ከጥቃቱ የተረፉ የአይን እማኞቹ የገለፁት።

የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች አርሶ አደሮችን ከገደሉ ቦኋላ አስከሬናቸው በየማሳው የጣሉት ሲሆን ከቀናት ቦኋላ የዘጠኙ ሟቾች አስከሬን ተገኝቶ ዛሬ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ስርአተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።

ከሟቾቹ መካከል፦
እንድሪስ አህመድ፣
በለጠ እንድሪስ፣
ጀማል አህመድ፣
ጀማል ሁሴን የተባሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል የተባለ ሲሆን ሌሎች በጉልበት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች እና በአዝመራ ስብሰባ ስራ ላይ ለነበሩ ቤተሰቦቻቸው ምግብ ለማድረስ የሄዱ ታዳጊዎችም እንዳሉበት የአይን እማኞቹ ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

ከአንድ አከባቢ ብቻ አዝመራ ስብሰባ ላይ እንዳሉ የተገደሉት የአማራ ተወላጅ የ25 አርሶ አደሮች ናቸው ሲሉ ለአማራ ድምፅ የገለፁት የአይን እማኞቹ፡የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች በሃያ አራት ቀበሌ ስር በሚገኙ ሌሎች አከባቢዎችም የገደሏቸውን አርሶ አደሮች አስከሬናቸውን በፓትሮል ጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰዱትም ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፀጥታ ኃይሎች በተለይ ከህዳር 9/2015 ዓ/ም ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ፣ጊዳ፣ሳሲጋ በተባሉ ወረዳዎች እንዲሁም በሆሮ ጉድሩ ወለጋ አሙሩ፣ጃርጄጋ ጃርቴ፣ሆሮ ቡሉቅ በተባሉ ወረዳዎች ስር በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ 300 የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች እንደተገደሉ የአማራ ድምፅ ሚድያ የአይን እማኞችን በማነጋገር በተለያየ ግዜ በሰራው ዘገባ አረጋግጧል።

    (የአማራ ድምፅ)
120 views#......, 08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ